MONACO & BARCA HAD MBAPPE
AGREEMENT
ባርሴሎና እና ሞናኮዎች የ18 አመቱ ታዳጊ ባለተሰጥዎ ተጭዋች ኬይላን ምባፔ በረብጣ የዝውውር ሂሳብ የፈረንሳዩን ክለብ ፒ.ኤስ.ጂን ከመቀላቀሉ በፊት ከባርሴሎና ጋር ሙሉ ለሙሉ ተስማምቶ ጨርሶ ነበር ያለን L'Equipe ነው።
እንደዘገባው ከሆነ ስምምነቱ ኬይላን ምባፔን ወደ ካታሎኑ ክለብ እንዲያመራ እና በተቃራኒው አርዳ ቱራን ወደ ሞናኮ እንዲዛወር በወረቀት ደረጃ ያለቀ ቢሆንም ተጭዋቹ ግን የስምምነቱን ፊርማ ማኖር አልቻለም።
ምባፔ በኃላ ላይ ሳይጠበቅ ለPSGዎች በአንድ አመት የውሰት ውል እና በቀጣዩ ክረምት በ€180 million የቋሚ ዝውውር የፓሪሱን ክለብ ለመቀላቀል መስማማቱ ይታወሳል።
MENDES WANTS €100M BARCA DEAL
FOR JAMES
የህምስሮድሪጌዝ ወኪል የሆነው ሜንዴዝ ደንበኛው በባየር ሙኒክ የቋሚ ውሉን እንዲፈርም ካደረገ በኃላ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ላይ ደግሞ በ€100 million, ሂሳብ ባርሴሎና እንዲዛወር ለማድረግ አቅዷል ያለው የስፔኑ ጋዜጣ Don Balon ነው።
ባየር ሙኒኮች ሮድሪጌዝን በሁለት አመት የውሰት ኮንትራት ያስፈረሙት ባለፈው ክረምት ሲሆን በስምምነታቸው መሰረት የሚፈልጉት ከሆነ የ€60m ሂሳብ ለሪያል ማድሪድ በመክፈል በቀጣዩ ክረምት ላይ በቋሚ ዝውውር የሚያስፈርሙበትን አማራጮች ተስማምተዋል።
ያም ሆኖ ሮድሪጌዝ ግን ባየር ሙኒኮች ካርሎ አንቼሎቲን በማሰናበታቸው ደስተኛ ያልሆነ ሲሆን ከሱ በተጨማሪም ቲያጎ አልካንትራ እና አርትሮ ቪዳልም በአሊያንዝ አሬናው ክለብ እስካሁን መረጋጋት ተስኖአቸዋል ተብሏል።
ስለሆነም ወኪሉ ሜንዴዝ ደንበኛው ወደ ባርሴሎና እንዲዛወር የሚፈልግ ሲሆን ተጫቹ ወደ ካምፕ ኑ የመሄድ ፍላጎት አለመያዙና ወደ ማድሪድ መመለስ መፈለጉ ለወኪሉ አስቸጋሪ ያደርግበታል ተብሏል።
NAVAS TO REPLACE CECH AT ARSENAL?
አርሰናሎች የሪያል ማድሪዱን ግብ ጠባቂ ኬይለር ናቫስ የፒተር ቼክ የረጅም ግዜ ተተኪ በመሆን ወደ ኤምሬትስ እንዲዛቀር ፍላጎት እንዳላቸው የስፔኑ እትም Diario Gol ዘገበ።
የናቫስ የሪያል ማድሪድ ቆይታ ባሁን ሰአት እርግጠኛ ያልሆነ ሲሆን ኮስታሪካዊው ኢንተርናሽናል ክለቡ በተደጋጋሚ ግዜ የማን.ዩናይትዱን ዴቪድ ደ ሂያ ለማዛቀር ተንቀሳቅሷል በሚሉ ዜናዎች ደስተኛ አልሆነም።
ሊቨርፑሎች ከወዲሁ ናቫስን የማዛወር ፍላጎት እንዳላቸው ለስፔኑ ክለብ ያሳወቁ ቢሆንም አሁን ደግሞ የአርሰናሉ አለቃ አርሰን ዌንገር ተጫቹን የቼክ ቁ1 ምትክ ለማድረግ ፈልገውታል።
ARSENAL EYE £10M DEAL FOR FORMER PLAYER
አርሰናሎች ኦጉዝሃን ኦዝያካፕን በድጋሚ መልሰው በ£10 million በማስፈረም ወደ ክለቡ ካመጡት በኃላ የሜሱት ኦዚልን ቦታ እንዲሸፍንላቸው ይፈልጋሉ ሲል የቱርኩ ድህረ ገፅ Turkish-Football ዘገበ።
ኦዝያካፕ አርሰናልን በመልቀቅ የቱርኩን ቤሺክታሽ ክለብ የተቀላቀለው በ2012 ላይ ሲሆን ወደእዛ ካመራ በኃላ ብቃቱን ተጠቅሞ ጥሩ እንቅስቃሴ በቱርኩ ሊግ እያደርገ ይገኛል።
አማካዩ በዚህ የውድድር አመቱ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊጉ ውድድር ላይ ባሳየው ድንቅ ብቃት ሳቢያ ፈላጊ ክለቦችን ያገኘ ሲሆን አርሰን ዌንገር በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ ለ25 አመቱ ተጭዋች ጥያቄ ለማቅረብ ተሰናድተዋል። ሜሱት ኦዚል አዲስ ኮንትራት አልፈርምም በማለቱ በክረምቱ ክለቡን እንደሚለቅ በመስጋታቸው ሊተኩት ይፈልጋሉ።
MOURINHO WANTS VARANE FOR DE GEA
ጆዜ ሞሪንዎ ራፋኤል ቫራንን በዴቪድ ደ ሂያ የሪያል ማድሪድ ዝውውር ስምምነት አካል በማድረግ ወደ ኦልትራፎርድ ሊያመጡት ይፈልጋሉ ሲል የዘገበው Don Balon ነው።
የማንቸስተር ዩናይትዱ ግብ ጠባቂ የሪያል ማድሪዶች የክረምቱ ቀዳሚ ቁ1 የዝውውር ኢላማቸው ያደረጉት ሲሆን ጆዜ ሞሪንዎ በበኩላቸው ስፔናዊው ወደ ላ ሊጋው ይመለሳል የሚል ከፍተኛ ስጋት አድሮባቸዋል።
ሆኖም በምላሹ ፖርቹጋላዊው ከማስሪድ የዝውውር አካል በማስረግ ተጭዋች ማግኘት የሚፈልጉ ሲሆን ፈረንሳዊውን ኢንተርናሽናል ተከላካይ የዝውውሩ አካል እንዲሆንላቸው የመረጡት ቀዳሚው ተጫዋች ሆኑአል።
FENERBAHCE OFFER SHAW UTD
ESCAPE
የቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ የማንቸስተር ዩናይትዱ ግራ ተመላላሽ ተከላካይ ሉክ ሾው ካለበት ቅዥት ሊያነቃው የሚችል የዝውውር ጥያቄ ሊያቀርቡለት ነው ያለው የFanatik እትም Football365 ዋቢ በማድረግ ነው።
የ22 አመቱ ተከላካይ በጆዜ ሞሪንዎ ከጉዳት ከተመለሰ ሁለት ድፍን ወራትን ያስቆጠረ ቢሆንም የመሰለፍ እድል እየተሰጠው ግን አይደለም። እንደውም በ2017-18 አመት ላይ ቋሚ ተሰላፊ የሆነበት ብቸኛው ጨዋታው በካራቦን ካፕ ላይ የተሰለፈበት ነው።
LUIZ FROZEN OUT AFTER QUESTIONING CONTE
ዴቪድ ሉዊዝ ከእሁዱ የማንቸስተር ዩናይትድ ጨዋታ ውጪ እንዲሆን የተደረገው በቡድኑ ታክቲክ ዙሪያ ከአንቶኒዮ ኮንቴ ጋር መስማማት ስላልቻለ ነው ብሏል The Times ጋዜጣ።
ብራዚላዊው ተከላካይ ሰማያዊዎቹ ማን.ዩናይትድን ከመግጠማቸው በፊት በስምንት የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት ችሏል። ሆኖም ሳይጠበቅ በእሁዱ ጨዋታ ላይ ከስኳዱ ውጪ እንዲሆን ተደርጎአል።
እናም ሪፖርቱ እንደዘገበው ከሆነ ተከላካዩ ከቡድኑ ውጪ የተደረገው ከጨዋታው በፊት በተፈጠረ የታክቲክ አለመግባባት ሳቢያ ነው።
CHELSEA CONSIDER DIAKHABY MOVE
ቼልሲዎች የሊዮኑን ተከላካይ ሙክታር ዲያባይ ለማዛወር እንቅስቃሴ ሊያደርጉ ተሰናድተዋል ያለው ደግሞ Daily Mail ነው።
የፈረንሳይ ከ21 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን አባል የሆነው ታዳጊ ተከላካይ በሊግ ዋኑ ክለብ በዚህ የውድድር አመት ላይ በተሰለፈባቸው ጭ8ዋታዎች በሙሉ ድንቅ እንቅስቃሴውን እያደረገ ሲሆን ማንቸስተር ሲቲ እና ጁቬንቱሶች ሳይቀሩ ተጫቹን ለማዛወር ከወዲሁ መልማዮቻቸው ወደ ፈረንሳይ በመላክ እየገመገሙት ይገኛሉ።
ሆኖም አንቶኒዮ ኮንቴ ክለባቸው የዝውውር ፉክክሩን በማሸነፍ ተጫቹን ከሁለቱ ክለቦች በመቅደም እንደሚያስፈርሙት ተማምነዋል ሲል ዘገባው አትቷል።
(አዘጋጅ እና ፀሐፊ፦ መንግስቱ ደሳለኝ)
No comments:
Post a Comment
አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦