Thursday, May 10, 2018

ዕለተ ሃሙስ የወጡ በርካታ አጫጭር እና ሰፋ ያሉ የዝውውር ዜናዎች ፣ አስተያየቶች እና ሌሎችም አጫጭር ትኩስ የእግር ኳስ መረጃዎች


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ባርሴሎና 8 ተጫዋቾችነ ለመሸጥ አቅዷል


➧ ባርሴሎና በክረምት የአትሌቲኮ ማድሪዱን አንቶን ግሪዝማን ለማስፈረም ይፈልጋል፡፡ እሱን ለማሳካት ደግሞ ከፍተኛ ገንዘብ ያስፈልገዋል፡፡ ገንዘቡን ደግሞ ስምንት ተጫዋቾችን በመሸጥ ለማዘጋጀት ወስኗል፡፡ የስምንቱ ተጫዋቾች ሽያጭ እስከ 100 ሚ. ዩሮ ሊያስገኝለት እንደሚችልም ተገምቷል፡፡

ተጫዋቾቹ ሉካ ዲኘ፣ አንድሬ ጎሜዝ፣ አልክስ ቪዳል፣ ፓኮ አልካሴር፣ ዴኒስ ሱዓሬዝ፣ ጄራርደ ዴሎፉ፣ ሙኒር ኤል ሀዳዲ እና ራፊናህ ናቸው፡፡

ባርሴሎና አንቶን ግሪዝማንን ከማስፈረሙም በተጨማሪም ሌሎች ተጫዋቾችንም እንሚያመጣ ይጠበቃል፡፡   (ምንጭ፡ Sky Sports News)



ሪያል ማድሪዶች ግብ ጠባቂ አሰሳ ላይ ናቸው


 ➧ ሪያል ማድሪዶች የሮማውን ግብ ጠባቂ አሊሰን ለማስፈረም መዘጋጀታቸውን RMC Sport ዘገቧል፡፡ አሊሰን በዚህ የውድድር አመት በሮማ ባሳየው ምርጥ ብቃት መሰረት ስሙ ከሊቨርፑል እና ማንችስተር ዩናይትድ ጋር ሲያያዝ ከርሟል፡፡ ሪያል ማድሪድ ከዚህ በፊት ስሙ ከቲቦ ኮርቱዋ እና ዴቪድ ዴ ሂያ ጋር ሲያያዝ ቢከርምም አሁን ግን ፉቱን ወደ አሊሰን በማዞር ለልጁ ክፍያ ለማቅረብ መዘጋጀቱም ተዘግቧል፡፡


 ዴ ሊግት በክረምቱ አያክስን መልቀቅ ይፈልጋል


 ➧ የአያክስ አምስተርዳሙ ተከላካይ ማቲያስ ዴ ሊግት በአውሮፓ ከሚገኙ ምርጥ ተጫዋቾች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በዚህም መሰረት የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት ወደ ሌላ ክለብ ለመዘዋወር እንዳቀደ ተዘግቧል፡፡ ወኪሉ ሚኖ ራዮላም ይህን እንደሚያሳካለት እምነት ጥሏል፡፡ ባየር ሙኒክ፣ ባርሴሎና፣ ማንችስተር ሲቲ እና ቶተንሃም ሆትስፐር የልጁ ፈላጊ መሆናቸውን De Telegraaf ዘግቧል፡፡



 ማንችስተር ሲቲዎች የሌዚስተር ሲቲውን ሪያድ ማህሬዝ ማስፈረም ይፈልጋሉ


➧ ሲቲዎች ባለፈው የጥር መስኮት ልጁን ለማስፈረም ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡ ይሁንና ሌዚስተር 95 ሚ. ፓውንድ ካልከፈላችሁ በማለቱ ዝውውሩ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ በሰዓቱ ሲቲ ያቀረበው የ65 ሚ. ፓውንድ ክፍያ ነበር፡፡ ማህሬዝም ቢሆን ወደ ሲቲ ለመሄድ ጥረት አድርጎ ነበር፡፡ ይሁንና አልተሳካም፡፡ አሁን ግን ሲቲዎች ዳግመኛ ወደ ሌዚስተር በመመለስ ልጁን ለማስፈረም ጥረት ያደርጋሉ ሲል The Times ዘግቧል፡፡


ፒኤስጂ የፉልሃሙን ወጣት ርያን ሴሴይኖን ለማስፈረም የሚደረገውን ጥረት ግፍተውበታል


➧ ፒኤስጂ የፉልሃሙን ወጣት ርያን ሴሴይኖን ለማስፈረም የሚደረገውን ጥረት ግፈቶበታል ሲል Daily Mirror ዘግቧል፡፡ የ17 አመቱ ተጫዋች በቶተንሃምና ማንችስተር ዩናይትድ ይፈለጋል፡፡ ነገር ግን የሊግ 1 ሻምፒዮኑ ፒኤስጂ 50 ሚ. ፓውንድ በመክፈል ልጁን ለመውሰድ ተዘጋጅቷል፡፡ የሴሴይኖን እጣ ፈንታ በክለቡ ውጤት ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡ ፉልሃም በአሁኑ ሰዓት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለማለፍ በጥሎ ማለፉ ተደልድሏል፡፡ ምናልባት አሸንፎ የሚያልፈ ከሆነ ወጣቱ በፉልሃም ሊቆይ ይችላል፡፡


‹‹ፖግባ በማንችስተር ዩናይትድ የሚቆይ ይመስለኛል›› 


 ➧ ‹‹ፖግባ በማንችስተር ዩናይትድ የሚቆይ ይመስለኛል›› ሲሉ ጆሴ ሞሪንሆ ለጋዜጠኞች ገልፀዋል፡፡ ፖግባ ከሞሪንሆ ጋር ግጭት ውስጥ ገብቷል ተብሎ ሲዘገብ ነበር፡፡ ይሁንና ክለቡም ሆነ እሳቸው ልጁን መሸጥ እንደማይፈልጉ አስታውቀዋል፡፡ ፖግባ ወደ ፈረንሳይ በማምራት ለፒኤስጂ ሊፈርም ይችላል የሚሉ በርካታ መረጃዎች ሲወጡ ነበር፡፡ ዘገባው የGoal ነው፡፡


የዌንገር ተተኪ እጩዎች ወደ 5 ዝቅ አሉ


 ➧ በአርሰናል የሚፈለጉ አሰልጣኞች ስም ዝርዝር ወደ አምስት ዝቅ ብሏል ሲል Daily Mail ዘግቧል፡፡ እንደ ደይሊ ሜል ዘገባ ከሆነ ሚኬል አርቴታ፣ ፓትሪክ ቪየራ፣ ማሲሚሊያኖ አሌግሪ፣ ዮዓኪም ሎው እና ሊዊስ ኤንሪኬ በዝርዝሩ ውስጥ ያሉ ናቸው፡፡ የክለቡ ባለስልጣናት ወጣት አሰልጣኝ ለመቅጠር መፈለጋቸው ደግሞ ለአርቴታ እና ቪየራ እድሉን ያሰፋል ሲል ዘገባው አክሏል፡፡


ሌሮይ ሳኔ - "ስለኮንትራት ለማውራት አልቸኩልም"


 ➧ የማንችስተር ሲቲው ሌሮይ ሳኔ ስለኮንትራት ለማውራት አልቸኩልም ማለቱን The Sun ዘገቧል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ የአመቱ ወጣት ተጫዋችን ኮንትራት ለማራዘም ሲቲዎች ከፍተኛ የሆነ ፍጎት አላቸው፡፡ በ2021 የሚጠናቀቀውን ኮንትራቱንም ከፍተኛ ደሞዝ በማቅረብ ለማራዘም አቅደዋል፡፡ ይሁንና ሳኔ ስለ ኮንትራት ማራዘም መነጋገር የሚፈልገው ከአለም ዋንጫው መጠናቀቅ በኋላ መሆኑ ተዘግቧል፡፡


 ሊቨርፑል ሌይቴን ለማስፈረም የሚደረገውን ጥረት እየመራ ይገኛል


 ➧ የፖርቶው ወጣት ተከላካይ በአርሰናል እና ማንችስተር ሲቲም ይፈለጋል፡፡ አርሰናል ክለቡ ፖርቶ የሚፈልገውን 15 ሚ. ዩሮ የውል ማፍረሻ ለመክፈልም ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ ይሁንና ሊቨርፑሎች በቅርቡ ጥረታቸውን በማጠናከር ልጁን ከአርሰናል ለመንጠቅ እየሞከሩ ይገኛል፡፡ ዘገባው የThe Guardian ነው፡፡


 ባርሴሎና ዴ ጆንግን በ2019 ማስፈረም ይፈልጋል


 ➧ አንደ Mundo Deportivo ዘገባ ከሆነ ባርሳዎች በ2018 ለማስፈረም ያቀዱት የአትሌቲኮውን አንቶን ግሪዝማን ነው፡፡ በተጨማሪም የግሬሚዮውን አማካይ አርተር ሜሎ ለማስፈረም ተስማምተዋል፡፡ ይሁንና በእድሜ እየገፋ ያለውን የመሃል ሜዳቸውን ሀይል ለመስጠም ወጣቱን የአያክስ አምስተርዳም አማካይ ፍሬንኪ ዴ ጆንግን ለማስፈረም አቅደዋል፡፡ ነገር ግን ልጁን በ2019 ነው ማስፈረም የሚፈልጉት


  ካርል ሄንዝ ሩሚኒግ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በክለባቸው እንደሚቆይ አስታወቁ


 ➧ የባየር ሙኒኩ ሀላፊ ካርል ሄንዝ ሩሚኒግ አጥቂያቸው ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በቀጣዩ አመት በክለባቸው እንደሚቆይ አስታወቁ፡፡ ካሪም ቤነዜማ በዚህ የውድድር አመት አስቸጋሪ ጊዜን በማሳለፉ ምክንያት ማድሪድ ሌዋንዶውስኪን ሊያስፈረም ይችላል የሚሉ በርካታ ዘገባዎች ሲወጡ ነበር፡፡ ይሁንና ሩሚኒግ አጥቂውን መልቀቅ እንደማይፈልጉ እና በቀጣዩ አመትም የባየር ሙኒክን ማለያ እንደሚለብስ ተናግረዋል ሲል የዘገበው Goal ነው፡፡


ኔይማር ከማድሪዶች ጋር በድብቅ ተነጋግሯል


➧ የፒኤስጂው ኮከብ ብራዚላዊው ኔይማር በማርች ወር ውስጥ ከሪያል ማድሪድ ጋር በድብቅ ድርድር ማድረጉ እየተዘገበ ይገኛል፡፡ ኔይማር ፈረንሳይን በመልቀቅ ወደ እስፔን መመለስ ይፈልጋል ሲልም Express- ASን በመጥቀስ አስንብቧል፡፡



➧ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ያደጉት ዎልቮች ወይኒ ሩኒን ማስፈረም ይፈልጋ፡፡ የ32 አመቱ ወይኒ ሩኒ ከአሰልጣኙ ጋር ባለመስማማቱ ክለቡን ሊለቅ ይችላል ሲል የዘገበው Birmingham Mail ነው፡፤


➧ አርሰናሎች ለጃክ ዊልሸር የ3 አመት ኮንትራት ማቅረባቸውን Star ዘገቧል፡፡ የዊልሸር ኮንትራት በዚህ ክረምት ይጠናቀቃል፡፡


➧ አርሰናሎች የባየር ሊቨርኩሰኑን ግብ ጠበቂ በርንድ ሌኖ ለማስፈረም ድርድር መጀመራቸውን Express - Bildን በመጥቀስ ዘግቧል፡፡

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ADVERTISEMENT

No comments:

Post a Comment

አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦

Featured Post/ቀጣይ ልጥፍ

የዝውውር ዜናዎች

  ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር...