⃣ MOU TO LEAVE MAN UTD FOR PSG
ማንቸስተር ዩናይትዶች በክረምቱ ጆዜ ሞሪንዎ ክለቡን በመልቀቅ ወደ ፈረንሳዩ ሃብታም ክለብ ፒኤስጂ እንደሚያመሩ እርግጠኞች ሆነዋል ሲል The Sun ዘገበ።
ምንም እንኳን የፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ወገን ሰዎች የሞሪንዎን የፓሪስ ዝውውር ወሬዎች ቢያጣጥሉአቸውም የክለቡ ሰዎች ግን ሰውዬው የፔፕ ጋርዲዮላውን ቡድን በዝውውርም ሆነ በቡድን ግንባታ በልጦ የመፎካከር አቅም እንደሌለው ስለተረዳ የቀድሞው የቼልሲ እና ሪያል ማድሪድ አለቃ ክለቡን በመልቀቅ ሊሄድ እንደሆነ ስጋት አድሮባቸዋል።
ከሦስተኛው አዲሱ ክለቡ ጋር እንዲሁ የቻምፒየንስ ሊጉን ዋንጫ የማሸነፍ እድል እንደሌለው ያስባል። ይሄንን ህልሙን ከበቂ የዝውውር ባጀት ጋር ሊያቀርብለት የሚችለው እና ቻምፒየንስ ሊጉን ሊያሸንፍ የሚረዳው ቡድን የፈረንሳዩ ሃብታም ክለብ ብቻ እንደሆነም ያምናል።
⃣ Sponsored By ዜናዎቹን ስፖንሰር ያደረገላችሁ ..
⃣ MAN UTD TRACKING ARTHUR
ማንቸስተር ዩናይትዶች የግሬሚዮውን አማካይ አርቱር ሜሎ ለማስፈረም እየተከታተሉት ይገኛሉ ሲል Daily Mail ዘገበ።
የ21 አመቱ ብራዚላዊ በዚህ አመት ምርጥ ብቃቱን እያሳየ ያለ ሲሆን በኦክቶበር ወር ላይ ብሄራዊ ቡድኑ ለሚያደርገው የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ ቡድኑን እንዲቀላቀል ጥሪ ተደርጎለታል።
ያም ሆኖ ማንቸስተር ዩናይትዶች ተጭዋቹን ለማስፈረም ገፍተው የሚሄዱ ከሆነ ከቼልሲ፣ ባርሴሎና እና አትሌቲኮ ማድሪድ ፉክክር ይጠብቃቸዋል ተብሏል።
⃣ MAN UTD MONITORING BARCA'S UMTITI
ጆዜ ሞሪንዎ የተዳከመውን የተከላካይ ክፍል ለማደስ ሲሉ በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ የባርሴሎናውን ተከላካይ ሳሙኤል ኡምቲትን እየተከታተሉት ነው ብሏል Mirror ጋዜጣ።
ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ የቡድኑን የተከላካይ መስመር ለማጠናከር ጠንካራ ፍላጎት ያላቸው ሲሆን ምንም እንኳን ኤሪክ ቤይሊን ለማጣመር በሚል በክረምቱ የ£30 million ሂሳብ በማውጣት ከቤኔፊካ ያዛወሩት ተከላካይ ቪክተር ሊንደሎፍ ሊጉን መልመድ ተድኖት ከዋናው ቡድን ውጪ እስከመደረግ ደርሷል።
⃣ ZIDANE MAKES HAZARD NO.1 TARGET
የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ዚነዲኔ ዚዳን የቸልሲዉን ጨዋታ ቀማሪ ኤደን ሀዛርድን በቀጣዩ ክረምት የማስፈረም ተቀዳሚ አማራጭ አድርገዉታል ተብሎል።
ብዙም ታማኝነት የሌለዉ የስፔኑ ጋዜጣ ዶን ባሎን የማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ በምርጥ ተጫዋቾች ላይ አይናቸዉን ማሳረፋቸዉ ተከትሎ
አሁን ደግሞ ወደ ቼልሲዉ ኮከብ ኤደን ሀዛርድ ላይ ፊታቸዉን አዙረዋል።
ዚዳንም የአጥቂዉ ክፍላቸዉ መዳከሙን ተከትሎ የአጥቂያቸዉን ቦታ ተጫዋቾች ተተኪ ከአሁኑ ለማስፈረም ስራቸዉን ጀምረዋል።
ዛዳንም ከዚህ ቀደም የቶተንሃሙን አጥቂ ሄሪ ኬንን የኮከባቸዉ ክርስቲያኖ ተተኪ ለማድረግ እንቅስቃሴ ላይ ነዉ። በተጨማሪም ደግሞ የጁቬንትሱን ኮከብ
አርጀንቲናዊዉ ፖዉሎ ዲባላን የጋሬዝ ቤል ተተኪ በማድረግ ወደ በርናባዉ መዉስድ ይፈልጋሉ።
ሁኖም ግን አሁንም በዚህ ሳያበቃ ቤልጄማዊዉ ኮከብ ኤደን ሀዛርድን የካሬም ቤንዜማ ተተኪ እንዲሆንላቸዉ በማሰብ እናስፈርምህ ሊሉት ከተጫዋቹ ጋር ንግግር ሊያደርጉ ነዉ ተብሎል።
ማድሪድ ኮከቦቹን ወደ ስፔን ለመዉስድ ከአሁኑ በቅርበት ሁነዉ እንቅስቃሴወቻቸዉን በጥንቃቄ ይተከታተሉ ነዉ ሲል Don Balon ዘግቧታል።
⃣ BARCA & MADRID TARGET TO COST AT LEAST €30M
የላሊጋዉ ክለቦች ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ የፊላሚኒጎዉን ወጣት ተጫዋች ላይ አነጣጥረዋል፣ ሁኖም ተጫዋቹን ሊንኮልን በ€30 million ለማስፈረም ተፋጠዋል።
ማርካ እንዳለዉ ከሆነ በህንድ አስተናጋጅነት የተካሄደዉ ከ17 የአለም ዋንጫ ላይ ተሰልፎ ለሀገሩ ብራዚል ጥሩ ብቃቱን ያሳየዉ ሊንኮልን በፊት ከሪያል ማድሪድ ጋር በ€45 million ስምምነት ሊያደርግ ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም ሳይፈርም ቀርቶል። ሁኖም የክለብ ጎደኛዉን ቪኒኪዩስ ጁኔርን ተከትሎ በአሁን ባለበት ክለብ ፍላሚንጎ ቀርቶል።
ከአሁኑ በሁለት ትልልቅ ክለቦች የእናስፈርም ጥያቄ ለልጁ ጥሩ እድል ነዉ ተብሎል ምክንያቱም ከወዲሁ በወጣትነቱ እዉቅናን ያተርፋል ተብሎል። (Marca)
⃣ MOYES TO ADD TWO TO FOUR IN JANUARY
ከሁለት ቀን በፊት የለንደኑን ክለብ ዌስታሃም ዩናይትድን የተረከቡት አሰልጣኝ ዳቪድ ሞይስ በጥር ሁለት እና አራት ተጫዋቾች ማስፈረም እንደሚፈልግ
ተናግሮል።
ጋዜጣዉ ኢቪኒግ እስታንዳርድ እንዳለዉ ከሆነ ሞይስ የክለቡን ጥልቀት ለማስፋት ሲል የግድ ተጫዋቾችን ማስፈረም አለበት ተብሎል። ሁኖም ዳቪድ ሞይስ ተጫዋቾቹ የሚያስፈረም ደግሞ ከቀድሞ ክለቦቹ ከሆኑት ማንችስተር ዩናይትድ እና ኤቨርተን ነዉ። ሞይስ ከቀድሞ ሁለቱ ክለቦቹ በዛ ያሉ ተጫዋቾችን በጃቸዉ ማስገባት እንደሚፈልጉ ጋዜጣዉ Evening standard ጨምሮ ዘግቧል።
⃣ MAN CITY PREP MILINKOVIC-SAVIC BID
ማንችስተር ሲቲ የላዚወን አማካኝ ሚሊንኮቪች ሳቪክን በጥር ለማስፈረም ተዘጋጅተዋል።
ሰርቢያዊዉ አማካኝ ሳቪክ በሌሎች ክለቦችም ይፈለጋል። ከክለቦቹ መካከል፦ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ጁቬንትስ እና ሪያል ማድሪድ ይገኙበታል።
ማንችስተር ሲቲ ተጫዋቹን በፈረንጆች አዲስ አመት በጥር ወር ላይ ለማስፈረም ከአሁኑ ከክለቡ ጋር ንግግር ጀምረዋል ተብሎል። (Source፦ Sky sport)
⃣ JACK WILSHER WANTED TO STAY
"ባሁን ሰአት ትኩረት ያደረኩት አሁን ባለኝ ቀሪ ኮንትራት ላይ ብቻ ነው። የወደፊቱ በራሱ ግዜ ይስተካከላል። ማድረግ ያለብኝ ከጉዳት ነፃ መሆን ብቻ ነው። በአርሰናል መቆየት እፈልጋለሁ። ይሄንን ለብዙ ጊዜያቶች ያህል ተናግሬዋለው። ወደ ሙሉ የአካል ብቃት ጥንካሬዬ የመጣሁት ገና አሁን ነው። አሁን ባለሁበት ክለብ እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ። በብልሃት እየተጫወትኩ ነው ያለሁት። ወደ ዋናው ቡድን ቋሚ ተሰላፊ ለመሆን እየሞከርኩ ነው በፕሪሚየር ሊጉሽተሰልፌ መጫወት እፈልጋለሁ።" - ጃክ ዊልሸር ስለ አርሰናል ቆይታው።
⃣ OTHER SHORT TRANSFER NEWS
ሪያል ማድሪዶች የቶተንሃሙን አጥቂ ሃሪ ኬን በማስፈረም የካሪም ቤንዜማ ተቀዳሚ ተመራጭ ተተኪው ሊያደርጉት ይፈልጋሉ። (Source: Diario Gol)
አርሰናሎች ስሙ በተደጋጋሚ ግዜ ከማንቸስተር ዩናይትድ ዝውውር ጋር እየስተነሳ ያለውን ጀርመናዊ አማካይ በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ የሚለቁት ከሆነ ለዝውውሩ የ£30m ሂሳብ ይጠይቃሉ። (Source: Daily Star)
ፓሪሰን ዥርሜዮች የኤሲ ሚላኑን ታዳጊ ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማ ማስፈረም ይፈልጋሉ።
(Source: TuttoMercatoWeb)
አትሌቲኮ ማድሪዶች የክለባቸውን ኮከብ አንቶኔ ጋሬዝማንን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ላይ በ€100m የውል ማፍረሻው ሂሳብ ሊሸጡት ይችላሉ። (Source: AS)
No comments:
Post a Comment
አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦