1. ፔግ ጓርዲዮላ ከቶኒ ክሩስ ጋር ዳግመኛ መገናኘት ይፈልጋል ሲል Don Balon አስነብቧል፡፡ ማንችስተር ዩናይትዶች ለረጅም ጊዜ ክሩስን ወደ ኦልትራፎርድ ለማዘዋወር ሲፈልጉ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ማንችስተር ሲቲዎች እጃቸውን ለማስገባት እየሞከሩ ነው፡፡ ጓርዲዮላ እና ክሩስ በባየር ሙኒክ አብረው ሰርተው ነበር፡፡
2. ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ አምስተ ተጫዋቾችን መሸጥ ይፈልጋል፡፡ የቶተንሃሙ አሰልጣኝ የቡድኑ መሪ ዳኒ ሌቪ የደሞዝ መዋቅሩን በማስቀተካከል ኮከብ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ እንዲያመጣለት ይፈልጋል፡፡ በከፍተኛ ገንዘብ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ደግሞ ቡድኑ ውስጥ ያሉትን አምስት ተጫዋቾች ለመሸኘት ወስኗል፡፡ ቶቢ አልደርዌልድ፣ ዳኒ ሮዝ፣ ሙሳ ዴምቤሌ፣ ፈርናንዶ ሎሬንቴ እና ሙሳ ሲሶኮ እንደሸጡ የተወሰነባቸው አምስት ተጫዋቾች መሆናቸውን Mirror ዘግቧል፡፡
3. ቸልሲዎች አንቶኒዮ ኮንቴን የሚያባርሩት ከሆን እሱን ጨምሮ ለዘጠኝ ስታፎች የውል ማፍረሻ ካሳ ለመክፈል ይገደዳሉ፡፡ ቸልሲ ከአንቶኒዮ ኮንቴ ጋር ለመለያየት ካሰቡ የኮንቴን የአንድ አመት ደሞዝ ለመክፈል ይገደዳሉ፡፡ ነገረ ግን ክፍያው እዛ ጋ አያበቃም፡፡ አንቶኒዮ ኮንቴ ከጣሊያን ያመጧቸው ሌላ 8 ረዳቶቹም ይከፈላቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ በቻምፒየንስ ሊጉ መሳተፍ ያልቻለው እና እስከ 50 ሚ. ፓውንድ ገቢ ላጣው ቸልሲ ትልቅ ራስ ምታት መሆኑን Daily Mail ዘግቧል፡፡
4. ፔፕ ጓርዲዮላ የቡዱኑ አካላት የዊልፍድ ዛሃን ሁኔታ እንዲከታተሉ ጠየቀ፡፡ ዛሃ ባለፈው እሁድ ለጋዜጠኞች በሰጠው መልስ ‹‹እኔ ቤቴ ነው ያለሁት ከቤቴ ደግሚ የትም መሄደ አልፈልግ›› ብሏል፡፡ ይሁንና ዛሃ ሀሳቡን የሚቀይር ከሆነ ጓርዲዮላ 50 ሚ. ፓውንድ በመክፈል ልጁን ወደ ኢቲሃድ ማዘዋወር ይፈልጋል ሲል Daily Star ዘግቧል፡፡
5. ቸልሲዎች የቶተንሃሙን አሰልየጣኝ ፖቸቲኖ ይፈልጋሉ ሲል Sun ዘግቧል፡፡ የቶተንሃሙ አሰልጣኝ ሞሪሲዮ ፖቼቲኖ እና የቡደኑ መሪ ዳኒ ሌቪ በዝውውር ጉዳይ ላይ ቅሬታ ውስጥ ገብተዋል፡፡ ፖቼቲኖ ተጫዋቾች እዲገዙለት ይፈልጋል፡፡ ሌቪ ግን እስካሁን ምላሽ አልሰጠውም፡፡ ይህ የማይሳካ ከሆነ ደግሞ ክለቡ ለመልቀቅ ይገደዳል፡፡ ቸልሲል ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ፖቸቲኖን ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ ለማምጣት አቅዷል፡፡
═════════════════════════
📂 ADVERTISEMENTS
የቴሌግራም ገፃችንን ይጎብኙ:
➧ https://t.me/hair_regrowth
═════════════════════════
6. የፕሪሚየር ሊጉ የዝውውር መስኮት ከተለመደው ቀን ቀደም ብሎ ሊከፈት ነው፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ የዝውውር መስኮት ከዚህ በፊት ጁን 1 ነበር የሚከፈተው፡፡ ይህ የዝውውር መስኮት ደግሞ የሚዘጋው ኦገስት 31 ነው፡፡ ይህም ማለት ፕሪሚየር ሊጉ ከተጀመረ በኋላ ነው የሚሆን፡፡ ይሁንና በዚህ የዝውውር አመት የዝውውር መስኮቱን ፕሪሚየር ሊጉ ከመጀመሩ በፊት ኦገስት 9 ለይ ለመዝጋት ወስነዋል፡፡ ስለዚህ አስቀድሞው ለመከፍት በመሰናቸው ከቀጣዩ ሀሙስ ሜይ 17 ጀምሮ የዝውውር መስኮቱ በእንግሊዝ ክፍት ይሆናል፡፡ (Sky Sports News)
7. ቦካ ጁኒየርሶች ዴቪድ ኦስፒናን የፍልጉታል፡፡ አርሰናሎች በዚህ የዝውውር መስኮት ግብ ጠባቂ ለማስፈረም እንደሚንቀሳቀሱ ይጠበቃል፡፡ የባየር ሊቨርኩሰኑ ቤርንድ ሌኖን ጨምሮ በርካታ ግብ ጠባቂዎች ስማቸው ከአርሰናል ጋር በመያያዝ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም ምክንያት የኦስፒና በአርሰናል የመቆየት ጉዳይ አጠራጣሪ እየሆነ ነው፡፡ ቦካዎችም ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ኮሎምቢያዊውን ግብ ጠባቂ ወደ አርጀንቲና ማምጣት ይፈልጋሉ፡፡ ዘገባው የSun ነው፡፡
8. ዌስትሃም ዩናይትዶች ከሻክታር ዶኔትስኩ አሰልጣኝ ፓውሎ ፌንሴካ ጋር ተነጋግረዋል ሲል Daily Mail አስነብቧል፡፡ የፎንሴካ ወኪል የሆነው ሆርጌ ሜንዴዝ ሰኞ እለት ከዌስትሃሙ ሊቀምነበር ዴቪድ ሱሊቫን ጋር Essex በሚገኘው ቤቱ በመገናኘት ተነጋግሯል፡፡ ዌስትሃሞች ከፎንሴካ በተጨማሪ የቀድሞውን የማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝ ማኑዌል ፔሌግሪኒንም ይፈልጋሉ፡፡ ይሁንና ፎንሴካ ወጣት በመሆኑ ወደሱ ማድላታቸውን ዘገባው አክሎ አስፍሯል፡፡
9. የኤቨርተኑ አሰልጣኝ ሳም አላርዳይስ በ48 ሰዓታት ውስጥ ከአሰልጣኝነት ሊባረሩ ይችላሉ፡፡ በኤቨርተን ከፍተኛ ሼር ያለው ባለሀብቱ ፈርሃድ ሞሺሪ ከአላርዳይስ ጋር በመገናኘት ከስራ መባረሩን ይነግረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በቦታው ደግሞ ከዋትፎርድ የተባረረው ሲልቫ እንደሚመጣ ይጠበቃል፡፡ የኤቨርተን ደጋፊዎች በአላርዳይስ የጨዋታ ዘይቤ ደስተኛ አለመሆናቸው እና ተቃውሞ ማሰማታቸው ለመባረራቸው ምክንያት እንደሆነ The Guardian አስነብቧል፡፡
10. ማንችስተር ዩናይትዶች ለናፖሊው የቀኝ ተመላላሽ ኤልሰዒድ ሀይሳጅ የውል ማፍረሻ የሆነውን 44 ሚ. ፓውንድ ለመክፈል መዘጋጀታቸውን Sun ዘግቧል፡፡ ዩናይትዶች በዚህ የዝውውር መስኮት የቀኝ እና የግራ ተመላላሽ የማስፈረም ፍላጎት አላቸው፡፡ አልባኒያዊው የ24 አመት ተጨዋችም ይሆን ቦታ እንዲሸፍን ወደ ኦልትፎረድ ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ተጫዋቹ የሚፈርም ከሆነ 7ኛው ወዱ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ይሆናል፡፡
═════════════════════════
📂 ADVERTISEMENTS
የቴሌግራም ገፃችንን ይጎብኙ:
➧ https://t.me/ethio_bodybuilders
═════════════════════════



No comments:
Post a Comment
አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦