Tuesday, May 8, 2018

ማክሰኞ ከሰአት በኃላ ላይ የወጡ በርካታ አጫጭር እና ሰፋ ያሉ የዝውውር ዜናዎች ፣ አስተያየቶች እና ሌሎችም አጫጭር ትኩስ የእግር ኳስ መረጃዎች


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ማንቸስተር ዩናይትዶች ሚሊንኮቪች ሳቪችን ለማዛወር ተስማሙ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


እንደ TheSun ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ማን.ዩናይትዶች በ80ሚ.ፓ የዝውውር ሂሳብ ወይም በ108ሚ. ዶላር ሂሳብ የላዚዎውን አማካይ ሰርጂ ሚሊንኮቪች ሳቪች ዝውውር ከስምምነት ላይ ደረሱ። ተጨዋቹ የመጀመሪያው የክለቡ ፈራሚ ይሆናል።


እንደ ዘገባው ከሆነ ጆዜ ሞሪንዎ በአማካይ ክፍል ላይ በማርዋን ፌላይኒ መውጣት እና በማይክል ካሪክ መልቀቅ ሳቢያ የሳሳውን የአማካይ ክፍል ማጠናከር ይፈልጋሉ።


የዝውውሩ ዋጋ ሚሊንኮቪች ሳቪች በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ ከፖል ፖግባ በመቀጠል ሁለተኛው ከፍተኛ የዝውውር ሂሳብ የተከፈለበት ተጭዋች ይሆናል።


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ኢኔሽታ ወደ ጃፖን ለመዛወር ተስማማ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


አንድሬስ ኢኔሽታ ወደ ጃፓኑ ክለብ ቪሴል ኮቤ ለመዛወር ከስምምነት ላይ ደረሰ ሲል ESPN ዘገበ።


ስፔናዊው የ31 አመት ኮከብ ለJ-League ተወዳዳሪው ክለብ ለ3ት አመታት ለመጫወት የተስማማ ሲሆን አመታዊ የ30ሚ. ዶላር ወይም የ22ሚ.ዩ ሂሳብ ደሞዝ ይከፈለዋል።


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
PSGዎች ዶናሩማን ተቀዳሚ ኢላማቸው አድርገውታል
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


እንደ ፈረንሳዊው ተነባቢ ጋዜጣ ዘገባ Lequipe እንዳስነበበው ከሆነ PSGዎች ዶናሩማን የክረምቱ የዝውውር መስኮት ተቀዳሚ ኢላማቸው አድርገውታል።


የሊግ ዋኑ ሻምፒየን ክለብ እንዳሉት ከሆነ ያሁኑን የክለባቸውን ግብ ጠባቂ አልፎንሴ አሪዎላ በዶናሩማ መተካት ይፈልጋሉ። ሆኖም ዝውውሩን እውን የሚያደርጉት የፊፋን Financial Fair Play Rule የማይትሱ ከሆነ ብቻ ነው።


የፓሪሱ ክለብ ሰዎች የክለቡን ቁ1 ግብ ጠባቂ በማሰስ ላይ ሲሆኑ ቲቢዎት ኩርቱዋንም ቀርበው አናግረውታል።


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አርሰናሎች በዊልሸር ኮንትራት ዙሪያ ተስፋ ሰንቀዋል
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


እንደ ቴሌግራፍ ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ አርሰናሎች ከጃክ ዊልሸር ጋር ሲያደርጉት የነበረውን የኮንትራት ድርድር ንግግር ተስፋ ሰጪ ሆኖላቸዋል። ተጨዋቹ በዚህ ሲዝን ወጥ በሆነ ጥሩ አቋም ብቃት ላይ ይገኛል።


መድፈኞቹ ባለፈው ክረምት ላይ ተጭዋቹን ለመሸጥ ብዙ ሞክረው የነበረ ቢሆንም አሁን ግን በክለቡ እያገኘ ያለውን ሳምንታዊ የ110,000 ፖውንድ ደሞዝ ላይ ጥቅማ ጥቅሞችን በመጨመር አዲስ ኮንትራት ሊያስፈርሙት ይፈልጋሉ።


ተጨዋቹ በሰሜን ለንደኑ ክለብ የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ለመፈራረም እንደተቃረበ ለቃቂው አሰልጣኝ አርሰን ዌንገር ተናግረዋል።


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የጀርጊንዎ ወኪል ደንበኛው በበርካታ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች እንደሚፈለግ ተናገረ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


እንደ ብራዚላዊው የናፖሊ አማካይ ጆርጊንዎ ወኪል ከሆነ ደንበኛው በ'አራት ወይም አምስት' የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ለዝውውር ይፈለጋል። ሆኖም የሴሪአው ክለብ የተጨዋቹ የወደፊት ቆይታ ላይ እስካሁን ምንም ውሳኔ አላሳለፈም።


ወኪል ጆአዎ ሳንቶስ እንዳለው ከሆነ ሁሉም ሰው የእንግሊዝ ክለቦች ሊያዛውሩት እንደሚፈልጉ ያውቃል። ሆኖም ግን የናፖሊዎችን ፍላጎት ስላልተረዳ ከየትኛውም ክለብ ጋር ንግግር እያደረገ አይደለም።


ጆርጊንዎ በክለቡ እስከ 2020 ድረስ የሚያቆየው ውል ያለው ሲሆን ጣሊያናዊው አማካይ አዲስ ኮንትራት ሊፈራረም እንደሚችልም ፍንጭ ሰጥተዋል።


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ሉዊስ ሄነሪኬ ራሱን አስወድዶ ከአርሰናል መንበር ለመረከብ እየራቀ ነው
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


እንደ the Mirror ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ አርሰን ዌንገርን ለመተካት በሚደረገው ፉክክር ላይ የቀድሞው የባርሴሎና አሰልጣኝ ሉዊስ ሄነሪኬ ውድ ኮንትራት በመጠየቅ ራሱን ከፉክክሩ እያገለለ ነው።


ሄነሪኬ ክለቡን ለመረከብ የጠየቀው አመታዊ ደሞዝ ከግብር በኃላ 15ሚ.ፓ ወይም 20ሚ. ዶላር ነው ተብሏል። ሆኖም አሁንም ድረስ ግን ከፉክክሩ ውጪ አይደለም።


አርሰናሎች መጪው የአለም ዋንጫ ውድድር ከመጀመሩ ቀደም ብለው ቀጣዩን የክለቡ አለቃ ለመቅጠርና ይፋ ለማድረግ እየሰሩ ይገኛሉ።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ማስታወቂያ ...

No comments:

Post a Comment

አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦

Featured Post/ቀጣይ ልጥፍ

የዝውውር ዜናዎች

  ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር...