Thursday, November 16, 2017

ሃሙስ አመሻሽ ላይ የወጡ በርካታ አጫጭር እና ሠፋ ያሉ የዝውውር ጭምጭምታዎች፣ ዜናዎች፣ አስተያየቶች እና ሌሎችም ትኩስ የእግር ኳስ መረጃዎች




MAN UTD IDENTIFY NO.1 JANUARY
TARGET


ማንቸስተር ዩናይትዶች የቫሌንሺያውን አማካይ ካርሎስ ሶለር የጥሩ የዝውውር መስኮት ቁ1 የዝውውር ኢላማቸው አድርገውታል ሲል The Independent ጋዜጣ ዘገበ።

ሶለር በባለፉት 12 ወራት ውስጥ በቫሌንሺያ ጥሩ ብቃቱን እያስመሰከረ ሲሆን ጆዜ ሞሪንዎ የ20 አመቱን አማካይ በማዛወር ደካማውን የቡድናቸው አማካይ ክፍል መጠገን ይፈልጋሉ።

ከስፔን 21 አመት በታች እየተጫወተ የሚገኘው ኮከብ በቫሌንሺያ የሚያቆየውን አዲስ ኮንትታት የተፈራረመው በባለፈው ሜይ ወር ላይ ሲሆን የውል ማፍረሻው ወደ €80 million, ሆኖ ቢቀመጥም ዩናይትዶች ይሄንን ዋጋ አውርደው በ £40m የዝውውር ሂሳብ ብቻ እንደሚያዛውሩት ተስፋ አድርገዋል። አስፈላጊ ከሆነም በውሰት እዛው የሚገኘውን ተጭዋቻቸው አንድሪያስ ፔሬራን የዝውውሩ አካል በማድረግ መስጠት ይፈልጋሉ።


ታላቅ ቅናሽ - በአዲስ አበባ (መገናኛ እና ሳሪስ) ፣ ሀዋሳ፣ አዳማ፣ ጂማ፣ ሽሬ፣ ደብረ ማርቆስ፣ መቀሌ፣ ሀረር፣ ጎንደር እና ደሴ ከተማ ነዋሪ ነዎት? እንግዲያውስ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናቶች አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ ብቻ  የአይቴል S11 እና S31 ስልኮችን በታላቅ ቅናሽ ይግዙ! እንዲሁም ሲገዙ ልዩ ስጦታዎች ከአይቴል ሞባይል እዚያው ይውሰዱ! ለበለጠ መረጃ የፌስቡክ ገፃችንን ይጎብኙ  ፦  www.facebook.com/itelMobileEthiopia/


MAN CITY BATTLE MAN UTD FOR GRIEZMANN


ማንቸስተር ሲቲዎች የአትሌቲኮ ማድሪዱን ኮከብ አንቶኔ ጋሬዝማንን ለማዛወር በሚደረገው ፉክክር ላይ የከተማቸውን ተቀናቃኝ ማን.ዩናይትዶች ለመፎካከር ዝግጁ ናቸው ያለው Sport's print edition ነው።

ዩናይትዶች ፈረንሳዊውን ኢንተርናሽናል ባለፈው ክረምት ላይ እንደሚያዛውሩት የሚጠበቅ የነበረ ቢሆንም የአትሌቲኮዎች የዝውውር እገዳ መነሳት ባለመቻሉ ግን ዝውውሩ እውን ሳይሆን ቀርቷል።

ሆኖም በተጭዋቹ ዝውውር ላይ አሁን ከማን.ሲቲዎች ጋር መፎካከር ያለባቸው ሲሆን የኢትሃዱ ክለብ አሁን ባለው የተሟላ ቡድን ላይ የ26 አመቱን የፊት አጥቂ በመጨመር ቡድኑን ይበልጥ ተፈሪ ማድረግ ይፈልጋሉ።



NEYMAR WANTED TO CANCEL PSG TRANSFER


ብራዚላዊዉ ኔይማር ጁኔር ያለማችን ሪከርድ ዋጋ በመስበር ወደ PSG ከመዘዋወሩ በፊት ዝውውሩ እንዳይሳካ የባርሴሎናን ክለብ ፕሬዝዳንት የሆኑት ማርዮ ባርቶሚዮን ሁሉ ጠይቁዋቸው ነበር ሲል ማርካ ዘግቡዋል።

ነገር ግን የተጫዋቹ ወኪል እና አባቱ የሆኑት ኔይማር ጁኔር በመጨረሻም ዝውውሩን እንዲሳካ አድርገውታል ተብሎል።

ሁኖም ግን ኔይማር አሁንም በፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ የመቆየቱ ነገር አጠራጣሪ ነዉ፣ ምክንያቱም ከካቪኒ ጋር በገባዉ ሰጣ ገባ እንደ ታዉቆል።  (marca)

ይገምቱ ይሸለሙ - የሳምንቱን የፕሪሚየር ሊጉ ታላቅ ጨዋታ ከታች ባለው ሊንክ ገብተው ይገምቱ እና ከአይቴ ሞባይል ኢትዮጵያ ባለ 100ብር ካርዶችን ይሸለሙ ፦  goo.gl/fpMJxP

BAYERN WANT GIROUD


የጀርመኑ ክለብ ባየርሙኒክ አይኑን ወደ አርሰናሉ አጥቂ ኦሊቨር ዤሩድ አዙሮል።

ባባሪያኖቹ የሮበርት ሌቫንዶቪስኪ ተጠባባቂ እንዲሆንላቸው በማሰብ ፈረንሳዩን አጥቂ ለማስፈረም አስቦል ተብሎል::

ዤሩድ በክለቡ ያለዉ ቦታ በሀገሩ ልጅ አሌክስ ሳንደር ላካዚት መያዙ አላስደሰተዉ በዚህም ክለቡ ሊለቅ
ይችላል ተብሎል።    (daily mirror)



BETIS LOOK TO SIGN WILSHERE


የስፔን ላሊጋው ክለብ ሬያል ቤቲስ በአርሰናል ቤት ያልተረጋጋውን እንግሊዛዊዉ አማካይ ጃክ ዊልሻየርን
እንደሚያዘዋውሩት ተስፍ አድርገዋልተብሎል።

ዊልሸር በሳምንት £90,000  ሳምንታዊ ደሞዝ እየከፈሉት ሪያል ቤትስን ሊቀላቀል ይችላል ሲል፣ (marca) ዘግቧል።



ARSENAL WILL SWAP ALEXIS FOR STERLING


የፕሪሜር ሊጉ ክለቦች አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ ተጫዋቾችን ሊለዋወጡ ነዉ ተባለ።

በአርሰናል ቤት ያለዉን ኩንትራት ዉል እስካሁን አለማደሱ አሌክሲ ሳንቸዝ በክለቡ አርሰናል የመቆየት ፍላጎት እንደሌለዉ ያስታዉቃል ተብሎል። ሆኖም አርሰናል ሳንቸዝ የማቆየት አሳቡ የሚሳካ አይመስልም በዚህም አርሰናል ተጫዋቹን ዝም ብሎ ከሚሸጠዉ ይልቅ ለሚሸጠዉ ክለብ ዉስጥ በምትኩ እንግሊዛዊዉን ተጫዋች ራሄም ስተርሊንግ መግዛት ይፈልጋሉ።

ሆነም ቀረ አሌክሲሳንቸዝ በጥር ሲቲ የሚቀላቀል ከሆነ ስተርሊንግም አርሰናል የመቀላቀሉ ነገር እዉን ይሆናል ሲል ያስነበበዉ (marca) ነዉ።

No comments:

Post a Comment

አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦

Featured Post/ቀጣይ ልጥፍ

የዝውውር ዜናዎች

  ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር...