Friday, December 8, 2017

አርብ ምሽት ላይ የወጡ ሠፊ የዝውውር ዜናዎች አስተያየቶች እና ሌሎችም አጫጭር ትኩስ የእግር ኳስ መረጃዎችን ያንብቡ - Latest Transfer News Update



የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ዚኔዲን ዚዳን በጥር  የዝውውሩ መስኮት ላይ አዲስ ግብ ጠባቂዉን ወደ ክለባቸዉ ማዘዋወር እንደሚፈልጉ ተነግሮል።
(Source: Daily Express)


በተያያዘ ዜና ሪያል ማድሪድ ዳቪድ ደያን ከማንንችስተር ዩናይትድ ለማስፈረም የማይፈነቅሉት ዲንጋይ የለም ተብሎል። ዛዳንም በጥር ሁለት ግብ ጠባቂወችን ማስፈረም መፈለጋቸዉ ተከትሎ ዋነኛዉ እና አንደኛዉ ኢላማቸዉ ደግሞ ዳቪድ ዴያ ነዉ ተብሎል።   (Source: MEN)


የእንግሊዙ ክለብ ወልብርሃምተን የቤኔፊካዉን አማካኝ ጆኦ ካርቫልሆን በ€15 million ለማስፈረም እየተመለከቱት ነዉ ተባለ። (Source: Birmingham Mail)


የባርሴሎናዉ ኮከብ አርጀንቲናዊዉ  ምትሀተኛ ሊዩነል ሜሲ እግር ኮስን በልጅነት ክለቤ ኒዌልስ ኦልድ ቦይ መጨረስ እንደሚፈልግ ተናግሮል።  (Source: Daily Express)


የፕሪሜር ሊጉ ክለብ ብራይተን በ£20m
 የዝውውር ሂሳብ በጥር የሴልቲኩን አጥቂ ሙሳ ዴምቤሌን ማስፈረም ይፈልጋሉ ሲል፣ (Source: Daily Mail) አስነብቧል።


አርሰናሎች ኮከባቸዉን ሜሲት ኦዚልን በክለቡ ለማቆየት ሲሉ አዲስ እና የተሻሻለ ኩንትራት ሊያቀርቡለት እንደሆነ እየተዘገበ ነዉ። በዚህም በተያያዘ እንዲሁም አሌክሲ ሳንቸዝን  በጥሩ ክለቡን ከመልቀቁ በፊት አዲስ ኩንትራት በማስፈረም በክለባቸዉ ማቆየት ይፈልጋሉ ተብሎል። (Source: Sun Sport)


ጀርገን ክለፕ ብራዚላዊዉን ኮከባቸዉን ፊሊፕ ኮንቲኒሆን በጥር ወር ለመሸጥ ሊገደዱ ይችላሉ ተብሎ። ምክንያቱ ደግሞ ኮንቲኒሆ በክለቡ መቆየት አለመፈለጉ እና በስፔኑ ሀያል ክለብ ባርሴሎና በጥብቅ መፈለጉ ነዉ ተብሎል። (Source: Daily Star)


የሻልክ 04ቱ አማካይ ሊዮን ጎረትዝከ ስሙ በተደጋጋሚ ግዜ ከአርሰናል እና ማንቸስተር ዩናይትድ  ዝውውር ጋር ሲነሳ ቢቆይም በጥር የዝውውርችመስኮት ላይ ወዴትኛው ክለብ እንደሚያመራ ውሳኔ አሳልፋለሁ ሲል ተናግሮአል።
(Mail)


የሳምንቱን ታላቅ ጨዋታ ማን.ዩናይትድ Vs ማን.ሲቲ  ሠፋ ያለ ቅድመ ዳሰሳ ነገ ይጠብቁን!


የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ፖርቹጋላዊዉ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የ2017 የባላንዶር ሽልማት ለ5ኛ ጊዜ አሸነፈ። ሮናልዶም በባሎንዶር ሽልማት ታሪክ 946 ድምፅ አግኝቶ በማሸነፍ አዲስ ታሪክ አፅፎል። ሮናልዶ የባላንዶር ሽልማቱን 5 ጊዜ በማሸነፍ ከተቀናቀኙ ሊዩነል ሜሲ ጋር እኩል ሆኖል። (bbc). ሙሉ 30ውም የባለንደዎር ተጭዋቾች ዝርዝር የሚከተለው ነው። ደረጃው የተሰጣቸውን ነጥብ መሰረት ያደረገ ነው። = ምልክት ያለበት በሁለት ተጭዋቾች በጋራ የተያዘ ደረጃ ነው። (Ballon d'Or top 30 voting) ...


29= Philippe Coutinho
29= Dries Mertens
28. Edin Dzeko
27. Mats Hummels
26. Jan Oblak
25. Karim Benzema
24. Radamel Falcao
23. Sadio Mane
21= Leonardo Bonucci
21= Pierre-Emerick Aubameyang
20. David de Gea
19. Eden Hazard
18. Antonio Griezmann
17. Toni Kroos
16. Marcelo
15. Paulo Dybala
14. Kevin de Bruyne
13. Luis Suarez
12. Isco
11. Cavani
10. Harry Kane
9. Robert Lewandowski
8. N'Golo Kante
7. Kylian Mbappe
6. Sergio Ramos
5. Luka Modric
4. Guanluigi Buffon
3. Neymar
2. Lionel Messi
1. Cristiano Ronaldo

No comments:

Post a Comment

አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦

Featured Post/ቀጣይ ልጥፍ

የዝውውር ዜናዎች

  ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር...