Sunday, November 12, 2017

እሁድ ምሽት ላይ የወጡ በርካታ አጫጭር እና ሠፋ ያሉ የዝውውር ጭምጭምታዎች፣ ዜናዎች፣ አስተያየቶች እና ሌሎችም ትኩስ የእግር ኳስ መረጃዎች




ARSENAL WANT ZAHA TO REPLACE
SANCHEZ


የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ለኮከባቸዉ ለአሌክሲስ ሳንቼዝ ተተኪ ይሆናል ያሉትን የክሪስታል ፓላሱን የአጥቂ መስመር ተሰላፊ አይቬሪኮስታዊዉን
ዊልፍሪድ ዛሃ እንደ አማራጭ ይዘውታል፡፡


የቺሊያዊው የአሌክስ ሳንቸዝ ኩንትራት በሚቀጥለው አመት የሚጠናቀቅ መሆኑን ተከትሎ አርሰን
ቬንገር ለአይቬሪኮስታዊው ኢንተርናሽናል £35
million አዘጋጅተዋል፡፡


ዛሃ በፓላስ ጥሩ ብቃቱን እያሳየ መሆኑ ተከትሎ አርሰኖሎች ሳንቸዝ ወደ ማን ሲቲ መሄዱ ካልቀረ ተጫዋቹን ማስፈረማቸዉ አይቀርም ተብሎል።
(The star)


BARCA TURNED DOWN AUBAMEYANG


ባርሴሎናዎች በክረምቱ የዝውውር መስኮት የቦርሺያ ዶርትመንዱን አጥቂ ጋቦናዊዉን ፔሬ ኤምሪክ ኦበምያንግ የማስፈረም እድል ቀርቦላቸው ነበር፡፡


ነገር ግን ኔይማር ፒኤስጂን መቀላቀሉን ተከትሎ የካታላኑ ክለብ ኦበምያንግን ለማስፈረም አማራጭ የቀረበለት ቢሆንም የ9 ቁጥር ቦታው በሉይስ ስዋሬዝ መያዙን ተከትሎ ሳያስፈርሙት ቀርተዋል፡፡


ሁኖም ባርሴሎና የሊዉስ ስዋሬዝ ብቃት መዉረድን ተከትሎ በጥር ተጫዋቹን በድጋሜ የእናስፈርም ጥያቄ ሊያቀርቡለት ይችላሉ ተብሎል።  (Mundo Deportivo).


CHELSEA EYEING UP €100M ICARDI


ቼልሲዎች በጥር የዝውውር መስኮት ላይ
የኢንተር ሚላን ማውሮ ኢካርዲ የጠየቀውን የ€100 million የውል ማፍረሻ ለመክፈል ተዘጋጅተዋል ተብሎል፡፡


አርጀንቲናዊው አጥቂ በጣሊያን ክለብ ኢንተር ሚላን ጥሩ አቋም እያሳየ ሲሆን 11 ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፎአል፡፡


ቼልሲም የአጥቂ ክፍሉን ለማጠናከር ሲል ተጫዋቹን ሊያስፈርመዉ እንደሚችሉ የተለያዩ ሚዲያወች እየዘገቡ ነዉ።    (daily mirror)


JUVENTUS PLOTTING BELLERIN BID


የአምናዉ የጣሊያን ሴሪያዉ ሻንምፒዩኑ ክለብ ጁቬንትስ የአርሰናሉን ሁለገብ ተጫዋች የሆነዉን ስፔናዊዉን ወጣት ሄክቶር ቤለሪን ደጎስ ባለ የዝውውር ሂሳብ ለማዘዋወር አስበዋል።


ቤሌሪን በአርሰናል ጥሩ የሚባል ብቃት ላይ ይገኛል። በዚህም በተለያዩ ክለቦች አይን ዉስጥ መግባት ችሎል። ሁኖም ተጫዋቹ በክለቡ አርሰናል የመቆየቱ ነገር አሳሳቢ ነዉ ተብሎል ሲል tuttomercato ዘግቧል።


OTHER SHORT STORIES 


ሪያል ማድሪዶች በዌልሳዊዉ ጋሬዝ ቤል የጉዳት ችግሮች ምክንያት ተስፋ ቆርጠዋል ተብሎል፡፡
በዚህም ተጫዋቹን ለፈላጊ ክለቦቹ ለሆኑት፦
ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ቼልሲ ወይም ቶተንሃም
አሳልፈዉ ሊሰጡት ይችላሉ ተብሎል፡፡
(Mirror)


የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ተጫዋች የሆነዉ አማካኙ ኤምሪ ቻን ከጁቬንቱስ የሚቀርብለትን ጥያቄ በማስተባበል የሊጉን ተቀናቃኝ ማንቸስተር ሲቲ ሊቀላቀል ይችላል፡፡


ጀርመናዊው ኢንተርናሽናል ኩንትራቱ በሚቀጥለው
ክረምት የሚጠናቀቅ ሲሆን በነጻ የፔፕ ጋርዴወላዉን ክለብ ማን ሲቲ የመቀላቀል እድል ይኖረዋል ተብሎል፡፡ (mirror)


ቀያይ ሰይጣኖቹ ማንቸስተር ዩናይትዶች የ29 አመቱን ቤልጄማዊዉን አማካይ ማርዋን ፌላይኒ በጥሩ የዝውውር መስኮት ለቤኪሽታሽ በ£8m ለመሸጥ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ተብሎል፡፡ ፌላይኒ በአሁኑ ሰአት በጉዳት ላይ ይገኛል።     (Mirror)


የካታሎኑ ክለብ ባርሴሎና በጥር የዝውውር መስኮት ላይ በቀዳሚነት የአያክሳምስተርዳሙን ተከላካይ ማቲያስ ዲላይት ለማስፈረም ከአሁኑ ንግግር ሊያደርግ ነዉ፡፡የካታላኑ ክለብ ከጄራርድ ፒኬ ጋር ይመሳሰላል የሚባልለትን የ18 አመቱን ወጣት ለማስፈረም እየተመለከተ ቢሆንም ዳቪንሰን ሳንቼዝን ለቶተንሃም የለቀቀው አያክስ ተከላካዩን በቀላል ለባርሴሎና አሳልፎ ይሰጣል ተብሎ አይጠበቅም ተብሎል፡፡     (Mundo Deportivo)


ሪያል ማድሪዶች ብራዚላዊውን የፒኤስጂ አጥቂ ኔይማር በሚቀጥለው ክረምት የማስፈረም
እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡    (Marca)


በተያያዘ ዜና ኔይማር ሀገሩ ብራዚል ጃፓንን 3-1 ባሸነፈችበት የወዳጅነት ጨዋታ ላይ የምሳ ግብዣዉ ላይ ባልታወቀ ምክንያት አልታደመም ተብሎል። (indepedent)


የሌስተር ሲቲዉ ተጫዋች የሆነዉ ዴማራይ ግራይ የበፊቶቹን አሰልጣኞች የሆኑትን አሰልጣኝ ክላዉዲወ ራኔሪ እና ክሬድ ሼክስፔርን እንዲመለሱ እፈልጋለሁኝ ሲል ለፎክስ ገልፆል። (sky)

No comments:

Post a Comment

አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦

Featured Post/ቀጣይ ልጥፍ

የዝውውር ዜናዎች

  ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር...