Saturday, December 2, 2017

እሁድ ከሰአት በኃላ ላይ የተሰሙ በርካታ አጫጭር እና ሠፋ ያሉ የዝውውር ጭምጭምታዎች፣ ዜናዎች፣ አስተያየቶች እና ሌሎችም ትኩስ ትኩስ የእግር ኳስ መረጃዎችን ያንብቡ



CHELSEA WANT AUBAMEYANG



የቼልሲዎች አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ በቦሩሲያ ዶርትመንዱ አጥቂ ፒር ኢምሬክ ኦበምያንግን ለማዛወር ከሊቨርፑል ጋር ለማዛወር ፉክክር ላይ ናቸው ሲል Sunday Express ዘግቧል።

ከጀርመን የወጡ ሪፖርቶች እንዳሉት ከሆነ
BVBዎች አጥቂውን ለመሸጥ ዝግጁ ሲሆኑ በዚህ የውድድር አመት ላይ ተጭዋቹ በጥሩ ብቃት ላይ ይገኛል።

ምንም እንኳን የርገን ክሎፕ ከዚህ በፊት ያሰለጠነው ጋቦናዊው አጥቂ ጋር አብሮ መስራት ቢፈልግም በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ እሱን ለማዛወር ከቼልሲ ጋር መፎካከር አለባቸው ተብሏል።


NEYMAR HAS REAL MADRID DEAL



ኔይማር ከሪያል ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ጋር በ2019 የዝውውር መስኮት ወደ ክለቡ ለመዛወር ከወዲሁ ቅድመ ስምምነት ማድረጉን የስፔኑ ጋዜጣ Don Balon ዘገበ።

ብራዚላዊው ባርሴሎናን በክረምቱ በመልቀቅ በአለም ሪከርድ የዝውውር ሂሳብ €222 million ወደ ፒ.ኤስ.ጂዎች ማምራቱ የሚታወቅ ቢሆንም ከወዲሁ ወደ ስፔን ለመመለስ እያቀደ ነው።


SANDRO OPENS CHELSEA DOOR



አሌክስ ሳንድሮ አሁንም ከ2018ቱ የአለም ዋንጫ በኃላ ወደ ቼልሲ የመዛወር ፍላጎት እንዳለው በመግለፅ ለቼልሲዎች ተስፋ ሰጥቶአል ሲል የጣሊያኑ TMW ዘግቧል።

ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ተመላላሽ ተከላካይ በባለፈው ክረምት ላይ ወደ ሰማያዊዎቹ ይዛወራል በሚል ሲወራበት ቢቆይም ከሩሲያው የአለም ዋንጫ በኃላ ግን ወደ ለንደን መምጣቱ የማይቀር እንደሆነ ዘገባው አትቷል።

ቀያይ ሰይጣኖቹ ማንችስተር ዩናይትዶች የቶተንሃሙን የግራ መስመር ተጫዋች የሆነዉን ዳኒ ሮዜን በ45 million  ለማስፈረም የጥር ወር የዝውውር መስኮትን እየተጠባበቁ ነዉ። የ27 አመቱ እንግሊዛዊዉ ተከላካይ ሮዝ በክለቡ ቶተንሃም ባለዉ ሁኔታ ደስተኛ አይደለም ሲል (Daily Star Sunday) ዘግቧል።


በአይቴል ሞባይል ኢትዮጵያ ስፖንሰር የተደረገ
ፅድት ጥርት ያሉ ምስሎች የአይቴል S11 እና S31 ስልኮች መለያዎች ናቸው



ሊቨርፑል ተዘጋጅተዋል ዳኒኤል ስቶሪጅን በመሸጥ በምትኩ የቦርሲያ ዶርትመንዱን አጥቂ ጋቦናዊዉን ፒኤሬ ኤምሪክ ኦባሜያንግ መግዛት። ከዚህ በፊት በዶርትመንድ ቤት ከአሰልጣኝ ጀርገን ክሎፕ ጋር አብረዉ መስራታቸዉ ይታወሳል። ተጫዋቹ ዳግመኛ በክሎፕ ስር ለመሰልጠን ወደ አንፊልድ ሊመጣ ይችላል ተብሎል። (Sunday Express)


አዲሱ የኤቨርተን አሰልጣኝ ሳማላርዳይስ የጥር የዝውውር መስኮት ላይ የሲቪያዉን አማካኝ ሲቴቬን ኒዞንዚን በ25 million ለማስፈረም እቅዳቸዉ ዉስጥ አካተዉታል ተባለ። (Mail on Sunday)


ማንችስተር ዩናይትድ የሪያል ማድሪዱን ዌልሳዊዉን አጥቂ ጋሬዝ ቤልን ለማስፈረም የዝውውሩን ሂሳቡን ዝቅ አድርገዉታል። ዩናይትዶች 100 million የነበረዉን ሂሳቡን ዝቅ ያደረጉበት ምክንያት ደግሞ እድሜዉ መግፋቱን ተከትሎ ቤል ለብዙ ጊዜ ሊያገለግላቸዉ ስለማይችል ነዉ ተብሎል። ማንችስተር ዩናይትድ 28 አመት ላይ የሚገኘዉን ቤልን በ£50m ወይንም በ£60m ሊያስፈርሙት ይችላሉ ሲል፣ (Sunday Mirror) አስነብቧል።


ማንችስተር ሲቲ የዌስትብሮሚች አሌቤኑን ተከላካይ የሆነዉ ጆንስ ኢቫንስን በጥር ለማስፈረም ቢጥሩም የሚሳካላቸዉ አይመስልም በዚህም ተጫዋቹን በክረምት ለማስፈረም ማሰባቸዉ ተነገረ። (Sunday Express)


ሪያል ማድሪድ የሊቨርፑሉን ኮከብ ግብፃዊዉን መሀመድ ሳላህን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳለዉ ታወቀ። (ON Sport TV - Egypt, via Evening Standard)

No comments:

Post a Comment

አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦

Featured Post/ቀጣይ ልጥፍ

የዝውውር ዜናዎች

  ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር...