ሜሱት ኦዚል በአርሰናል የመቆየቱ ነገር አጠራጣሪ እየሆነ መጥቷል። ተጭዋቹ ቡድኑ ከሜዳ ውጪ በሚያደርገው ጨዋታዎች ላይ ቤንች ላይ መቀመጡ አላስደሰተውም።
ኡናይ ኤምሬ በበኩላቸው ቡድኑ ከኢንተርናሽናል እረፍት በፊት ከክሪስታል ፓላስ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ ነጥብ ሲጥል ለቡድኑ ባደረገው አስተዋፅዎ ደስተኛ አይደሉም። ከዛም በበርንማውዙ ጨዋታ ላይ ተጠባባቂ አድርገውታል። ተጭዋቹ ኢምሬትስን የሚለቅ ከሆነ ማን.ዩናይትዶች አማካዩን የማዛወር የተሻ እድል አላቸው። (ምንጭ፦ johncrossmirror)
.
ማንቸስተር ሲቲዎች የፖርቹጋሉን የ21 አመት ብሄራዊ ቡድን ተጭዋች ስቴፈን ኢውስታኪዮ ለማዛወር እየተከታተሉት ነው። ለቼቫስ የሚጫወተው ባለተሰጥዎ በባርሴሎና፣ ሪያል ቤቲስ እና ስፖርቲንግም ጭምር ይፈለጋል። ኮንትራቱ ላይ የ£13.3m ውል ማፍረሻ አለው። (ምንጭ፦ Daily Mail)
.
ጋላታሳራዮች የሊቨርፑሎቹን አጥቂ ዶሚኒክ ሶላንኬ እና ዲቮክ ኦርጂን የማዛወር እንቅስቃሴ ጀምረዋል።
(ምንጭ፦ Daily Mirror)
.
ኦስማን ዴምቤሌይ ለባርሴሎና ክለብ አመራሮች የጥር የዝውውር መስኮት ከመከፈቱ በፊት ከክለቡ እንዲለቁት መወትወቱን ቀጥሎበታል። ስሙ ከአርሰናል ዝውውር ጋር መያያዙን ተከትሎ በጥር ክለቡን መልቀቅ ይፈልጋል። (ምንጭ፦ Daily Mail)
.
ኤሲ ሚላኖች የቼልሲውን እና የእንግሊዙን ኢንተርናሽናል መሃል ተከላካይ ጋሪ ካሂል እንዲያስፈርሙት ቀርቦላቸው ሳይቀበሉት ቀርተዋል።
(ምንጭ፦ Calciomercato)
.
ማንቸስተር ዩናይትዶች የቦሩሲያ ዶርትመንዱን አማካይ አክስል ዊትሰል መከታተላቸውን አሁንም ቀጥለውበታል። ምንም እንኳን ክለቡ በክረምቱ ብራዚላዊውን አማካይ ፍሬድ ቢያዛውርም ሞሪንዎ አሁንም የአማካይ ክፍሉ ችግር እንዳልተቀረፈ ተረድተውታል። (ምንጭ፦ Daily Star)
.
የቀድሞው የአርሰናል አለቃ አርሰን ዌንገር ወደ አሰልጣኝነት ስራቸው መመለስ የሚፈልጉ ሲሆን ኒኮ ኮቫችን ለማሰናበት የተዘጋጁት ባየር ሙኒኮች ፈረንሳዊውን አሰልጣኝ ቀጣዩ የቡድናቸው አለቃ አድርገው ሊሾሙአቸው እያጤኑበት ነው ተብሏል።
(ምንጭ፦ Telegraph)
.
የቀድሞው እንግሊዛዊ ኢንተርናሽናል አሽሊ ኮል በአሜሪካው የ MLS ሊግ ክለብ LA Galaxy ተለቋል። (ምንጭ፦ LAGalaxy)
.
ጎንዛሎ ሂጉዌይን ቼልሲን የመቀላቀል ፍላጎት አለው። አርጀንቲናዊው አጥቂ በናፖሊ ከማውሪዚዮ ሳሪ ጋር አንድ ላይ የሰራ ሲሆን በድጋሚ የለንደኑን ክለብ ተቀላቅሎ ከአሰልጣኙ ጋር በድጋሚ መስራት ይፈልጋል። (ምንጭ፦ Corriere dello Sport)
.
ኔይማር እና ክለቡ PSGዎች ብራዚላዊው ኮከብ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ላይ ለዝውውሩ የ€200 ሚሊዮን ዩሮ ሂሳብ የሚቀርብላቸው ከሆነ ወደ ላ ሊጋው እንዲዛወር ፍቃዳቸውን እንደሚሰጡት ከወዲሁ ቅድመ ስምምነት ቃል ገብተውለታል። (ምንጭ፦ Betevé)
.
ሪያል ማድሪዶች የጁቬንቱሱን ፓብሎ ዳይባላ ለማዛወር የነበራቸውን ምኞች እንደማይሳካ ተስፋ አስቆርጧቸዋል። ከእርሱ ይልቅ በክረምቱ ብራዚላዊውን ኮከብ ኔይማር ወደ በርናባው ለማዛወር ሙከራ ለማድረግ ወስነዋል።
(ምንጭ፦ Calciomercato)
.
የቼልሲው የፊት መስመር ተሰላፊ ኤዲን ሃዛርድ ወደ ፈረንሳዩ ክለብ PSG ይዛወራል መባሉን አስተባበለ። ሆኖም የ27 አመቱ ቤልጂየማዊ ኮከብ በክረምቱ ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ፍንጭ ሰትቷል።
(ምንጭ፦ Canal+)
.
ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃሞች የሳምፕዶሪያውን የ22 አመት ተከላካይ ጃኪም አንደርሰን ሁኔታ በቅርበት በመከታተል ላይ ናቸው። (ምንጭ፦ Daily Mirror)
.
Official: ማይክ ዲን የፊታችን እሁድ የሚደረገውን ተጠባቂ የለንደ ደርቢ አርሰናል እና ቶተንሃም ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በመሃል ዳኝነት እንደሚመሩት FAው አሳውቋል።
.
አርሰንልን ሲጫውቱ ክለቡ የውጤት ድርቅ ይመታዋል የሚባልላቸው እና ከቀድሞው የአርሰናል አለቃ አርሰን ዌንገር ጋር በተደጋጋሚ ውዝግብ ውስጥ ሲገቡ የታዩት ዳኛ ማይክ ዲን በአንድ ወቅት ከቬንገር ጋር ስለፈጠሩት ዱላ ቀረሽ ግብግብ ተጠይቀው፦
"ከጨዋታው በኃላ ወደኔ ሲመጣ ለዱላ ተጋብዞ በንዴት መንፈስ ነበር። ጣቶቹን ወደኔ እየጠቆመ ደጋግሞ 'አንተ ታማኝ ዳኛ አይደለህም' ሲል ይናገረኝ ነበር። 'ስለዚህ አጭበርባሪ ነህ እያልከኝ ነው?' ስል መለስኩለት። 'አሁንም እደግመዋለው አንተን ላምንህ አልችልም በፍፁም' ሲል በድጋሚ መለሰልኝ"
"ከዛም 'እንደዚህ ጨዋታዎች ላይ ስትበድለን ዛሬ የመጀመሪያህ አይደለም፤ ሁልግዜም ትበድለናለህ፤ አንተኮ ፕሮፌሽናል ዳኛ መሆን ይጠበቅብሃል። አንተ ክብረ ቢስ የሆንክ ዳኛ ነህ' ሲል ወረደብኝ። በመሃል የዌስብሮም የሜዳ ላይ ኦፊሰሮች በነሃላችን ገብተው ካለሁበት የስቴዲየሙ ክፍል ይዘውት ወጡ" - ሲል ምን ያህል ከፈረንሳዊው አለቃ ጋር ያን ወቅት ዱላ ቀረሽ ለሆነ ፀብ ተቃርበው እንደነበር ተናግሯል።
(ምንጭ፦ TheSun)
.
በርካታ የአውሮፓ ክለቦች ሊቨርፑል፣ አርሰናል እና ማንቸስተር ሲቲን ጨምሮ የሊዮኑን አማካይ ታንጋይ ንዶምቤሌይን ሁኔታ በቅርበት ሆነው በመከታተል ላይ ናቸው። ተጭዋቹ የ £55 million ዋጋ ያወጣል ተብሏል። (ምንጭ፦ Anfieldhq)
.
ሊቨርፑሎች ክሪስቲያን ፑሊሲችን ከቦሩሲያ ዶርትመንድ በ£70 million ፓውንድ ሂሳብ ሊያዛውሩት ይችላሉ። ሆኖም። አሜሪካዊውን አማካይ ማስፈረም የሚችሉት በ2019 የዝውውር መስኮት ላይ ብቻ ከሆነ ነው። (ምንጭ፦ LiverpoolEco)
.
ማንቸስተር ሲቲዎች በበኩላቸው አሌክሳንደር ዚቺንኮን በጥር የዝውውር መስኮት ላይ ለመሸጥ የነበራቸውን እቅድ ሙሉ ለሙሉ ሰርዘውታል። ይሄ የሆነው ቤንጃሚን ሜንዲ ጉዳት ስላጋጠመው ነው።
(ምንጭ፦ TelegraphDucker)
.
ሪያል ማድሪዶች በጥር የዝውውር መስኮት ላይ የማን.ሲቲውን ተፈላጊ ባለተሰጥዎ አማካይ ብራሂም ዲያዝን ለማዛወር ሙከራ ያደርጋሉ። ለዝውውሩ ከፍተኛ ችግር እንደሚገጥማቸው ይረዱታል። በጥር የማይሳካላቸው ከሆነ ግን በክረምቱ ኮንትራቱ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ያዛውሩታል። ተጭዋቹ በክረምቱ ወደ በርናባው ለማምራት ቅድመ ስምምነት ላይ ደርሷል ተብሏል። (ምንጭ፦ ellarguero)
.
ሜሱት ኦዚል ሳይጠበቅ አርሰናልን ሊለቅ ይችላል የሚሉ ወሬዎች መሰማት ጀምረዋል። ኤምሬትስን ከለቀቀ ማን.ዩናይትድ አማካዩን የማዛወር የተሻለ እድል አላቸው ተብሏል። (ምንጭ፦ Express)
.
ሞዬስ : "በኔ ዘመን ቶኒ ክሩስ ወደ ማን.ዩናይትድ ለመምጣት ሙሉ ለሙሉ ተስማምቶ ነበር። ከነ ባለቤቱ አግኝቼው በግል ተነጋግረን ነበር። ባየር ሙኒክ እያለ ወደ ዩናይትድ ለመምጣት በሁሉም ነገር ላይ ከስምምነት ደርሰን ነበር።" (ምንጭ፦ Bild)
.
ያፕ ሄንኪንሰን በባየር ሙኒክ እየተከሰተ ስላለው የቡድኑ ቀውስ ዝምታቸውን ሰብልረዋል:
"በቡድኑ ውስጥ መልአክ የሆኑ እና ሰይጣን የሆኑ ሁለት አይነት ሰዎች አሉ። በጉዳት ሳቢያ የማይጫወቱ ደግሞ የቡድኑ ቁልፍ ተችዋቾችም አሉ። በክለቡ አናት ላይ የተከመረ ትልቅ የችግር ተራራ ይገኛል።" - ሲል አስገራሚ ምላሽ ሙኒክ ላይ ሰጥተዋል። (ምንጭ፦ Westdeutsche Zeitung)