REAL OFFER BALE & KROOS FOR NEYMAR
የሪያል ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ የፒ.ኤስ.ጂውን አጥቂ ኔይማር በክረምቱ ለማዛወር የቆረጡ ሲሆን በምትኩ ለፓሪሱ ክለብ ቶኒ ክሮስን እና ጋሬዝ ቤልን ለመስጠት አቅደዋል ያለው Don Balon ነው።
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ ብራዚላዊውን ኮከብ አሁን ላይ ለማዛወር ባጠቃላይ የ€400 million, ሂሳብ የሚያስፈልግ ሲሆን ሪያሎች ግን ቤል እና ክሮስን በመስጠት ዋጋውን ለማውረድ አስበዋል።
ባሁኑ ሰአት PSGዎች ተጭዋቹን የመሸጥ ምንም አይነት ፍላጎት የላቸውም ሆኖም ማድሪዶች ተጭዋቹን በቀጣዮቹ ሁለት ሲዝኖች ውስጥ ለማዛወር ቆርጠዋል።
MADRID TARGET LYON STAR
የሊዮኑ አጥቂ ንምቢ ኪየታ በሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ተቀዳሚ የዝውውር ኢላምን መሆን ችሏል ያለው ደግሞ SFR Sport ነው በAS በኩል።
ፌከር በዚህ የውድድር አመት ላይ በሊዮን ድንቅ ብቃቱን ያሳየ ሲሆን የ24 አመቱ ፈረንሳዊ ኢንተርናሽናል እንደ አጥቂም እንደ አማካይ አጥቂም ሆኖ መጫወት ይችላል። በባርሴሎናም መልማዮች ታይቷል።
አርሰናሎች፣ ጁቬንቱስ እና ማንቸስተር ዩናይትዶችም በፌከር ዝውውር ላይ ፍላጎት ያላቸው ሲሆን ሆኖም ግን ማድሪዶች በዚህ አመት እያሳየ ያለውን እንቅስቃሴ በአካል እየተከታተሉት ይገኛሉ።
BARCA TO RAISE UMTITI RELEASE CLAUSE TO €180M
ባርሴሎናዎች በማንቸስተር ዩናይትድ በጥብቅ እየተፈለገ ያለውን ተከላካይ ሳሙኤል ኡምቲትን በ2018 አመት መጀመሪያ ላይ አዲስ የተሻሻለ ኮንትራት ለማስፈረም አቅደዋል ሲል Sport ዘገበ።
የኡምቲት ባርሴሎና ኮንትራት የሚጠናቀቀው በ2021 ላይ ሲሆን በአመት የ€3 million ደሞዝ እየተከፈለው ይገኛል። በኮንትራቱ ላይ የ€60m ውል ማፍረሻም ተቀምጦአል።
በአዲሱ ኮንትራቱ ደሞዙን ለማሳደግ የታሰበ ሲሆን በዋነኛነት ከፈላጊ ክለቡ ማን.ዩናይትዶችን ለማሸሽ ሲባል አዲስ የ€180m ሂሳብ ውል ማፍረሻ ለማካተት ታቅዷል።
BARCA MIDFIELDER SET FOR NEW
DEAL
ባርሴሎናዎች አማካያቸውን ሰርጂ ሮቤርቶ አዲስ የአምስት አመት ኮንትራት ለማስፈረም እና ፈላጊ ክለቦቹን ሁለቱን የማንቸስተር ከተማ ክለቦች ሲቲ እና ዩናይትድ ለማሸሽ አቅደዋል ሲል Mundo Deportivo ዘገበ።
የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ሰርጂ ሮቤርቶን ማዛወር ይፈልጋሉ በሚል ስማቸው ከተጭዋቹ ዝውውር ጋር በተደጋጋሚ ግዜ ሲነሳ ቢቆይም የተጭዋቹ ውል የሚያበቃው በ2019 ላይ ነው።
ያም ሆኖ ግን የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦችን ለማሸሽ ባርሴሎናዎች ለተጭዋቹ አዲስ ኮንትራት ውል አቅርበው የውል ማፍረሻ ሂሳቡን ከ€40 million ሂሳብ ወደ €400m ሂሳብ ማሳደግ ይፈልጋሉ።
GORETZKA WANTS PREMIER LEAGUE
MOVE
የሻልካው አማካይ ሊዮን ጎረትስካ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች መዛወር የሚፈልግ ሲሆን በቀጣዩ አመት ከኮንትራቱ ሙሉ ለሙሉ ነፃ ይሆናል ብሏል Sport .
ጀርመናዊው ኢንተርናሽናል ቡድን አሰልጣኝ የሆኑት ኦሊቨር ቤይሮፍ እንዳሉት ከሆነ የእንግሊዝ ክለቦች እያቀረቡ ያሉት የዝውውር እና የደሞዝ ክፍያዎች የትኛውንም ተጭዋች ልብ የሚያሸፍቱ መሆናቸውን አምነው ተጭዋቹ የሪያል ማድሪድ ፤ ባርሴሎና እና ባየር ሙኒክ የዝውውር ኢላማ እንደሆነ ዘግበዋል።
ያም ሆኖ የ22 አመቱ ተጫዋች ከስፔን እና ከጀርመን ሃያል ክለቦች እየቀረቡለት ያለውን ጥያቄ ያልተቀበላቸው ሲሆን ፍላጎቱ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መዛወር ብቻ ነው ተብሏል። አርሰናል፤ ቶተንሃም፤ ሊቨርፑል እና ቼልሲ ከተጭዋቹ ዝውውር ጋር ስማቸው የተነሱ ክለቦች ናቸው።
MAN UTD TO SELL SHAW FOR £20M
ማንቸስተር ዩናይትዶች ሉክ ሾውን በ20ሚ.ፓ ሂሳብ ብቻ በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ ሊለቁት ፍቃደኞች ናቸው ብሏል የTimes ነው።
ሻው በቅርቡ ወደ ፌነርባቼ ቱርክ ሊያመራ ነው በሚል ሲወራበት የቆየ ሲሆን እርሱ ክን ወደ ኢስታምቡሉ ክለብ መዛወርን አይፈልግም። ዩናይትዶች ግን ግራ ተመላላሽ ተከላካዩን በቅናሽ የዝውውር ሂሳብ ለማዛወር ለመልቀቅ ፍቃደኞች ናቸው። ተከላካዩ እያሳየ ያለው ብቃት ጆዜ ሞሪንዎን አላሳመናቸውም ተብሏል።
CAN TO SNUB JUVE FOR CITY
ሊቨርፑሎች አማካያቸው ኤምሬ ካን የጣሊያኑን ክለብ ጁቬንቱስ ጥያቄ ችላ በማለት ወደ እንሊዙ ማንቸስተር ሲቲ ለመዛወር አስቧል ያለው Star ነው።
ጀርመናዊው ኢንተርናሽናል ካን በጁን ወር ላይ ከሊቨርፑል ኮንትራቱ ሙሉ ለሙሉ ነፃ ሲሆን ጁቬንቱሶች በነፃ የዝውውር ሂሳብ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ላይ ለማዛወር በጥር ወር ላይ ከስምምነት እንደርሳለን የሚል ተስፋ ነበራቸው።
ሆኖም ጀርመናዊው ተጭዋች ካን ሊቨርፑል እና ጁቬንትስን ጥያቄ ችላ በማለት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መሪ ክለብ ማንቸስተር ሲቲ እንደሚያቀና ጠርጥረዋል።


No comments:
Post a Comment
አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦