አይቴል ሞባይል ለስድስተኛ ጌዜ የትምህርት መርጃ መሳርያዎችን በደብረ ማርቆስ ከተማ ድጋፍ አደረገ!!!!
አይቴል ሞባይል በትላንትናው ለት ማለትም ጥቅምት 28 2010 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ በአዲስ ሕይወት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ291 ተማሪዎች የትምህርት መርጃ መሳርያዎችን ድጋፍ አድርጎአል።
አይቴል ሞባይል ይህን ፕሮግራም ሲያዘጋጅ በያዝበዉ አመት ብቻ ለስድስተኛ ጌዜ ሲሆን ይህ ሰናይ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ስንገልፅ በደስታ ነዉ፡፡ አይቴል ሞባይል በተመሳሳይ ሁኔታ በባሕር ዳር፣ ሐዋሳ፣ ጎንደር፣ ኮምቦልቻ፣ መቀሌ እና አዲስ አበባ (ሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር) በሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የትምህርት መርጃ መሳርያዎችን ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ነዉ፡፡
በዚህ ተግባሩ አይቴል ሞባይል ሁሌም የማህበረሰቡ አንድ አካል መሆኑን እያሳየ ይገኛል። ከዚህ በፊት አይቴል ሞባይል ኢትዮጵያ ጥቅምት 14 2010 ዓ.ም የሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበርን በመጎብኘት የተለያዩ ስጦታዎችን ቦታው ድረስ በመሄድ የትምህርት መሳርያ መርጃ ቁሳቁስ ለ305 ተማሪዎችና መምህራን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን አይቴል ሞባይል በያዝነዉ ወር 10ኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ ደግሞ በአማራ ክልል በሚገኙት ከተሞች በጎንደር፣ ባህር ዳር እና ኮምቦልቻ ከተሞች ተመሳሳይ የበጎ አድራጎት ስራዎችን መስራቱ የሚታወስ ነዉ።
አይቴል ሞባይል ኢትዮጵያ በየሳምንቱ የሚደረጉ የተለያዩ አውሮፓ ሊጎችን ትላልቅ ጨዋታዎች እያስገመተች ለትክክለኛ ገማቾች ሽልማት ታበረክታለች።
አይቴል ሞባይል ኢትዮጵያ በተለያዩ የሃገሪቷ ክፍሎች ለችግረኛ ተማሪዎ የደብተር ፣ መፅሃፍትና መማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጋለች ፤ ወደፊትም ታደርጋለች።
እርስዎም የአይቴል ቤተሰብ ይሁኑና ይሸለሙ!
እርስዎም በአይቴል አዳዲስ ሞዴል የሞባይል ምርቶች ህይወትዎን ፣ አኗኗርዎን እና ስራዎን ቀለል እያደረጉ የአይቴል ቤተሰቦችን /Itel Family/ በተለያዩ ማህበራዊ ገፆቻችን በኩል በመቀላቀል አባል በመሆን ከሽልማቶቻችን ፤ ከበጎ አድራጎታችን ገፀ በረከቶች ተቋዳሽ ይሆኑ ዘንድ እየጋበዝን።
ከታች የሚገኘውን የitel mobile ገፃችንን ፌስቡክ ገፃችንን Like አድርገው በመቀላቀል በየሳምንቱ የሚደረጉ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ግምት በማስቀመጥ ከሽልማቶቻችን ከስጦታዎቻችን ተካፋይ መሆን ይችላሉ..
👉 www.facebook.com/itelmobile




No comments:
Post a Comment
አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦