Thursday, October 26, 2017

ሃሙስ ምሽት ላይ የወጡ ሠፊ የዝውውር ዜናዎች፣ አስተያየቶች እና ሌሎችም አጫጭር ትኩስ የእግር ኳስ መረጃዎች



¤   የቼሊሲዉ አሰልጣኝ አንቶኒዩ ኮንቴ ታዳጊዉ ተጫዋች ብራዚላዊዉ ቻሪሊን ሞሶንዳን በጥር የዝዉዉር መስኮት ላይ ለሌላ ክለብ አሳልፈዉ ለመስጠት ለሽያጭ አቅርበዉታል ሲል London Evening Standard ዘግቧታል።




¤   ማንችስተር ዩናይትድ የቦርሲያ ዶርትመንዱ አጥቂ ማርኮ ሬዩስን በክለቡ ዶርትመንድ እስከ ፈረንጆች 2019 ያለዉን የኩንትራት ጊዜ በማቆረጥ በጥር የዝውውር መስከት ማስፈረም ይፈልጋሉ ተባለ። ማርኮ ሬዩስ በአሁኑ ሰአት በጉዳት ምክንያት ክለቡን ቦርሲያ ዶርትመንድ እያገለገለ አይደለም።   (star)



¤   VALVERDE TERGETS NEW DEFENDERS


የባርሴሎናዉ አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ አዲስ ተከላካይ ማስፈረም ይፈልጋሉ ተብሎል።

ምክንያቱም የባርሴሎና የተከላካይ ክፍል መዳከሙ እና በተከላካይ ክፍሉ ያሉ ተጫዋቾች አቆም መቀነስ ነዉ ተብሎል።

ቫልቬርዴሜ በአሰልጣኝ ጆሲ ኤኒሬኬ ከተተኩ በሆላ በክረምቱ የዝውውር ጊዜ ሁነኛ ተከላካይ ማስፈረም አልቻሉም። ሁኖም በጥር የዝዉዉር ጊዜ የተከላካይ ክፍላቸዉ ለማጠናከር ብለዉ የግራ መስመር ተመላላሽ የሆነዉን ኢንጎ ማርቲኔዝን  ቀዳሚ የክለባቸዉ ተመራጭ ተጫዋች አድርገዉታል።

ሁኖም ቫልቬርዴ የጥር የተጫዋቾች የዝዉዉር መስኮት ላይ ልጁ ለማስፈረም ከአሁኑ ስራቸዉን ጀምረዋል በማለት፣metro. ጋዜጣ ዘግቧታል።

በተያያዘ ዜና ባርሴሎና በመጪዉ ክረምት ኮሎንቢያዊዉን ተከላካይ ዬርይ ሚናን ለማስፈረም ከልጁ ጋር ንግግር እያደረጉ ነዉ ተባለ።   (metro)


¤   BUFFON'S RETIREMENT PLANS


አንጋፋዉ ጣሊያዊዉ የጁቬንትሱ ግብ ጠባቂ ጁሊጂያን ቡፎን ስለወደፊቱ እቅዱ ተናግሮል።

ቡፎን በአስተያየቱም እንዲህ አለ፦ እኔ በአሁኑ አመት ከክለቤ ጁቬንትስ ጋር ታላቁን ዋንጫ የአዉሮፓ ሻምፒዩንስሊግን የማላነሳ ከሆነ በአሁኑ የ2018 የሩሲያ የአለም ዋንጫ በሆላ እራሴን ከእግር ኮስ አከላለዉ በማለት በባሎንዶር ሽልማት ዝግጅት ላይ በተደረገለት የአጭር ቀለ መጠየቅ አስተያየቱን ሰጦል።

አጋፋዉ ግብ ጠባቂ ቡፎን የተለያዩ ዋንጫወችን ከክለቡ ጁቬንትስ ጋር ቢያነሳም እንኮን ታላቁን ዋንጫ የአዉሮፓ ሻንምፒዩን ስሊግ እስካሁን ማንሳ አልቻለም።

ቡፎን ጨምሮም አምና ከክለቤ ጁቬንትስ ጋር የሴሪያዉን እና የኮፓ ኤታሊያን ዋንጫ በማንሳት ጥሩ ጊዜን አሳልፌለዉ ነገር ግን የሴሪያዉን ዋንጫ ማንሳት ብቻ ለእኔ በቂ አይደለም በማለት ተናግሮል።    (done deal)


¤   REUS: FOUR OR FIVE CLUBS WANT ME


የቦርሲያ ዶርትመንዱ አጥቂ ጀርመናዊዉ ኢንተርናሽናል ማርኮ ሬዩስ በተለያዩ አምስት ክለቦች ይፈለጋል ሲል፣ mirror ዘግቧል።

ከክለቦቹ መካከል አርሰናል፣ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ሪያል ማድሪድ እና በባየር ሙኒክ ይገኙበታል ተብሎል።     (mirror)


¤   LIVERPOOL WILL SELL COUTINHO FOR €150M


ብራዚላዊዉ የሊቨርፑሉ ኮከብ ፊሊፕ ኩቲንዎ ወደ ስፔኑ ሀያል ክለብ ባርሴሎና በጥር መሄዱ እርግጥ መስሎል እየተባለ ነዉ።

የጀርገን ክሎፑ ሊቨርፑል በተጨዋቹ ላይ ያለዉ እምነት መቀነሱ ታዉቆል። ምክንያቱም በክረምቱ የዝዉዉር ጊዜ ኮንቲኒሆ ወደ ባርሴሎና መሄድ
እንሚፈልግ በግልፅ መናገሩ እና ብራዚል በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ ጎል ካገባ በሆላ ማልቀሱ ወደ ባርሴሎና የመሄድ ፍላጎቱ ከፍተኛ እንደሆነ መታወቁ ልጁ ባርሳን በጥር መቀላቀሉ አይቀርም ሲባል መቆየቱ ይታወቃል።

ሁኖም ባርሴሎና አሁን ኮንቲኒሆን በ150 million እናስፈርም ሊሉት ተዘጋጅተዋል በማለት የስፔኑ ታማኝ ጋዜጣ mundov deportivo ዘግቧል።

በመሆኑም ሌላኛዉ የማስፈረም ፍላጎት ያለዉ ፒኤሲጂ ኮንቲኒሆን ልቀቁልን በማለት ለባርሴሎና ነግሮቸዋል ሲል mundov deportivo አክሎ ዘግቧል።


¤   ማንችስተር ዩናይትድ ተዘጋጅተዋል በ£30 million የቫሌንሴዉን ካርሎስ ሶሌርን ለማስፈረም ሲል the Sun ዘገበ። ካርሎስ በእንግሊዙ ሀያል ክለብ መፈለጉ ቫሌንሴወች ልጁ ማጣታቸዉ አይቀርም ተብሎል። ምክንያቱም ካርሎስ ወደ እንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ መጦ የመጫወት ፍላጎት ስላለዉ ነው።


¤   ARSENAL WANT TO KEEP OZIL AND ALEXIS




የሰሜን የለንደኑ ክለብ አርሰናል ሁለቱን ኮከቦች ሜሴት ኦዚል እና አሌክሲ ሳንቸዝን በኢምረተስ ለማቆየት ከአሁኑ ድርድር ሊያደርግ ነዉ።

ሁለቱ ተጫዋቾች ባሳለፍነዉ ሳምንት አርሰናል ኤቨርተንን በሜዳዉ ጉዲሰን ፓርክ አስተናግዶ 5፣2 ባሸነፈበት ጨዋታ ሁለቱም በጨዋታዉ ላይ አንዳንድ ጎል አስቆጥረዋል።

በመሆኑም ሁለቱ ኮከቦቹ ለክለባቸዉ ያላቸዉን ወሳኝነት በጨዋታዉ ላይ አሳይተዋል።
አርሰናሎችም ሁለቱን ተጫዋቾች ለማቆየት የማይፈነቅሉት ዲንጋይ የለም ተብሎል።
(daily mirror)


¤   DRAXLER TO LIVERPOOL?



ሊቨርፑል በጥር ፊሌፔን ኮንቲኒሆን የሚያጣ ከሆነ በምትኩ ጀርመናዊዉን ኢንተርናሽናል የፒኤሲጂዉን አማካኝ ጁሊያን ድራስለርን ያስፈርማሉ ተብሎል።
የመሀል ሞተሩ ድራክስለር በፒኤስጂ በቂ ቦታ እያገኘ አለመሆኑ ክለቡን ሊለቅ ይችላል ተብሎል።

ጀርመናዊዉ ኮከብ በሀገሩ ሰዉ በሆነዉ አሰልጣኝ ጀርገን ክሎፕ መሰልጠን እንደሚፈልግ ከዚህ በፊት ተናግሮ። ክሎፕ ልጁን በጥር የዝዉዉር ጊዜ
ለማምጣት ከአሁኑ በቅርበት ሁነዉ እየተከታተሉት እንደሆነ የዜናዉ አዉታሩ daily star ዘግቧል።


¤   COUTINHO WANTS JANUARY MOVE




አሁን አመሻሽ በወጣ ሌላ ዜና ደግሞ የካታሎኑ ክለብ ባርሴሎና ከሊቨርፑል ጋር በብራዚላዊዉ ኮከብ ፊሊፕ ኮንቲኒሆ የዝዉዉር ጉዳይ ላይ ስምምነት ሊያደርግ ነዉ ተባለ።

ጨዋታ አቀጣጣዩ ፊሊፕ ኮንቲኒሆ በጥር ወደ ሚፈልግበት ክለብ እንዲሄድ አሰልጣኝ ጀርገ ክሎፕ ነግረዉታል ተብሎል። ኮከቡ በስፔኑ ሀያል ክለብ ባርሴሎና የእናስፈርምህ ጥያቄ ከተጠየቀ ሰነባብቶል። በዚህም ባርሴሎና አሁን ልጁ ለማግኘት በሊቨርፑል የተጠየቁትን አዲስ የዝውውር ሂሳብ በማቅረብ ሊስማሙ ይችላሉ ሲል bbc ዘግቧል።

ፀሃፊ፦ ሙሴ አማረ
አዘጋጅ እና አርታኢ፦ መንግስቱ ደሳለኝ

No comments:

Post a Comment

አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦

Featured Post/ቀጣይ ልጥፍ

የዝውውር ዜናዎች

  ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር...