MAN UTD TO MAKE ANOTHER RUN
AT BALE
ማንቸስተር ዩናይትዶች ለሦስተኛ ግዜ የሪያል ማድሪዱን አጥቂ ጋሬዝ ቤልን ለማዛወር ጥረት ያደርጋሉ ያለን the Mirror ጋዜጣ ነው።
እንደ ሪፖርቱ ዘገባ ከሆነ ሪያል ማድሪዶች በጋሬዝ ቤል ተደጋጋሚ ጉዳት የተማረሩ ሲሆን ማን.ዩናይትዶች በበኩላቸው ደግሞ ጆዜ ሞሪንዎ ዌልሳዊውን አማካይ ወደ እንግሊዝ በመመለስ የቀድሞ አካል ብቃቱ ላይ እንደሚመልሱት እምነት አላቸው።
ያም ሆኖ ማን.ዩናይትዶች የላ ሊጋው ክለብ ለዝውውሩ እየጠየቀ ያለውን የ£85 million ሂሳብ የማስቀነስ ተልእኮ ያለባቸው ሲሆን የቤል ኮንትራት እስከ 2022 ድረስ የሚቆይ ይሆናል።
MAN UTD TO MAKE JANUARY MOVE FOR ROSE
ጆዜ ሞሪንዎ የቶተንሃሙን ግራ ተመላላሽ ተከላካይ ዳኒ ሮዝን በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ በማዘዋወር ወደ ኦልትራፎርድ ሊያመጡት ይፈልጋሉ ሲል The Sun አስነብቧል።
ሮስ ለረጅም ጊዜያቶች ያህል ወደ ኦልትራፎርድ ይዛወራል በሚል በተደጋጋሚ ሲወራበት የቆየ ሲሆን ሪፖርቱ አክሎ እንደዘገበው ከሆነ ሮስ ወደ ቀያይ ሰይጣኖቹ የመዛቀር ፍላጎት አለው።
ቶተንሃሞች ተጭዋቹን እንዲለቁት ማሳመን የዩናይትዶች ተቀዳሚ ተግባር የሚሆን ሲሆን ዩናይትዶች ስፐርሶችን ለማለስለስ ሉክ ሾውን የዝውውሩ አካል በማድረግ ሊያቀርቡት ይችላሉ።
OZIL IS BARCA'S COUTINHO BACK-UP
ባርሴሎናዎች የፊሊፕ ኩቲንዎ ዝውውር የማይሳካላቸው ከሆነ ፊታቸውን ወደ አርሰናሉ አማካይ ሜሱት ኦዚል ለማዞር በተጠባባቂነት መያዛቸውን Mundo Deportivo ዘገበ።
የሊቨርፑሉ ኮከብ ኩቲንዎን በክረምት ለማዛወር ያደረጉት ተደጋጋሚ ጥረት ከከሸፈባቸው በኃላ በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ የካታላኑ ክለብ የዝውውር ኢላማ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ሆኖም ሊቨርፑሎች አሁንም ተጭዋቹን ላለመልቀቅ የያዙትን አቋም የቀጠሉበት ሲሆን ዝውውሩ የማይሳካ ከሆነ ባርሴሎናዎች በእርሱ ምትክ በክረምቱ ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን ሜሱት ኦዚልን በቅናሽ ዋጋ ከአርሰናል ለማዛወር ጥረት ያደርጋሉ።
BARCA TRACKING LYON MIDFIELDER
ባርሴሎናዎች የሊዮኑን አማካይ ሉካስ ቱሳልት በዚህ የውድድር አመት ላይ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በቅርበት እየተከታተሉት ይገኛሉ ሲል Mundo
Deportivo ዘገበ።
ቱሳርት በክረምቱ ክለቡን የለቀቀውን ኮሬንቲን ቶሊሶን በመተካት መታየት የጀመረ ሲሆን በዚህ አመት ያደረጋቸውን በርካታ ጨዋታዎች ብዙ የባርሴሎና ቁልፍ ሰዎች በአካል በመሄድ ተመልክተውታል።
ARSENAL SCOUT BORO WINGER
አርሰናሎች የሚድልስቦሮውን ታዳጊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ማርከስ ታቬርኒየርን ለማዛወር የሙከራ ግዜ ሰጥተውታል ሲል Daily Mail ዘገበ።
ታቨርኒየር በቅርቡ ቡድኑ ከሰንደርላንድ ጋር ሲጫወት የማሸነፊያውን ጎል ያስቆጠረ ሲሆን የእንግሊዙ ከ19 አመት በታች ተጫዋች በኤቨርተን ፣ በርንማውዝ እና አስቶን ቪላም ጭምር እየተከታተሉት ይገኛል።
BARCA MAKE FEKIR CONTACT
ባርሴሎናዎች አርሰናሎች ለሊዮኑ አማካይ ናቢል ፌከር ዝውውር ጥያቄ አቀረቡ የሚል ወሬ መሰማቱን ተከትሎ ተጭዋቹን እንዳይቀሙ ከተጭዋቹ ወኪሎች ጋር ንግግር ማድረግ ጀምረዋል ሲል Sport ዘገበ።
ፌከር በዚህ አመት እያሳየ ያለውን ምርጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ የአርሰናሎች ተቀዳሚ የዝውውር ኢላማ የሆነ ሲሆን ሪያል ማድሪዶችም መልማዮቻቸውን ልከው ተመልክተውታል።
ይሄም ሆኖ ባርሴሎናዎች ፌከርን በሌላ ክለብ ላለመነጠቅ በሚል ከወዲሁ በዝውውሩ ዙሪያ በጥልቀት በመንቀሳቀስ ጥያቄ ለማቅረብ የተሰናዱ ሲሆን በጃቸው ማስገባት ከፈለጉ ለዝውውሩ ከ €50 million በላይ መክፈል ይኖርባቸዋል ተብሏል።
ታላቅ ቅናሽ - በአዲስ አበባ (መገናኛ እና ሳሪስ) ፣ ሀዋሳ፣ አዳማ፣ ጂማ፣ ሽሬ፣ ደብረ ማርቆስ፣ መቀሌ፣ ሀረር፣ ጎንደር እና ደሴ ከተማ ነዋሪ ነዎት? እንግዲያውስ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናቶች ቅዳሜ እና እሁድ ብቻ የአይቴል S11 እና S31 ስልኮችን በታላቅ ቅናሽ ይግዙ! እንዲሁም ሲገዙ ልዩ ስጦታዎች ከአይቴል ሞባይል እዚያው ይውሰዱ! ለበለጠ መረጃ የፌስቡክ ገፃችንን ይጎብኙ ፦ www.facebook.com/itelMobileEthiopia/
MOURINHO PLOTS LUIZ SWOOP
የማንቸስተር ዩናይትዱ አለቃ ጆዜ ሞሪንዎ የቼልሲውን መሃል ተከላካይ ዴቪድ ሉዊዝ በማዛወር በድጋሚ አብረውት መስራት ይፈልጋሉ ሲል Express ዘገበ።
የቀድሞው የቼልሲ አለቃ የብራዚላዊው ተጭዋችን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተሉት ያሉ ሲሆን ተጭዋቹ ከዩናይትድ ጋር በነበረው ጨዋታ ላይ ከቡድኑ ውጪ ከተደረገ በኃላ ሁኔታውን እየተከታተሉት ይገኛል።
ሉዊዝ ከቼልሲው አለቃ አንቶኒዮ ኮንቴ ጋር ቡድኑ በቻምፒየንስ ሊጉ በሮማ ሰፊ በሆነ የ3ለ0 ውጤት ከተሸነፈ በኃላ ግጭት ውስጥ መግባታቸው የሚታወስ ነው።