ARSENAL & CITY WANT £5M AJAX MIDFIELDER
የእንግሊዞቹ ክለቦች የሆኑት አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ የኒዉዘርላንዱ ክለብ የሆነዉ የአያክስ አምስተርዳሙን ተጫዋች ፍሬንኪ ዲጆንግን በ€5 million ለማስፈረም ፉክክር ዉስጥ ገብተዋል።
ዘ ሰን እንዳለዉ ከሆነ የ20 አመቱን ወጣቱን ተጫዋች አምና በኢሮፖ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ ክለቡ አያክስ ከ ማንችስተር ዩናይትድ ሲጫወቱ ሌላኛዉ የፕሪሜር ሊግ ክለብ የሆነዉ ቼልሲ በልጁ ብቃት በመሳባቸዉ ባለፈዉ ክረምት ሊያስፈርሙት ቢሞክሩም ሳይሳካለት ቀርቶል።
አማካኙ በሁለቱ የፕሪሜር ሊግ ክለቦች አርሰናል እና ማን ሲቲ መፈለጉ ተከትሎ አንዳቸዉ ልጁ ወደ እንግሊዝ ማስኮብለላቸዉ አይቀርም ተብሎል።
LIVERPOOL AND INTER WANT DAVID SILVA
ሊቨርፑል እና ኢንተር ሚላን የማንችስተር ሲቲዉን የጨዋታ አቀጣጣይ ዳቪድ ሲሊቫ ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል።
ሲሊቫ በማንችስተር ሲቲ ጥሩን ጊዜ እያሳለፈ ቢገኝም ተጫዋቹ በክለቡ ጥሩ ወራዊ ደሞዝ አያገኝም በዚህም ምክንያት ሊቨርፑል እና ኢንተር ተጫዋቹን ጥሩ ሳምንታዊ ደሞዝ የሚከፍሉት ከሆነ ተጫዋቹ ክለቡን ይለቃል ተብሎ ይታሰባል።
የ31 አመቱ ጎልማሳ ዳቪድ ሲሊቫ በማን ሲቲ ያለዉ ኩንትራት በፈረንጆች 2019 ይጠናቀቃል።
ነገር ግን ሲሊቫ በፔፕ ጋር ዲወላ መወደዱ ክለቡ ለተጫዋቹ ጥሩ ደሞዝ በማቅረብ በክለቡ ሊያቆዩት እንደሚችሉ ተነግሮል። (daily mail)
CITY TO RIVAL MAN UTD FOR ESPANYOL LEFT-BACK
ሁለቱ ማንችስተር ሲቲ እና ማንችስተር ዩናይትድ የስፓኞሉን የግራ መስመር ተመላላሹን አሮን ማርቲን ለመስፈረም ፉክክር ዉስጥ ሊያደርጉ ነዉ።
ፔፕ ጋርዴዉላ በክረምቱ የዝዉዉር መስኮት ከሪያል ቤትስ ያስፈረሙት ቤንጃሜን ሜንዴ በአሁኑ ሰአት በጉዳት ምክንያት ክለቡን ማን ሲቲ እያገለገለ አይገኝም። ሁኖም የሜንዴ ጉዳት ለእረጅም ጊዜ ከሜዳ የሚያርቀዉ መሆኑን ተከትሎ የቦታዉ ተተኪ ለማድረግ ሲል ሲቲ ተጫዋቹን ለማስፈረም ከፍተኛ የዝውውር ሂሳብ ያቀርባል ተብሎል።
ሁኖም ሁለቱ የማንችስተር ከተሞች የ22 አመቱን ወጣት ለማስፈረም የጥር ወር የዝውውር መስኮት እየተጠባበቁ ነዉ ተብሏል ሲል sky sport ዘግቧል።
BARCA WATCH CHELSEA & MAN UTD STARS
የባርሴሎና ቴክኒካል ሴክሪታር የሆኑት ሮበርት ፈርናንዴዝ እና ዩርባኖ ኦርቴጋ ትናንት በስታምፎርድ ብሪጅ ቼልሲ ማንችስተር ዩናይትድን 1፣0 በሸነፈበት ጨዋታ ላይ የቼልሲ እና የማን ዩናይትድ ተጫዋቾችን ተመልክቶቾዋል።
ከተጫዋቾች መካከል በቼልሲ በኩል በጨዋታዉ አመቻችቶ ያቀበለዉ ሴዛር አዝብሊኪታ እና በጨዋታዉ የማሸነፊዋን ጎል ያስቆጠረዉ አልቫሮ ሞራታ ሲሆኑ፤በማንችስተር ዩናይትድ በኩል ተቀይረዉ ወደ ሜዳ የገቡትን አንድሬ ሄሬራን እና አንቶን ማሪሲያል ናቸዉ።
ሁኖም አራቶቹ ተጫዋቾች በባርሴሎና አለቆች ተወደዋል በዚህም ባርሴሎና የማስፈረም ስራ ሊሰራ ይችላል ተብሎል። (bbc)
MAN UTD WANT DONNARUMMA TO
REPLACE DE GEA
ጆዜ ሞሪንዎ የዴቪድ ደ ሂያ ምትክ በማድረግ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ለማዛወር ሲሉ ከኤሲ ሚላኑ ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማ ጋር በየግዜው ንግግር ላይ መሆናቸውን የስፔኑ ህትመት Don Balon ዘገበ።
ዴቪድ ደ ሂያ በተደጋጋሚ ግዜ ኦልትራፎርድን በመልቀቅ ወደ ትውልድ ሃገሩ ክለብ ወደሆነው ሪያል ማድሪድ ከሰባት አመታት የዩናይትድ ቆይታው በኃላ በክረምቱ ቡድኑን መልቀቅ ይፈልጋል። በቅርቡ ደግሞ የፈረንሳዩ ክለብ ፒ.ኤስ.ጂዎች ደ ሂያን ለማዛወር ፉክክሩን ከማድሪድ ቀድመውት እየመሩት መሆኑ ሲዘገብ ስፔናዊው ግብ ጠባቂ የ€70 million ሂሳብ ቀርቦለታል ተብሏል።
ስለሆነም ጆዜ ሞሪንዎ ደ ሂያን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ላይ እንደሚያጡት ስለተሰማቸው ክለቡ የኤሲ ሚላኑን ዶናሩማ በማዛወር የስፔናዊው ቁ1 ተተኪ እንዲሆንላቸው ይፈልጋሉ።
OTHER SHORT STORIES
ዌስትሃም ዩናይትዶች ክለባቸው በፕሪሚየር ሊጉ ደካማ ውጤት ማስመዝገቡን ተከትሎ አሰልጣኙን ስላቨን ብሊች አባረዋል። በምትኩ የቀድሞው የምልን.ዩናይትድ እና ኤቨርተን አሰልጣኝ የነበሩት ዴቪድ ሞዬስ ክለቡን እንደሚይዙት ይጠበቃል።
(Source: @JimWhite)
ፋቤጋስ ማን.ዩናይትድን ካሸነፉ በኃላ: "በዛሬው ጨዋታ ኳስ በብዛት ተቆጣጥረናል። የጎል ማግባት እድሎችን ፈጥረናል እንዲሁም ጥሩ ተከላክለናል። እንደ ትልቅ ቡድን ነው የተጫወትነው። በዛሬው ፐርፎርማንሳችን ልንኮራ ይገባል። ሊያልቅ አካባቢ ትንሽ ከብዶን ነበር። ምናልባት አብዝተን ተከላክለናል። ሆኖም በኳስ ቁጥጥር እንበልጥ ነበር ይሄ ደሞ ያጣነውና የጎደለን ነገር ነበር። መከላከል ምርጥ ቢሆንም ጥሩ እግር ኳስ መጫወትም አለብን" [ለSky sports]
ጆዜ ሞሪንዎ ከቼልሲው ሽንፈት በኃላ: “ትልልቅ የሆኑ ከባባድ ጭ9ዋታዎችን አድርገን መጥተናል። ቶተንሃም፣ ሊቨርፑል እና ቼልሲ ያደረግናቸው ጨዋታዎች ያለ ወሳኝ ልጆቻችን ነው።“
ጆዜ ሞሪንዎ አንቶኒዮ ኮንቴን ስላለመጨበጣቸው: "ጨዋታው እንዳለቀ ወዲያውኑ ከሜዳው ተሰወረ። ሆኖም የምክትሉን እጅ ጨብጫለሁ። በመሰረቱ እሱንም ጨበጥኩ ምክትሉ አንድ ነው ለውጥ የለውም"
(አዘጋጅና አርታኢ መንግስቱ ደሳለኝ)
ፀሐፊ - ሙሴ አማረ
No comments:
Post a Comment
አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦