Wednesday, November 8, 2017

ዕሮብ ምሽት ላይ የወጡ በርካታ አጫጭር እና ሠፋ ያሉ የዝውውር ዜናዎች፣ አስተያየቶች እና ሌሎችም ትኩስ የእግር ኳስ መረጃዎች

P
MAN UTD WON'T RECALL PEREIRA እንደ Superdeporte ሪፖርት ከሆነ ቫሌንሺያዎች በውሰት ከማንቸስተር ዩናይትድ የወሰዱት አማካይ አንድሪያስ ፔሬራ በእናት ክለቡ በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ እንደማይወሰድባቸው ተማምነዋል ብሏል። ዩናይትዶች ልጁን በውሰት ሲሰጡት ውሉ ላይ ከፈለጉት በጥር የመውሰድ መብትን ያካተቱበት ቢሆንም ቫሌንሺያዎች በላሊጋው ጥሩ ብቃት እያሳየላቸው የሚገኘውን የክንፍ ተጫዋች ዩናይትዶች መልሰው እንደማይወስዱባቸው ተስፋ አድርገዋል።
MOU TOLD TO SELL BEFORE BUYING ጆዜ ሞሪንዎ በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ አዳዲስ ተጫቾችን ማዛቀር የሚፈልግ ከሆነ በቅድሚያ በቡድኑ ውስጥ ያሉ አላስፈላጊ ተጭዋቾችን መሸጥ እንዳለበት በክለቡ ተነግሮአቸዋል ሲል የዘገበው BBC ነው። የኦልትራፎርዱ ክለብ የሰሞዝ ክፍያ ጣሪያ ከባለፈው አመት በ13.5% ጭማሮ እንዳሳየ የፋይናንስ ሪፖርቶች የጠቆሙ ሲሆን የክለቡ ቦርድ አዳዲስ ተጭዋቾች ቡድኑን ከመቀላቀላቸው በፊት የደሞዝ ወጪ ቢሉ አሁን ካለበት እንዲወርድ ይፈልጋሉ። ሪፖርቱ አክሎ እንደገለፀው ከሆነ በ2014 የዝውውር መስኮት ላይ በ£27 million ሂሳብ ቀያዮቹ ሰይጣኖችን የተቀላቀለው ሉክ ሾው ክለቡን የሚለቅ የመጀመሪያው ተጭዋች ይሆናል።
MADRID LINE UP MATA BID ሪያል ማድሪዶች የማንቸስተር ዩናይትዱን አማካይ ዩሃን ማታ በጥር የዝውውር መስኮት ላይ ለማስፈረም ጥያቄ ያቀርባሉ ሲል Express ጋዜጣ ዘገበ። ማታ ቡድኑ ባደረጋቸው የቅርብ ጨዋታዎቹ ላይ ቋሚ ተሰላፊ መሆን ያልቻለ ሲሆን ኮንትራቱ በዚህ ክረምት ላይ የሚጠናቀቅ በመሆኑ ዩናይትዶች በነፃ ዝውውር በሲዝኑ መጨረሻ ላይ ከሚለቅባቸው በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ በመሸጥ ከ29 አመቱ ስፔናዊ ዝውውር ገንዘብ ሊያገኙበት ይፈልጋሉ ተብሏል። ማታ በማድሪድ ታዳጊዎች ሲስተም ውስጥ ሰልጥኞ ያለፈ ተጫዋች ሲሆን ወደ ልጅነት አሳዳጊው ክለብ በርናባው መመለስን ይፈልግ ይሆናል ሲክ ዘገባው አካሏል።
BARCA PLAN JANUARY CLEAR OUT ባርሴሎናወች ተዘጋጅተዋል በጥር 3 ተጫዋቾች ለመሸጥ። ባርሴሎና በአሁኑ ሰአት በጉዳት ምክንያት ክለቡን እያገለገለ እማይገኘዉን አርዳ ቱራን በጥር ለሌላ ክለብ ለመሸጥ አስበዋል። እንዱሁም አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ሌሎኞችን ቶማስ ቨልማሪን እና አሌክስ ቪዳል ለመሸጥ ማሰባቸዉን ገልፀዋል። ቫልቬርዴም ሁለቱን ቪዳልን እና ቨርማሊን የመሸጡ ምክንያት የተባለዉ ደግሞ በክረምቱ ያስፈረሙት ፖርቹጋላዊዉ ኔልሰን ሲሞዲ እና ጥሩ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘዉ ስፔናዊዉ ሰርጆ ሮቤርቶ ቦታቸዉ መያዙ ነዉ ተብሎል። በዚህም 3 ተጫዋቾች ካፕኑን ለቀዉ መሄዳቸዉ አይቀርም ተብሎል። (the Sun)
DE LIGT TOPS BARCA WISHLIST ባርሴሎና የ18 አመቱን የአያክስ አምስተርዳሙን ተከላካይ ማቲጅስ ዲሊጊትን በቀጣዩ ክረምት ለማስፈረም አስበዋል። ሪፖርቱ ሙንዶቭ ዲፖርቲቮ እንዳለዉ ከሆነ ታዳኒዉን ተጫዋች ለማስፈረም ባርሴሎና የልጁን እንቅስቃሴ ከስር ከስር የተከታተሉት ነው ተብሎል። በተያያዘ ዜና ባርሴሎና የፖላ ሜራዉን ወጣት ተጫዋች ዩሪይ ሚናን ወደ ላ ሊጋዉ ለማምጣት ማሰባቸዉን ጋዜጣው ጨምሮ ዘግቦታል። (mundov deportivo)
Sponsored By
PSG TO SELL £70M DUO IN JANUARY የፈረንሳዩ ሀብታም ክለብ ፒኤሲጂ ከመግዛት ወደ መሸጥ ተዘዋዉሮል። ፖሪሴንት ጀርሜን አርጀንቲናዊዉ አጥቂ አንጂል ዲ ዲማሪያን እና ብራዚላዊዉ ሉካስ ሞራን በ€70 million የዝውውር ሂሳብ በጥር የዝውውር መስኮት ለመሸጥ ተዘጋጅቶል ተብሎል። የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤሲጂዎች ቅርብ ሰው እንዳለዉ ከሆነ ሁለቱ ተጫዋቾች በመጠነኛ እና በተመሳሳይ ዋጋ ለመሸጥ እንዳሰቡ ተናግረዋል። ሁኖም ሁለቱ ተጫዋቾች በትልልቅ ክለቦች ይፈለጋሉ በዚም የጨዋታ አቀጣጣዩ አንጅል ዲ ማሪያ በስፔኑ ሀያል ክለብ ባርሴሎና በጥብቅ ይፈለጋል ተብሎል። አርጀንቲናዊዉ በክረምቱ ለባርሴሎና ይፈርማል ቢባልም ሳይፈርም መቅረቱ ይታወሳል። ሁኖም አሁን በድጋሜ ዲማሪያም በጥር ወር የካታሎኑን ባርሴሎና ይቀላቀላል ተብሎ ይታሰባል። ሌላኛዉ ብራዚላዊዉ ኮከብ ሉካስ ሞራ በክለቡ በተደጋጋሚ ቦታ ማግኘት አልችል ብሎ ቆይቶል። ሁኖም ሉካስ በጥር ሰማዩችን ቼልሲወችን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል ሲል Sky sport ዘግቧል።
OZIL DEMANDS WILSHERE'S NO.10 SHIRT ሜሲት ኦዚል በአርሰናል ቤት እንድቆይ ከፈለጋቹህ የጃክ ዉሊሼርን 10 ቁጥር መለያ ማሊያ ስጡኝ ብሎል። የ10 ቁጥርን መለያ ማይሰጡት ከሆነ ክለቡን እለቃለሁኝ ብሎል። ካለበለዚያ ጀርመናዊዉ ኢንተርናሽናል አርሰናልን ለቅቄ ወደ ማንችስተር ዩናይትድን በመቀላቀል የ10 ቁጥር መለያ አገኛለሁኝ ሲል ለክለቡ ሰዎች ነግሮአቸዋል ተብሎል። ኦዚል እስከ ሲዝኑ መጨረሻ በአርሰናል አዲስ ኩንትራት የማይፈርም ከሆነ ፍላይ ኤምሬትስን ለቆ ማንችስተር ዩናይትድን መቀላቀሉ አይቀርም ተብሎል። (daily mail)  
ፀሐፊ፦ ሙሴ አማረ አዘጋጅና አርታኢ፦ መንግስቱ ደሳለኝ

No comments:

Post a Comment

አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦

Featured Post/ቀጣይ ልጥፍ

የዝውውር ዜናዎች

  ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር...