✔ PSG LINE UP CONTE
PSGዎች በቻምፒየንስ ሊጉ ላይ ግማሽ ፍፃሜ መድረስ የማይችሉ ከሆነ አሰልጣኙን ለመቀየር ወስነዋል። እናም የቼልሲው አለቃ አንቶኒዮ ኮንቴ የክለቡ ባለቤቶችን ቅድመ ሁኔታ የሚያሟሉ ናቸው ብሏል Le Parisien.
ምንም እንኳን ጣሊያናዊው አሰልጣኝ በስታምፎርድ ብሪጁ ክለብ የሚያቆየው ኮንትራት እስከ 2019 ያለው ቢሆንም ከባለስልጣናቱ ጋር ተቃቅሮአል።
በሌላ በኩል ደግሞ የኡናይ ኢምሬ የሊግ ዋኑ ኮንትራታቸው በቀጣዩ ክረምት ላይ ኤክስፓየር የሚያደርግ ይሆናል። ምንም እንኲን በሊጉ እስካሁን ምንም ሽንፈት ባይደርስበትም የመባረር ጫና ውስጥ ይገኛል።
✔ BARCA MAKE £105M COUTINHO BID
ባርሴሎናዎች የሊቨርፑሉን አማካይ ፊሊፕ ኩቲንዎን ለማዛወር የ£105 million ሂሳብ አቀረቡ ያለን የስፔኑ እትም Sport ነው።
የካታላኑ ክለብ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ላይ ኩቲንዎን ለማዛወር ያልተሳካ ሙከራ አድርገው ከሽፎባቸዋል። አሁን ግን ብራዚላዊውን ተጭዋች ለማስፈረም የተሻሻለ ሂሳብ በመያዝ በድጋሚ ሙከራ ለማድረግ ተሰናድተዋል።
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ ምንም እንኳን ሊቨርፑሎች በተደጋጋሚ ግዜ ከባርሴሎና የቀረበላቸውን ሂሳብ በክረምቱ ውድቅ ቢያደርጉትም በቀጥታ የ £132m ሂሳብ የሚቀርብላቸው ከሆነ ግን ሊለቁት ይችላሉ።
✔ ARSENAL SET OZIL ASKING PRICE
አርሰናሎች ብፕጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ ሜሱት ኦዚልን ለመልቀቅ የ£30 million ሂሳብ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ ብሏል Daily Star ጋዜጣ።
መድፈኞቹ ጀርመናዊውን አማካይ ለመሸጥ ዝግጁ የሆኑ ሲሆን ኮንትራቱ በ2017-18 አመት ላይ ይጠናቀቃል ተብሏል። እናም የማንቸስተር ዩናይትዱ አለቃ ጆዜ ሞሪንዎ በሪያል ማድሪድ ሳለ ያሰለጠነውን አማካይ ወደ ኦልትራፎርድ በማዛወር በድጋሚ አብሮት መስራት ይፈልጋል።
✔ MAN UTD AGREE DEAL FOR EMBALO
ማንቸስተር ዩናይትዶች የቤኔፊካውን ታዳጊ ኮከብ ኡማሮ ኢምቦሎን ከወዲሁ ለማዛወር ቅድመ ስምምነት ላይ ደረሱ ብሏል Mirror .
የ16 አመቱ የቀኝ ክንፍ ተጫዋች በዚህ አመት በተደረጉ የፖርቹጋል ከ17 አመት በታች 18 ጨዋታዎች ላይ 15 ጎሎችን በማስቆጠር የበርካታ ትላልቅ አውሮፓ ክለቦችን ትኩረት መሳብ ችሎ ነበር። ያም ሆኖ ተጭዋቹ እስካሁን ድረስ ምንም የፖርቹጋል ፕሪሚየር ሊጋ ጨዋታ አላረገም።
✔ BARCELONA SCOUTING FEKIR
ባርሴሎናዎች የሊዮኑን የፊት መስመር ተጭዋች ናቢ ፊከር እድገት ሁኔታ በቅርበት ሆነው እየተከታተሉት ይገኛል ያለው ደግሞ Marca ነው።
የ24 አመቱ ተጭዋች በዚህ የውድድር አመት ላይ ለሊግ ዋኑ ክለብ ድንቅ ብቃቱን እያሳየ ሲሆን የባርሴሎናው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሮበርት ፈርናንዴዝ ሊዮኖች በዩሮፓ ሊጉ ኤቨርተንን ሲያሸንፉ በአካል ተገኝተው ገምግመውታል።
የካምፕ ኑው ግዙፍ ክለብ ለተጭዋቹ ዝውውር ጥያቄ ለማቅረብ የተሰናዱ ሲሆን ከፊሊፕ ኩቲንዎ ይልቅ በቀላሉ እንደሚያገኙትም ያስባሉ።
✔ OTHER SHORT STORIES
▶ ፖል ፖግባ ፣ ማይክል ካሪክ እና ማርኮስ ሮሆ ከማንቸስተር ዩናይትድ ሁለተኛው ቡድን ጋር ልምምድ ሰርተዋል። [ESPN]
▶ ዌስትሃም ዩናይትዶች በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ የበርንማውዙን ሃሪ አርተር እና በክረምቱ ጠይቀውት የነበረውን ደግሞ ዊልያም ካርቫልዮ ለማዛወር ጥያቄ ያቀርባሉ። (Source: Daily Mirror)
▶ ክሪስታል ፓላሶች አሰልጣኝ ሮይ ሆድሰን የአርሰናሉን አማካይ ጃክ ዊልሸር በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ ለማስፈረም ጥያቄ ያቀርባሉ። (Source: Telegraph)
▶ ባየር ሙኒኮች የኢንተር ሚላኑን አጥቂ ማውሮ ኢካርዲን ለማዛወር የሚደረገውን ፉክክር ከአርሰናል እና ቼልሲ ጋር ተቀላቅለዋል። (Source: Don Balon)
▶ ታዋቂው የኢንተርኔት ኦንላየን ሽያጭ ተቋን Amazon በማንቸስተር ሲቲ ከመጋረጃው ጀርባ የሚሰሩ ተከታታይ የዶክመንተሪ ፊልሞች ስራ ላይ ለክለቡ ቢያንስ የ£10m ሂሳብ ለመክፈል ተስማምተዋል። (Source: tariqpanja )
▶ ማንቸስተር ሲቲዎች ለብራዚላዊው አጥቂ ገብርኤል ሄሱስ አዲስ ሳምንታዊ የተሻሻለ የ£100,000 ደሞዝ ሊከፍሉትሽያሰቡ ሲሆን ሳምንታዊ የ£30,000 ጭማሪ ያለው ነው። (Source: Daily Mail)
▶ ሰርጂዎ አጉዌይሮ በ2019 የውድድር አመት ላይ ማንቸስተር ሲቲን በመልቀቅ ወደ አሳዳጊ ክለቡ ኢንዲፐንዴንቴ እንደሚመለስ ተናገረ።
(Source: Daily Mirror)
No comments:
Post a Comment
አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦