Saturday, May 12, 2018

ቅዳሜ የወጡ የዝውውር ዜናዎችና መረጃዎችን ያንብቡ - Latest Transfer News Update


═════════════════════════
📂  ሞሪንዎ ክላይቨርትን ይፈልጉታል
═════════════════════════


እንደ the guardian ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ጆዜ ሞሪንዎ የአያክሱን ታዳጊ ጀስቲን ክላይቨርትን ማዛወር ይፈልጋሉ።

የ19 አመቱ ተጭዋች በመጀመሪያው የኤርዲቪዜ የውድድር አመቱ ላይ ድንቅ ብቃቱን ማሳየቱን ተከትሎ በበርካታ የአውሮፓ ትላልቅ ክለቦች አይን ውስጥ መግባት ችሏል።

ጆዜ ሞሪንዎ እንደሚያምኑት ከሆነ ዩናይትዶች ተጨዋቹን ከሆላንዱ ክለብ ለመንጠቅ ጥሩ ስቴፕ እንደሄዱ እና ክረምት ላይ ሂሳብ አቅርበው እንደሚወስዱት ያምናሉ።


═════════════════════════
📂  ዲሲ ዩናይትዶች ሮኒን የማዛወር ፍላጎት እንዳላቸው አረጋገጡ
═════════════════════════


የዲሲ ዩናይትዱ አለቃ ቤን ሆልሰን እንደተናገሩት ከሆነ ዋይኒ ሩኒን የማዛወር ፍላጎት አላቸው።

እንግሊዛዊው ኢንተርናሽናል ወደ አደገበት ክለብ ኤቨርተን ከተመለሰ በኃላ ከዲሲ ክለብ ሰዎች ጋር ድርድር ላይ ቢሆንም እንደ ኦልሰን ገለፃ ከሆነ ግን ድርድሩ እስካሁን አልተጠናቀቀም።

"ድርድሩ አሁን ላይ አልተጠናቀቀም"  ሲሉ ኦልሰን ለTMZ ተናግረዋል።


═════════════════════════
📂  ቼልሲዎች ካንቴን በአሴንሶ ሊቀይሩት ነው
═════════════════════════


እንደ ስፔኑ ተነባቢ Don Ballon ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ቼልሲዎች የሪያል ማድሪዱን ማርኮ አሴንሶን ለማስፈረም ሲሉ ንጎሎ ካንቴንም ሳይቀር ለመስጠት ዝግጁ ናቸው።

ስፔናዊው ተጭዋች የሮማን አቭራሞቪች የክረምቱ ዝውውር ዋነኛ ኢላማቸው ሲሆን እርሱን ለማዛወር ሲሉ ኮከብ ተጭዋቻቸውን ለመስጠትም ፍቃደኛ ናቸው።

ሪያል ማድሪዶች ሙሉ ትኩረታቸውን ከኤዲን ሃዛርድ ዝውውር ወደ ኔይማር ማዞራቸውን ተከትሎ ቼልሲዎች በበኩላቸው ካንቴን መስዋት ለማድረግ ተሰናድተዋል።


═════════════════════════
📂  ጋሬዝማን ከአትሌቲኮዎች ጋር ወሳኝ ንግግር አድርጓል
═════════════════════════


እንደ Mundo Deportivo ዘገባ ከሆነ አንቶኔ ጋሬዝንማ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ባለስልጣናት ጋር በወደፊት የክለቡ ቆይታው ዙሪያ ንግግር አድርጓል።

ምንም እንኳን በቅርቡ ተጨዋቹ ወደ ባርሴሎና መዛወር እንደሚፈልግ ፍንፅ ቢሰጥም አሁን ግን በክለቡ ሊቆይ እንደሚችል አመላካች ነገር ማሳየት ጀምሮአል።

ባለፈው አርብ ለት የሱ የህግ ሰዎች ከማድሪዶች ጋር ተገናኝተው ዝውውሩ ቢጠናቀቅ ምን አይነት ህጋዊ ተፅህኖዎችን ሊያመጣ እንደሚችል ተነጋግረዋል።

═════════════════════════
📂  ማን.ዩናይትዶች ጀርጊንዎ ላይ የነበራቸውን ፍላጎት አንስተዋል
═════════════════════════


እንደ ማንቸስተር ኢቭኒንግ ዘገባ ከሆነ ማን.ዩናይትዶች በናፖሊው አማካይ ጀርጊንዎ ላይ ያላቸውን ፍላጎት ትተውታል።

የዩናይትዶች ከጣሊያናዊው የ26 አመት አማካይ  ዝውውር ፉክክር ራሳቸውን ማግለላቸው ለጎረቤቶቻቸው የቅርብ ተቀናቃኞች ማን.ሲቲዎች ልጁን እንዲያስፈርሙት የተሻለ እድል የሚፈጥር ይሆናል።

የዩናይትድ ሰዎች በእርሱ ፋንታ ሚሊንኮቪች ሳቪች፣ አርቱሮ ቪዳል፣ ጂያን ሚኬል ሴሪ፣ ፍሬድ እና ማርኮ ቬራቲን ጉዳይ እየተከታተሉ ይገኛሉ።


═════════════════════════
📂  ጆዜ ሞሪንዎ የዩናይትድ ደሞዝ ጣሪያን ቢልን ሊቀንሱ ነው
═════════════════════════


እንደ ሚረር ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ የዩናይትዱ አለቃ ጆዜ ሞሪንዎ የቡድኑን ከፍተኛ የደሞዝ ጣሪያ ድምር መጠን በመቀነስ ለዝውውር የሚሆናቸውን የ150ሚ.ፓ ወይም የ203ሚ.ዶ ሂሳብ ለማትረፍ አስበዋል።

ይሄ ማለት እንደ ማቲዩ ዳርሜይን፣ ዴይሊ ብላይንድ እና ሉክ ሾው የመሳሰሉ ተጭዋቾች ክለቡን የመልቀቅ እድላቸው ሰፊ ነው።
═════════════════════════
ADVERTISEMENT


═════════════════════════
ሌሎች አጫጭር ወሬዎች ...
═════════════════════════


📂  የማንችስተር ዩናይትዱ የፊት አጥቂ ሮሜሉ ሉካኩ በሚቀጥለው ሳምንት ከቼልሲ ለሚደረገው የኤፍ, ኤ ካፕ ፍፃሜ ወደ ጨዋታ እንደሚመለስ ተማምኖዋል።   (ሜይል)


📂  አዲሱ የሊቨርፑል ወዱ ፈራሚ ቨርጂል ቫንዳይክ በውሉ ላይ አንድ ይፋ ያልወጣ አንቀፅ እንዳለበት በመረጃ አፈትላኪው (ፉትቦል ሊክስ) በኩል ተጠቅሷል፣ አንቀፁም እንደሚለው ተከላካዩ ለ22 ጨዋታዎች ያክል ጎሉን ካላስደፈረ £750,000 ሺህ ጉርሻ እንደሚያገኝ የሰፈረ ሲሆን፣ ጎል ባገባ ቁጥር ደግሞ ተጨማሪ £20,000 እንደሚሰጠው በውሉ ላይ ሰፍሯል።   (ሜይል)


📂  በኦልትራፎርድ ስታዲዮም ውስጥ በህክምና ላይ ያሉትን ሰር አሌክስ ፈርጉሰንን ለማሰብ አዲስ ባነር ተዘጋጅቷል፣ «እያንዳንዳችን አሌክስ ፈርጉሰንን እንወዳለን» የሚል ነው።   (ሜይል)


📂  የአርሰናሉ አጥቂ ኦቦሚያንግ ከዶርትመንድ ሲመጣ በነበረው ሂደትና፣ በውሉ ዙሪያ ያልተሰሙ አዳዲስ መረጃዎች እየወጡ ሲሆን፣ ለዚህም ደግሞ አፈትላኪ መረጃዎችን በማውጣት ቀዳሚ የሆነው ፉትቦል ሊክስ ነው፣ አሁን በለቀቀው መረጃም አርሰናል ለዝውውሩ ለተጫዋቹ £18.2 ሚሊዮን  የከፈሉ ሲሆን፣ አስከ 2021 የሚያቆየውን ውል በታማኝነት ከጨረሰ ደግሞ £15.15 ሚልዮን ሎያሊቲ ይከፈለዋል፣ ሌላው የኦቦሚያንግ ጉርሻ ደግሞ፣ የመጀመሪያ ተሰላፊ በሆነበት ጨዋታ አርሰናል ካሸነፈ በየጨዋታው £50 ሺህ እንደሚሰጠው የታወቀ ሲሆን በእስካሂኑ ሂደትም £250 ሺህ ያክል እንዳገኘም ተዘግቧል።  (ሜይል፣ጋርዲያን)


📂  ቼልሲ የ2018/19 አዲሱን የመጀመሪያውን ማሊያ ያስተዋወቀ ሲሆን ሆኖም በደጋፊዎቹ ዘንድ የተጠበቀውን ተቀባይነትን እንዳላገኘ እየተነገረ ነው።  (ደይሊ ስታር)


📂  የቀድሞው የባርሴሎናና ጁቬንቱስ ፉልባክ ዳኒ አልቬዝ በሳምንቱ አጋማሽ በተደረገው የፈረንሳይ ዋንጫ ላይ ከፍተኛ ጉዳትን ያሰተናገደ ሲሆን፣ እንደተፈራውም የጉዳቱ መጠን ከአለም ዋንጫው እንዳገለለው የታወቀው ትላንት ምሽት ነበር።(ማሪካ


📂  አንቶኒዮ ኮንቴ የሱ ቼልሲ ከሞውሪንሆው ቼልሲ የተሻለ እንደሆነ አስረግጦ ተናግሯል ። (ጋርዲያን)


📂  ማንችስተር ዩናይትድ ጀርጊንሆ ላይ የነበረው ፍላጎት በመቀዛቀዙ ፣ ማንችስተር ሲቲ የናፖሊውን አማካኝ ለማግኘት የተሻለ ወቅት ላይ እንደሚገኝ ታውቋል። (ማንችስተር ኢቭኒንግ)


📂  የአርሰናሉ የመሰመር ተጫዋች ሄክቶር ቤለሪን፣ በሚቀጥለው የውድድር ዘመንም በአርሰናል መቆየት እንደሚፈልግ ተናግሯል ። (ስካይ ስፖርት)


📂  የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ፣ወደ ማድሪድ የመሄድ ፍላጎት አለው እየተባለ የሚታማው ብራዚላዊው ኔይማር እና ሮናልዶ በአንድ ቡድን ውስጥ መጫወት እንደሚችሉ ተናግሯል።  (ማርካ)


📂  ሊቨርፑልና አርሰናል €65 ሚሊዮን ያወጣል የተባለውን የናፖሊ አማካኝ ፔግሮ ዜሌንስኪ  ለማግኘት በፉክክር ላይ ናቸው። (ኮሬሮ ዴሎ ስፖርት)


📂  የአርሰናል አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር በመጨረሻው የጨዋታ በፊት ቃለ ምልልሳቸው ፣ አርሰናል ወደ ኤምሬትስ ከተዘዋወረ ቡሃላ በሃይበሪ የነበረውን የተለየ መንፈስ እንዳጡት አምነዋል። (ሚረር)

═════════════════════════
ADVERTISEMENT

No comments:

Post a Comment

አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦

Featured Post/ቀጣይ ልጥፍ

የዝውውር ዜናዎች

  ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር...