Wednesday, May 16, 2018

ዕረቡ ከሰአት በኃላ የወጡ የዝውውር ዜናዎችና መረጃዎችን ያንብቡ - Latest Transfer News Update



1. ቸልሲዎች የኒሱን አማካይ ጄን ማይክል ሴሪ ለማስፈረም የሚደረገውን ፉክክር እየመሩ ይገኛሉ ሲል Mirror ዘግቧል፡፡ አርሰናል ልጁን ለማስፈረም ከተጫዋቹ ጋር ተነጋግሮ ነበር፡፡ ይሁንና 40 ሚ. ፓውንድ የተገመተውን ኮትዲቯራዊ ተጫዋች የመውሰድ እድል ያለው ቸልሲ ነው ሲል ዘገባው ደምድሟል፡፡



2. የቶተንሃሙ አሰልጣኝ ሞውሪሲዮ ፖቼቲኖ ከቸልሲ የሚደረገውን ማንኛውም እንቅስቃሴ በማቆም እዛው ቶተንሃም ለመቆየት መወሰኑን Daily Star ዘግቧል፡፡ ከኤፍኤ ዋንጫው መጠናቀቅ በኋላ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ቸልሲን እንደሚለቅ ይጠበቃል፡፡ ቸልሲዎች ደግሞ በሱ ቦታ ፖቼቲኖን ለማምጣ አቅደው ነበር፡፡ ይሁንና በቶተንሃም ደስተኛ የሆነው ፖቼቲኖ እዛው ለመቆየት ወስኗል፡፡



3. ኒውካስትል ዩናይትድ ሁለት የቸልሲ ተጫዋቾችን በውሰት መውሰድ ይፈልጋል፡፡ ተጫዋቾቹም ኬኔዲ እና ታሚ አብራሃም ናቸው፡፡ ኬኔዲ በ2017/18 የውድድር አመት በውሰት ከኒውካስትል ጋር የቆየ ሲሆን ለራፋ ቤኒቴዙ ቡድን ምርጥ እንቅስቃሴ ማድረግ ችሏል፡፡ በዚህ ደስተኛ የሆኑት ራፋ ልጁን ዳግመኛ ወደ ኒውካስትል ማምጣት ይፈልጋሉ፡፡ ሌላኛው ተጫዋች ደግሞ ለስዋንዚ ሲቲ በውሰት ሲጫወት የነበረው ታሚ አብረሃም ነው፡፡ አብረሃም 8 ጎሎችን ለስዋንዚ ያስቆጠረ ሲሆን፣ ኒውካስትሎች እሱንም በውሰት መውሰድ ይፈልጋሉ፡፡ ዘገባው የteamTalk ነው፡፡



4. ሶዩንኩ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መዘዋወር ይፈልጋል፡፡ ለፍራይበርግ የሚጫወተው የ21 አመቱ ተከላካይ ካግላር ሶዩንኮ በበርካታ የአውሮፓ ክለቦች እየተፈለገ ይገኛል፡፡ አርሰናል፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ማንችስተር ሲቲ ልጁን የሚፈልጉ ክለቦች ናቸው፡፡ አርሰናሎች ቱርካዊውን ተከላካይ ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ሲሆን ወኪሉ ግን ከተለያዩ ክለቦች ጋር እየተነጋገረ መሆኑን Football London ዘግቧል፡፡

═════════════════════════
📂  ADVERTISEMENTS

የቴሌግራም ገፃችንን ይጎብኙ:
➧ https://t.me/hair_regrowth
═════════════════════════


5. ኤዲን ሃዛርድ ኮንትራቱን ከማራዘሙ በፊት ክለቡ በዝውውር መስኮቱ የሚደርገውን እንቅስቃሴ ማየት ይፈልጋል ሲል Goal ዘግቧል፡፡ ኤዲን ሀዛርድ ኮንትራቱ በ2020 ነው የሚጠናቀቀው፡፡ ቸልሲዎች ደግሞ ኮንትራቱን ለማራዘም እና በሳምንት እስከ 300 ሺ ፓውንድ ሊከፍሉት አቅደዋል፡፡ ነገር ግን ሀዛርድ ኮንትራቱን ከማራዘሙ በፊት ወደ ክለቡ የሚመጡ ተጫዋቾቸን ማየት እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡ ሀዛርድ  ስለ ወደፊት ሁኔታው ሲጠየቅ ‹‹ምርጥ ተጫዋቾች ወደ ክለቡ እንዲመጡ እፈልጋለው፡፡ ምክንያቱም በቀጣይ አመት ፕሪሚየር ሊጉን ማሸነፍ እፈልጋለሁ›› በሏል፡፡



6. አርሰናል እና ቶተንሃም ሆትስፐር ማሪዮ ሌሚናን ለማስፈረም ተፋጠዋል፡፡ አማካዩ ማሪዮ ሌሚና ባለፈው ክረምት ነበር ከጁቬንቱስ ወደ ሳውዛምፕተን የተዘዋወረው፡፡ ለሳውዛምፕተንም 29 ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል፡፡ የመሃል ሜዳ ክፍላቸውን ማጠናከር የሚፈልጉት ሁለቱ ክለቦች ደግሞ ልጁን ወደ ክለባቸው ለማዘዋወር አቅደዋል፡፡ ኤቨርተን እና ዌስተሃምም ልጁን ይፈልጉታል፡፡ ዘጋበው Footmercato ነው፡፡



7. የሌዚስተር ሲቲው ሃሪ ማጓየር የወደፊት እቅዱን ከአለም ዋንጫው በኋላ እንደሚያስታውቅ ተናግሯል፡፡ የ25 አመቱ ማጓየር ባለፈው ክረምት ወደ ሌዚስተር የተዘዋወረ ሲሆን በመጀመሪያው አመት ምርጥ እንቅስቃሴ ማድረግ ችሏል፡፡ ይህም የበርካታ ክለቦች እይታ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል፡፡ በተለይ ማንችስተር ሲቲ ልጁን ይፈልጋል፡፡ ማጓር ግን ሁሉንም ነገር ከአለም ዋንጫው መጠናቀቅ በኋላ አስታውቃለው ማለቱን Mirror ዘግቧል፡፡



8. ‹‹በየአመቱ 300 ሚ. ፓውንድ ወጪ አናደርግም›› ሲል ፔፕ ጓርዲዮላ ተናገረ፡፡ ሲቲ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በተለያዩ ተጫዋቾች ላይ ወጪ በማድረግ የፐሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ብዙ ሪከርዶችን በመሰበር አንስቷል፡፡ በተጨማሪም የካራባኦ ካፕ ዋጫንም መውሰድ ችሏል፡፡ ስለወዲፊቱ የተጠየቀው ጓርዲዮላ ‹‹አሁን ቡድናችን ጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለው፡፡ ከአንድ ወይም ሁለት ተጫዋች በላይ አናስፈረምም፡፡ በየአመቱ 300 ሚ. ፓውንድ የማውጣት አቅምም የለንም›› ማለቱን Goal ዘግቧል፡፡



9. ሌዚስተር ሲቲ እና ዌስትሃም ዩናይትድ የ21 አመቱን የማንችስተር ሲቲ የክንፍ ተጫዋች ማስፈረም ይፈልጋሉ፡፡ ፓትሪክ ሮበርትስ ባለፉት ሁለት አመታት ለሴልቲክ በውሰት ሲጫወት ከርሟል፡፡ በዚህም ወርም ወደ ሲቲ እንደሚመለስ ይጠበቃል፡፡ ይሁንና የመሰለፍ እድሉ አናሳ በመሆኑ በክለቡ የመቆየቱ ነገር አጠራጣሪ ነው፡፡ ይህን አጋጣሚ በመጠቀምም 15 ሚ. ፓውንድ የተገመተውን ተጫዋች ለመውሰድ ሌዚስተር እና ዌስትሃም ተዘጋጅተዋል ሲል Express ዘግቧል፡፡



10. አትሌቲኮ ማድሪድ የሴልቲኩን ቲርኔይ ለማስፈረም የሚደረገው ፉክክር ተቀላቅሏል፡፡ የ20 አመቱ ወጣት የግራ ተመላላሽ ኬረን ቴርኔይ በዘንድሮው የውድድር አመት ባሳየው ምርጥ ብቃት ምክንያት የበርካታ ክለቦች እይታ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል፡፡ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ቶተንሃም እና ቦርንሞዝ ልጁን በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡ አትሌቲኮ ማድሪድም አሁን ስኮትላንዳዊውን ከሚፈልጉ ክለቦች ውስጥ ሆኗል፡፡ እሁድ እለት ሴልቲክ ከማዘርዌል ጋር የሚደርጉትን የስኮትሽ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ እንዲመለከቱም መለማዮች ለመላቅ ማቀዳቸውን The Sun ዘግቧል፡፡



11. ማንችስተር ዩናይትድ የኖቲንግሃም ፎረስቱን ታዳጊ ማቲው ቦንድስዌል ለማስፈረም ተቃርቧል፡፡ የ16 አመቱ ተመላላሽ በኖቲንግሃም ፎረስት እንዲቆይ ኮንትራት ቢቀርብለትም አልተቀበለውም፡፡ በዚህም ምክንያት ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ሊሄድ ይችላል ሲል Daily Mail ዘግቧል፡፡



12. አልፊ መውሰን እና ፋቢያንስኪ ስዋንዚ ሲቲን ሊለቁ ይችላሉ፡፡ ስዋንዚ ወደ ቻምፒየን ሺፑ መውረዱን ተከትሎ በርካታ ተጫዋቾች ክልቡን ሊለቁ ይችላሉ፡፡ ከነዛ ውስጥ ተከላካዩ አልፊ መውሰን እና ግብ ጠባቂው ፋቢያንስኪ ይገኙበታል፡፡ 20 ሚ. ፓውንድ የተገመተውን መውሰን በዌስትሃም እና ሳውዛምፕተን የሚፈለግ ሲሆን፤ ዋትፎርድ፣ ኒውካስትል፣ ክሪታል ፓላስ እና ዌስተሃም የፋቢያንስኪን ሁኔታ በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡ ዘገባው የThe Guardian ነው፡፡

═════════════════════════
📂  ADVERTISEMENTS

የቴሌግራም ገፃችንን ይጎብኙ:
➧ https://t.me/ethio_bodybuilders
═════════════════════════

No comments:

Post a Comment

አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦

Featured Post/ቀጣይ ልጥፍ

የዝውውር ዜናዎች

  ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር...