Monday, May 21, 2018

ሰኞ ከሰአት በኃላ ላይ የወጡ የዝውውር ዜናዎችና ሌሎች መረጃዎች



ፔፕ ጓርዲዮላ ኤዲን ሃዛርድን በክረምት ማስፈረም ይፈልጋል፡፡ የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ በክረምት ማስፈረም ከሚፈለጋቸው ተጫዋቾች ውስጥ ሃዛርድን ተቀዳሚ ምርጫው አድርጓል፡፡ ሲቲዎች በከፍተኛ ሁኔታ ሪከርዶችን እየሰባበሩ ሻምፒየን ቢሆኑም አሁንም ቡድናቸውን ማጠናከር ይፈልጋሉ፡፡ ይሁንና ሃዛርድን በርካሽ ዋጋ አያገኝቱም፡፡ በትንሹ 100 ሚ. ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ እና 300 ሺህ ፓውንድ ሳምንታዊ ደሞዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ (Daily Star)



የቶተንሃም ሆትስፐሩ ተከላካይ ቶቢ አልደርዊረልድ በማንችስተር ዩናይትድ ከሚፈልጉ ተጫዋቾች ውስጥ የመጀመሪያው ሆኗል፡፡ ጆሴ ሞሪንሆ በኦልትራፎርድ ያደረጉት የ2ኛው አመት ቆይታ ያለዋንጫ ተጠናቋል፡፡ ማንችስተር ዩናይትድም ለሞሪኒሆ 250 ሚ. ፓውንድ ለዝውውር ለመስጠት ወስኗል፡፡ በዚህም ሞሪንሆ የናፖሊውን ጆርጊንሆ፣ የሻክታሩን ፍሬድ እንዲሁም የኒሱን ጄን ማይክል ሴሪ ለማስፈረም እንደሚንቀሳቀሱ ይጠበቃል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ አንቶኒ ማርሲያል፣ ሉክ ሾው፣ ዴሊ ብሊንድ እና ማቲዮ ዳርሚያን ኦልትራፎርድን በመልቀቅ ወደ ሌላ ክለብ ሊያቀኑ ይችላሉ፡፡ (Mirror)



ተሰናባቹ የፒኤስጂ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪ የአርቴታ ተፎካካሪ ሆኖ ብቅ ብሏል፡፡ የቀድሞው የአርሰናል አማካይ ሚኬል አርቴታ የአርሰናል አሰልጣኝ የመሆን እድሉ ሰፊ መሆኑን ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ ሲዘገብ ነበር፡፡ ይሁንና እስካሁን ምንም የተፈረመ ስምምነት የለም፡፡ በሲቪያ እና ፒኤስጂ በርካታ ዋንጫዎችን ማሳካት የቻለው ኡናይ ኤምሪ ዋንጫ ለተጠማው አርሰናል መፍትሄ ሊሆን ይችላል የሚሉ የአርሰናል የቦርድ አባላት መኖራቸው ለአርቴታ እንቅፋት ሊሆን ይችላል፡፡ (Daily Mail)



ሮማዎች የአያክሱን ጀስቲን ክላይቨርት ለማስፈረም የሚደረገውን ፉክክር በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ክላይቨርት ከአያክስ የቀረበለትን አዲስ ኮንትራት አልፈርምም በማለቱ ክለቡ ሊሸጠው እንደሚገደድ ታውቋል፡፡ በርካታ ክለቦች ልጁን ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ማንችስተር ዩናይትድ የልጁ ማረፊያ ሊሆን ይችላል ቢባልም ሮማዎች ገፍተው በመሄድ ልጁን በእጃቸው ለማስገባት ጥረት ባመድረግ ላይ ናቸው፡፡ (France Football)

═════════════════════════
📂  ADVERTISEMENTS

የቴሌግራም ገፃችንን ይጎብኙ:
➧ https://t.me/hair_regrowth
═════════════════════════

ፖግባ ወደፊት ለፒኤስጂ መጫወት እንደሚችል አስታወቀ፡፡ በዚህ የወድድር አመት ከአጋማሽ በኋላ በአብዛኛው ጨዋዎች ወደ ተቀያሪ ወንበር የወረደው ፖግባ ማንችስተርን ሊለቅ ይችላል የሚሉ ዘገባዎች እንዲወጡ አድርጎ ነበር፡፡ ይሁንና እሱ በማንችስተር መቆየት እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡ በቅርቡ ደግሞ ፓሪስ ውስጥ በተደረገ የፎቶ ስነስርዓት ላይም ተገኝቶ ነበር፡፡ ከካናል ፕላስ ለቀረበለት ጥያቄም ለፎቶ ፕሮግራም ፓሪስ መገኘቱ ከዝውውር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ከገለፀ በኋላ አንድ ቀን በParc des france ለምን አልጫወትም; ውብ ስታዲየም ነው ሲሉ ወደፊት ሊዘዋወር እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል፡፡ (Goal)



ኤቨርተኖች የቀድሞውን የዋትፎርድ አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ እንደሚቀጥረት ተስፋ አድርጓል፡፡ ኤቨርተኖች በጥር ወር ሲልቫን ለማዘዋወር በመንቀሳቀሳቸው ዋትፎርዶች ጉዳዩን ለፕሪሚየር ሊጉ ከሰው ነበር፡፡ ዋትፎርዶች በኋላ ሲልቫን ከአሰልጣኝነት አባረውትም ነበር፡፡ የኤቨርተኑ ባለቤት ፋርሃድ ሞሺሪ ሲልቫን ከማስፈረማቸው በፊት የክሱ ጉዳይ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ይፈልጋሉ፡፡ (Daily Mail)



ባየርሙኒኮች የቫሌንሺያውን አጥቂ ሮድሪጎ ሞሬኖ ለማስፈረም የሚደረገውን ፉክክር በመምራት ላይ ይገኛል፡፡ በ2017/18 ለቫሌንሺያ 19 ጎሎችን ያስቆጠረው የ27 አመቱ ሮድሪጎ በብርካታ አውሮፓ ክለቦች በመፈለግ ላይ ይገኛል፡፡ ባየር ሙኒክም እንዚህን ክለቦች በመምራት ላይ ይገኛል፡፡ ሙኒኮች አጥቂውን ላመስፈረም ከቫሌንሺያ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል፡፡ ሮድሪጎም በ60 ሚ. ዩሮ ወደ ጀርመን ሊዘዋወር ይችላል፡፡ (Marca)



የቀድሞው የማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝ ማኑዌል ፔሌግሪኒ አዲሱ የዌስትሃም አሰልጣኝ ለመሆን ተቃርበዋል፡፡ ዌስትሃሞች የኒውካስትሉን ራፋ ቤኒቴዝ ለመቅጠር ፈልገው ነበር፡፡ ይሁንና የኒውካስትሉ ባለቤት ማይክ አሽሊ ለዝውውር ብዙ ገንዘብ እንደሚመድብ ቃል ከገባ በኋላ ቤኒቴዝ እዛው ለመቆት ወስነዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ዌስትሃሞች የአሁኑን የሄቤ ቻይና ፎርቹን አሰልጣኝ ለመቅጠር ተቃርቧል፡፡ (Mirror)



የናፖሊው ሊቀመንበር ኦውሪሊዮ ዴ ላውሬንቲስ አሰልጣኛቸው ማውሪዚዮ ሳሪ ክለባቸውን ሊለቁ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ላውረንቲስ እንደተናገሩት ከሆነ ሳሪን አዲስ ኮንትራት ለማስፈረም ያደረጉት ጥረት እንዳለተሳካ እና ጊዜ እያለቀባቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ሳሪ ቸልሲዎች ኮንቴን የሚያባሩ ከሆነ የሳቸውን ቦታ እንደሚተኩ ይጠበቃል፡፡ (Goal)



የአርሰናሉ አማካይ ጃክ ዊልሸር የቀረበለትን የ3 አመት ኮንትራት በመፈራረም በክለቡ እንደሚቆይ አስታውቋል፡፡ ዊልሸር ኮንትራቱ በዚህ አመት የሚናቀቅ ሲሆን ኤቨርተን እና ዌልቭስ ልጁን ማስፈረም ይፈልጉ ነበር፡፡ (Mirror)

═════════════════════════
📂  ADVERTISEMENTS

የቴሌግራም ገፃችንን ይጎብኙ:
➧ https://t.me/ethio_bodybuilders
═════════════════════════

No comments:

Post a Comment

አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦

Featured Post/ቀጣይ ልጥፍ

የዝውውር ዜናዎች

  ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር...