▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
● የርገን ክሎፕ የ70ሚ.ዩ የዝውውር ግምት የተሰጠውን ፌከር አግኝተውታል
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
እንደ Canal Plus ዘገባ ከሆነ የሊቨርፑሉ አለቃ የርገን ክሎፕ በ70ሚ.ዩ ወይም በ80ሚ.ዶ የዝውውር ሂሳብ ግምት የተሰጠውን የሊዮን ኮከብ ናቢ ፊከር አግኝተው በዝውውሩ ዙሪያ አነጋግረውታል።
እንደ ዘገባው ከሆነ የፈረንሳዊው ኢንተርናሽናል የ24 አመት ኮከብ አንፊልድ ዝውውር ከመጠናቀቅ ምንም እንሰማያደናቅፈው የተነገረ ሲሆን በ2018-19 የውድድር አመት ላይ ይዛወራል።
ቼልሲዎችም ተጨዋቹን የማዛወር ፍላጎት የነበራቸው ቢሆንም እርሱ ግን ከሰማያዊዎቹ ይልቅ ቀዮቹን መርጧል።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
● ማን.ዩናይትዶች ለፑሊሲች ዝውውር ማርሻል እና ገንዘብ ሊያቀርቡ ነው
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ማንቸስተር ዩናይትዶች አሜሪካዊውን አማካይ ክርስቲያን ፑሊሲች ለማዛወር ሲሉ አንቶኒዮ ማርሻል እና ተጨማሪ ጥሬ ገንዘብ ለክለቡ ቦሩሲያ ዶርትመንዶች ሊሰጡአቸው አቅደዋል።
እንደ mirror ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ የ22 አመቱ ፈረንሳዊ ኢንተርናሽናል አጥቂ በኦልትራፎርድ ተመራጭ መሆን እያቃተው ሲሆን በጆዜ ሞሪንዎ በክረምቱ ሊለቀቅ ተወስኖበታል።
በዚህ ሳቢያ ፈረንሳዊው ተጭዋች በጀርመኑ ቡንደስሊጋ ላይ ምርጥ ብቃቱን እያሳየ ባለው እና ከእርሱ በ3ት አመታት እድሜ በሚያንሰው የክንፍ ተጭዋች ዝውውር አካል ሊደረግ ይችላል።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
● አትሌቲኮ ማድሪዶች ከካቫኒ ጋር ከሞላ ጎደል ተስማምተዋል
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
እንደ Mundo Deportivo ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ አትሌቲኮ ማድሪዶች የPSGውን አጥቂ ኤድሰን ካቫኒን ለማዛወር ቅድመ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የቡድኑ አለቃ ዲያጎ ሲሞኔ በመጨረሻም አንቶኔ ጋሬዝማን ከሲዝኑ መጠናቀቅ በኃላ ክለቡን እንደሚለቅ ያመነ ሲሆን ከወዲሁ ትልቅ ስም ባለው ተጫዋች ሊተካው አቅዷል።
ኡራጉዋዊው ኢንተርናሽናል ከኔይማር ጋር ስምምነት ስላሌለው የፓሪሱን ክለብ መልቀቅ የሚፈልግ ሲሆን ዲያጎ ጎዲን እና ጆዜ ጊሚኔዝ ደግሞ ወደ አትሌቲኮ እንዲመጣ አሳምነውታል።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
● ኤቨርተኖች ሳም አላርዳይስን አርሰን ዌንገር እንዲተኳቸው ይፈልጋሉ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
እንደ dailystar ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ኤቨርተኞች የክለባቸውን አለቃ ሳም አላርዳይስን በማሰናበት አርሰን ዌንገር ቦታቸውን እንዲተኩላቸው ይፈልጋሉ።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
● ብራይተር፦ ኔይማር በቀጣዩ አመት ለሪያል ማድሪድ ወሳኝ ተጭዋች ይሆናል
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
እንደ እውቁ ጀርመናዊ ፓል ብራይተር እምነት ከሆነ የኔይማር የሪያል ማድሪድ የክረምቱ ዝውውር የማይቀር ሲሆን የPSGው ብራዚላዊ ኮከብ በቀጣይ አመት የማድሪዶች ቁልፉ ሰው ይሆናል የሚል ግምታቸውን ተናግረዋል።
በሪያል ማድሪድ ቆይታቸው ወቅት የላ ሊ ጋውን ዋንጫ ከክለቡ ጋር ማንሳት የቻሉት ብራይተር ለጀርመን Sport 1 ቴሌቭዥን ጣቢያ በሰጡት ቃለ መጠይቅ መሰረት "እመኑኝ ኔይማር በበርናባው ወሳኝ ይሆናል" ብለዋል።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
● ሄክተር ቤለሪን ወደ ባርሴሎና
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ሄክቶር ቤለሪን ስሙ በተደጋጋሚ ግዜ ከጁቬንቱስ እና ባርሴሎና ዝውውር ጋር ተያይዞ መነሳቱን ተከትሎ ሲጠየቅ በክለቡ አርሰናል ፍፁም ደስተኛ መሆኑን እና ስለነዚህ ወሬዎች ቦታ እንደሌለው በመግለፅ አስተባብሎአቸዋል።
ከ2015 ጀምሮ ከመድፈኞቹ አካዳሚ በቅሎ ድንቅ ብቃቱን ያሳየው ስፔናዊ ተመላላሽ ተከላካይ ለረጅም ጊዜያት ያህል ወደ አሳዳጊው የካታሎን ክለብ ሊመለስ ይችላል ሲባል ከቆየ በኃላ በቅርብ ግዜ ደግሞ ስሙ ከጁቬንቱሶች ዝውውር ጋር ተያይዞ መወራቱ የሚታወስ ነው።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
● አንቸሎቲ የአርሰናሎች ቁ2 ተመራጭ ናቸው
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አርሰናሎች አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር እያደረጉ ባሉት ጥረት ላይ ማሲሞ አሌግሪን የማያዛውሩ ከሆነ በምትካቸው ካርሎ አንቸሎቲን ለማምጣት እንደሚሰሩ dailystar ዘግቧል።
መድፈኞቹ የጁቮንቱሱን አለቃ እንደ ሁነኛ ቁ1 የአርሰን ዌንገር ምትክ አድርገው የሚያዩአቸው ቢሆንም ካልተሳካ ግን አንቸሎቲን እንደ አጭር ግዜ መፍትሄ ተቆጥረው ያዛውሩአቸዋል።
ተሳክቶላቸው አንቸሎቲን ወደ ኤምሬትስ የሚያዛውሩ ከሆነ ከፓትሪክ ቪየራ፣ ሚካኤል አርቴታ እና ዜሊኮ ቡቫች አንዳቸውን ምክትል አሰልጣኝ በማድረግ በሂደት ቡድኑን ሙሉ ለሙሉ እንዲረከቡ የማድረግ እቅድ አላቸው።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
● ሃዛርድ ለቼልሲዎች ተስፋ ሰጥቷቸዋል
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ኤዲን ሃዛርድ በለንደን ህይወቱ ፍፁም ደስተኛ መሆኑን በመግለፅ እና የቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ማግኘት ማጣት በወደፊት ቆይታው ላይ ተፅህኖ እንደማይፈጥርበት በመናገር ለቼልሲ ሰዎች ተስፋ ሰጥቷል።
ቤልጂየማዊው የ27 አመት ኮከብ ተጫዋች ስሙ በተደጋጋሚ ግዜ ከስፔኑ ሃያል ክለብ ሪያል ማድሪድ እና ከሊግ ዋኑ ሻምፒየኖች ፒኤስጂ ጋር ተያይዞ ሲወራ መቆየቱ ክለቡን ስጋት ላይ ጥሎት ቆይቷል።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ADVERTISEMENT


No comments:
Post a Comment
አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦