አንቶን ግሪዝማን ከአትሌቲኮ ማድሪድ ደጋፊዎች ባደረገለት አቀባበል ምክንያት ክለቡን ለመልቀቅ ተቃርቧል፡፡ ግሪዝማን ለረጅም ጊዜ ስሙ ከባርሴሎና ጋር ሲያያዝ ነበር፡፡ ይሁንና ባለፈው ሳምንት ደግሞ በአትሌቲኮ መቆየት እፈልጋለው ብሏል የሚሉ ዘገባዎችም ወጥተው ነበር፡፡ ቢሆንም በዋንዳሜትሮፖሊታኖ በተደረገለት አቀባበል ደጋፊዎቹ በመጮሃቸው እና በማፏጫተው አሁን ዳግመኛ ክለቡን እንዲለቅ ሊያስገድድው እንደሚችል ተዘግቧል፡፡ (Marca)
ቸልሲዎች የባየር ሙኒኩን ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በዚህ ክረምት ለማስፈረም ከሚፈልጓቸው ተጫዋቾች ውስጥ የመጀመሪያ ተፈላጊ አድርገውታል፡፡ በአንቶኒዮ ኮንቴ የመጀመሪያ የአሰልጣኝነት ዘመን የፕሪሚየር ሊጉ ቻምፒየን የሆኑት ቸልሲዎች በዚህኛው የውድድር አመት ግን አምስተኛ ሆነው ለመጨረስ ተገደዋል፡፡ እንዲሁም በቀጣዩ የውድድር አመት በቻምፒየንስ ሊግ የመሳተፍ እድልም አጥተዋል፡፡ የአንቶኒዮ ኮንቴ የወደፊት እጣ ፈንታ እስካሁን ያልተወሰነ ቢሆንም፤ አልቫሮ ሞራታ ክለቡን ይለቃል ተብሎ ስለሚጠበቀው በሱ ምትክ ሮበርት ሌዋንዶዊስኪን የመጀመሪያ ምርጫ አድርገዋል፡፡ (Telegraph)
ማንችስተር ሲቲ የሌዚስተሩን ሪያድ ማህሬዝ ለማስፈረም ተቃርቧል፡፡ ማህሬዝ በ2015/16 ቻምፒየን የሆነው የሌዘስተር አስገራሚ ቡድን አባል ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ተላያዩ ክለቦች ለመዘዋወር በራሱም ጭምር ጥያቄ አቅርቦ አልተሳካለትም፡፡ አሁን ግን ሲቲዎች በ60 ሚ. ፓውንድ ልጁን ወደ ኢቲሃድ ለማዘዋወር ተቃርበዋል፡፡ (Manchester Evening News)
ቡፎን የወደፊት እጣ ፈንታውን ለመወሰን ቢያንስ ሳምንት እንደሚፈልግ አስቃወቀ፡፡ ከጁቬንቱስ ጋር የተለያየው ቡፎን ስሜቴን ለማረጋገት ሳምንት እፈልጋለው ብሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ፒኤስጂም ሆነ ሌላ ክለቡ ዝነኛውን ግብ ጠባቂ ለማስፈረም የተወሰኑ ቀናቶችን ለመጠበቅ ይገደዳሉ፡፡ (Goal)
ለሳሪ ምንም አይነት የቀረበ ክፍያ የለም፡፡ የናፖሊው አሰልጣኝ ማውሪዚዮ ሳሪ ክለቡን ሁለተኛ ሆኖ እንዲያጠናቅቅ ከረዱት በኋላ በተለያዩ ክለቦች በመፈለግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ቸልሲ፣ ዜኒት እና ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ የሚለቅ ከሆነ ቶተንሃሞች አሰልጣኙን ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን የአሰልጣኙ ወኪል አሌሳንድሮ ፔሌግሪኒ እስካሁን ምንም አይነት ክለብ ጥያቄ እንዳላቀረበ እና እሳቸውን መቅጠር የሚፈልግ ክለብ የውል ማፍረሻ የሆነውን 8 ሚ. ዩሮ ለናፖሊ መክፈል ይኖርበታል፡፡ (Goal)
═════════════════════════
📂 ADVERTISEMENTS
የቴሌግራም ገፃችንን ይጎብኙ:
➧ https://t.me/hair_regrowth
═════════════════════════
አርሰናሎች ኡናይ ኤምሪ አሰልጣኛቸው እንዲሆን መርጠዋል፡፡ አርሰን ቬንገር አርሰናልን መልቀቃቸው ተቀትሎ በርካታ ስሞች ከአርሰናል ጋር ሲያዝ ነበር፡፡ እስከ ትላንት ድረስም ሚኬል አርቴታ የአርሰናል አሰልጣኝ የመሆን እድል አለው ሲባል ነበር፡፡ ይሁንና አሁን አርሰናሎች ኡናይ ኤምሬን ለመቅጠር እንደወሰኑ ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡ በቫሌንሺያ እና ሲቪያ በውስን በጀት ቡድኖቹን ከሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና ጋር እንዲፎካከር ያደረገው ኤምሬ ለአርሰናል ተስማሚ መሆኑ በቦርዱ ታምኖበታል፡፡ በዚህም ምክንያት ቀጣዩ የአርሰናል አሰልጣኝ የዚህ አመቱ የፈረንሳይ ምርጥ አሰልጣኝነት ሽልማትን ያገኘው ኡናይ ኤምሬ ይሆናል፡፡ (Goal)
ኔይማር ወደ ሪያል ማድሪድ ለማምራት ይፈልጋል፡፡ ብራዚላዊው ኮከብ ለክለቡ ፒኤስጂ መልቀቅ እንደሚፈልግ ተናግሯል፡፡ ወኪሉም ቢሆን ከሪያል ማድሪዱ ፕሬዚዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ጋር ተነጋግሯል፡፡ ይሁንና ክለቡ ፒኤስጂ እንዲሁ በቀላሉ ተጫዋቹን የሚለቀው አይሆንም፡፡ ዝውውሩም ከአለም ዋንጫው በኋላ እንጂ ከዛ ወዲ የመጠናቀቅ እድልም አይኖረውም፡፡ (Goal)
ሳንቲ ካዞርላ ከአርሰናል ጋር ተለያየ፡፡ ስድስት አመታትን ከአርሰናል ጋር ያሳለፈው ካዞርላ በጉዳት ምክንያት ከ2016 ወዲህ ለክለቡ ተሰልፎ አልተጫወተም፡፡ ኮንትራቱም በመጠናቀቁ ምክንያት አርሰናሎች ሊለቁት ወስነዋል፡፡ ካዞርላም ወደ ቪያሪያል ሊያመራ ይችላል፡፡ ካዞርላ ለቪያሪያል ከ2007-2011 ተጫውቶ ነበር፡፡ አሁን ለቅድመ ልምምድ ወደክለቡ ይመለሳል፡፡ ይሁንና ስለቀረበለት ኮንትራት ምንም የተባለ ነገር የለም፡፡ (Goal)
ፔሌግሪኒ የዌስትሃም አሰልጣኝ ለመሆን ተስማሙ፡፡ ቺሊያዊው የቀድሞ የማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የቻይናውን ሄቤ ፎርቹን በማሰልጠን ላይ ነበሩ፡፡ አሁን ከክለቡ ጋር የተለያዩ ሲሆን ወደ አሰልጣኝነት የመመለስ ፍላጎትም አላቸው፡፡ ወደ ለንደን አቅንተው ከዌስትሃም ባለቤት ዴቪድ ሱሊቫን ጋር ተነጋግረዋል፡፡ (Telegraph)
ባርሴሎናዎች የቶተንሃሙን ወጣት ቲዮ ግሪፊት ለማስፈረም ተስፋ ሰንቀዋል፡፡ በሌላ ቶተንሃሞችም የባርሴሎናውን ሪካርድ ፒዩጅ ለማስፈረም ተስፋ አድርገዋል፡፡ ባርሴሎናዎችም በድር በምድር ያሉ ይመስላል የ18 አመቱን የቶተንሃም ወጣት ለመውስድ ተዘጋጅተዋል፡፡ (Daily Star)
ሊቨርፑሎች ሁለት ተከላካዮች ላይ አነጣጥረዋል፡፡ በ75 ሚ. ፓውንድ ቨርጂል ቫንዳይክን ከሳውዛምፕተን ያስፈረሙት ሊቨርፑሎች አሁንም የተከላካይ መስመራቸውን ማጠናከር ይፈልጋሉ፡፡ የኒውካስትሉ ጀማል ላሰል እና የበርንሌው ጀምስ ትራኮወስኪ የሚለጉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡ (Independent)
ጆሴ በተሰናባቹ ምክትል አሰልጣኝ ሩዪ ፋሪያ ቦታ ኬረን ማክኬናን ሹሟል፡፡ ማክኬና የዩናይትድ ከ18 አመት በታች አሰልጣኝ ሲሆን፣ ባለፈው አመት ነበር ከቶተንሃም ወደ ማንችስተር የተቀላቀለው፡፡ ያሰልጥነው የነበረው የ18 አመት በታች ቡድንም የሰሜን ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አሸንፏል፡፡
(ምንጭ፡ Sky Sports News)
ዌስትሃም ዩናይትድ ማኑዌል ፔሌግሪኒን አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ። ፔሌግሪኒ የ3 አመት ኮንትራትም ከለንደኑ ክለብ ጋር ተፈራርመዋል:: ማኑዌል ፔሌግሪኒ ከዚህ በፊት ከማንችስተር ሲቲ ጋር ቻምፒየን ሆነው ነበር፡፡
አርሰናል በቀጣይ የውድድር አመት ለብሶ የሚጫወትበትን ማለያ ይፋ አድርጓል፡፡ ቁጥራቸው የተቀየረላቸው ተጫዋቾችም አሉ፡፡
ፒተር ቼክ 1 ቁጥር፣
ቤሌሪን 2፣
ሙሀመድ ኤልኔኒ 4፤
ግራኒት ዣካ ደግሞ 34 ቁጥር ይለብሳሉ፡፡
═════════════════════════
📂 ADVERTISEMENTS
የቴሌግራም ገፃችንን ይጎብኙ:
➧ https://t.me/ethio_bodybuilders
═════════════════════════