Monday, October 30, 2017

ሰኞ ምሽት ላይ የወጡ ሠፊ የዝውውር ዜናዎች፣ አስተያየቶች እና ሌሎችም አጫጭር ትኩስ የእግር ኳስ መረጃዎች



PSG SET SIGHTS ON COUTINHO

ፒኤሲጂ ለኮንቲኒሆ €200 million ሊያቀርብ ነዉ።

ፊሊፕ ኮንቲኒሆ ወደ ፒኤሲጂ መሄድ አልፈልግም ቢልም እንኮን ፒኤሲጅወች ተስፋ በለመቁረጥ በድጋሜ የእናስፈርም ጥያቄ ሊያቀርቡለት ነዉ።

የሊቨርፑሉ የጨዋታ አቀጣጣይ የሆነዉ ብራዚላዊዉ ፊሊፕ ኮንቲኒሆን በቀጣዩ ክረምት የፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤሲጂ ለማስፈረም ከሊቨርፑል ባለስልጣናት ጋር ንግግር ሊያደርጉ ነዉ።

ፒኤሲጂ ብራዚላዊዉን ኮከብ ከሀገሩ ልጅ ኔይማር ጁኔር ጋር ለማጣመር ሲል ሁለተኛ ጥያቄ ለኮንቲኒሆ ሊያቀርቡ ተዘጋጅተዋል። ኮንቲኒሆ ግን በጥር የካታሎኑን ክለብ ባርሴሎና መቀላቀል እንደሚፈልግ ተናግሮል።     (the sun)


ARSENAL MISS OUT ON LEMAR

አርሰናል ፈረንሳዩን የሞናኮዉን አማካኝ ቶማስ ሌማርን በጥር ከሚያዛዉራቸዉ ተጫዋቾች መካከል ዉጭ ሊያደርገዉ እንደሆነ እየተዘገበ ነዉ።

ምክንያቱ ደግሞ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በክረምቱ የዝውውር መስኮት ተጫዋቹን ለማስፈረም ቢጥሩም እንኮን ሳያስፈርሙት ቀርተዋል። በዚህም አርሰናሎች ፊታቸዉን ወደ ሌላ ተጫዋች ሊያዞሩ እንደሆነ በመታወቁ አርሰናሎች ሌማርን ከእቅዳቸዉ ዉጭ ማድረጋቸዉ አይቀርም ተብሎል።   (daily mirror)


THREE CLUBS EYE CARRICK

የ36 አመቱ የማንችስተር ዩናይትድ አማካኝ እንዲሁም አንበል(capitan) ማይክል ካሪክ በተለያዩ የእንግሊዝ ክለቦች አይን ዉስጥ ገብቶል።

ካሪክ በአሁኑ 2017 አመት የእንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ እስካሁን ለክለቡ ተሰልፍ አልተጫወተም።

በክለቡ ማን ዩናይትድ የመሰለፍ እድል ማጣቱን ተከትሎ በጥር ተጫዋቹን ለማስፈረም ዌስትብሮሚች አልቤን፣ ሌስተር ሲቲ እና የሻምፒዩን ሽፑ ክለብ አስቶንቪላ ካሪክን ለማስፈረም ተፋጠዋል ሲል evening standard ዘግቧል።

Advertisement
ፅድት ጥርት ያሉ ምስሎችን በitel S11 ስልክ በመነሳት ከቤተሰብዎ ጋር ያሳለፉትን ትውስታዎን ያስቀሩአቸው!


LIVERPOOL WANT CASILAS

ሊቨርፑል አንጋፋዉን ግብ ጠባቂ ስፔናዊዉን አይከር ካስሊያስን የማስፈረም ሰፊ እድል አለዉ ተባለ።
ካስሊያስ በአሁኑ ሰአት ለፖርችጋሉ ክለብ ለሆነዉ ለፖርቶ በመጫወት ላይ ይገኛል።

በዚህም ሊቨርፑል በጥር ለማዛወር በቂ እድል አለዉ ተብሎል። ሊቨርፑል ካስሊያስን በነፃ ዝውውር ሊያመጣዉ ይችላል በማለት bbc ዘግቧል።

ትናንት ምሽት በላሊጋዉ ወደ ካታሎን ግዛት አቅንቶ ጌሮናን የገጠመ ሪያል ማድሪድ 2፣1 ሲሸነፍ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጊሮናዉ ተጫዋች ላይ ያልተገባ በሀሪ አሳይቶል። በዚህም በላሊጋዉ ለሁለተኛ ጊዜ ቅጣት ሊጣልበት ይችላል ተብሎል።

በሮናልዶ ጉዳይ ላይ የላሊጋዉ ምላሽ ዛሬ ምሽት ይታወቃል ተብሎል።    (sky sport)



MANGALA TO MILAN?

የማንችስተር ሲቲዉ ተከላካይ ኢልኩሚ ማንጋላ በሴሪያዉ ክለብ ኢንተር ሚላን ይፈለጋል።

ማንጋላ በማንችስተር ሲቲ የመሰለፍ እድል እያገኘ አለመሆኑ ተከተሎ ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግ ይታዉቆል።

ኢንተር ሚላንም ልጁን በጥር የዝውውር ጊዜ ለማስፈረም እንደሚፈልጉ ለሲቲወች ነግሮቸዋል።   (done deal)



GUNNERS TARGET JORGINHO

ምሽቱን በወጣ ዜና መድፈኞቹ ከ ብራዚላዊዉ አማካኝ  ጆርጊንሆ ላይ አነጣጥረዉበታል።

የሴሪያዉ ክለብ ናፖሊ አማካኝ የሆነዉ ጆርጊንሆ አርሰናል ባለስልጣናትን እንደሳባቸዉ እየተነገረ ነዉ።

አማካኙን ወደ ኢሜሬትስ በማስኮብለል ለማስፈረም አርሰናል የጥር የዝውውር ጊዜን ወይንም ቀጣዬ ክረምት እየተጠባበቁ ነዉ ሲል marca ዘግቧል።


OTHER SHORT STORIES

አስቶን ቪላ፣ ዌስት ብሮም እና ሌስተር ሲቲዎች የማንቸስተር ዩናይትዱን አምበል ማይክል ካሪክ ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው።   (Source: Daily Mirror)


ኢዲ ኒኪታህ በአርሰናል የሚያቆየውን አዲስ የአምስት አመት ኮንትራት ሲፈራረም ሳምንታዊ ደሞዙን ወደ 650% ጭማሪ ይደረግለታል። (Source: Sun on Sunday)


DEAL DONE: ፌዴሪኮ ፋዚዎ አዲስ የሦስት አመት ኮንትራት በሮማ ፈርሟል። (Source: ASRomaEN)



የማንቸስተር ሲቲው ቤልጂየማዊ አማካይ ኬቨር ዲ ብሪየን አዲሱን ሳምንታዊ £250,000 የሚያስገኝለትን ደሞዝ ሲፈራረም የክለቡ የምንግዜም ከፍተኛው ተከፋይ ተጫዋች ይሆናል።
(Source: Daily Star)


ባርሴሎናዎች ለአትሌቲኮ ማድሪዱ አጥቂ አንቶኔ ጋሬዝማን ዝውውር በክረምቱ የ£89m ሂሳብ ለማቅረብ ዝግጁ ናቸው።   (Source: Mundo Deportivo)



ማንቸስተር ዩናይትዶች ማርከስ ራሽፎርድን ለሪያል ማድሪድ በመሸጥ በምትኩ ማርከስ አሴንሶን ከሎስ ብላንኮዎቹ መውሰድ ይፈልጋል።  (Source: Daily Express)

No comments:

Post a Comment

አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦

Featured Post/ቀጣይ ልጥፍ

የዝውውር ዜናዎች

  ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር...