Tuesday, November 6, 2018

ማንቸስተር ዩናይትድ እና ባርሴሎና በሮናልዶ ዝውውር ተፋጠዋል



UNITED LAUNCH RONALDO BID

.

ማንቸስተር ዩናይትዶች የቤኔፊካ ታዳጊ ባለተሰጥዎ ሮናልዶ ካማራ ለማዛወር ከባርሴሎናዎች ጋር አንገት ላንገት ተናንቀዋል። የ15 አመቱ ባለተሰጥዎ ለቤኔፊካ ታዳጊ ቡድን በድንቅ አቋምና እንቅስቃሴ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች የእናዛውርህ ጥያቄ እየቀረበለት ይገኛል።

MANCHESTER UNITED ማንቸስተር ዩናይትዶችም ፖርቹጋላዊው ሌላኛው መጤ ታዳጊ ባለተሰጥዎ ተጭዋች ለማዛወር እንቅስቃሴ ላይ ናቸው ሲሉ በርካታ ሪፖርቶች ጠቁመዋል።

ከስፖርቲንግ ሊዝበን ትልቁን ክርስቲያኖ ሮናልዶ ካዛወሩት ከ15 አመታት በኃላ ቀያይ ሰይጣኖቹ ሌላኛውን ደግመው ለመውሰድ አልመዋል።

እንደ ፖርቹጋሉ ተነባቢ ጋዜጣ እትም Record , ገለፃ ከሆነ የቤኔፊካው ባለተሰጥዎ ሮናልዶ ካማራ ታዳጊ ቡድኑ ባደረጋቸው በUefa Youth League ጨዋታዎች በሙሉ አስደናቂ ሆኑአል።

በጃንዋሪ 2003 ላይ የተወለደው ታዳጊ ክርስቲያኖ ወደ ኦልትራፎርድ ከመዛወሩ ከሰባት ወራት በፊት ነው የተወለደው። እስከ ጁላይ ወር 2015 ድረስም የስፓርቲንግ ሊዝበን አካዳሚ ቡድን አባል ሆኖ ነበር። ከዛም ወደ ተቀናቃኛቸው ቤኔፊካ ተዛወረ።

የአማካይ አጥቂው ለፖርቹጋል ከ17 አመት በታች ቡድን አባል ቢሆንም የጊኒ ቢዛዋን ቡድን የመወከል መብትም ባለቤት ነው።

ተጭዋቹ ከእርሱ በ2 አመታት ከሚበልጡት ታዳጊዎችም ጋር ተጫውቶ ከኳስ ጋር ድንቅ እንቅስቃሴን በማድረግ የበርካቶችን ቀልብ የገዛ ሲሆን ማን.ዩናይትዶች ታዳጊውን ለማዛወር ከበርካታ ታላላቅ ክለቦች ጋር ፉክክር ማድረግ ይኖርባቸዋል።

ካማራ በቤኔፊካ እስከ 2020 ድረስ የሚያቆየው ውል ያለው ሲሆን ወሰ 16 አመት የልደት በአሉን ከማክበሩ በፊት ግን በርካታ ክለቦች ትኩረት አድርገው እየተከታተሉት ይገኛሉ። 16 አመት ከሞላው በኃላ ለፈለገው የአውሮፓ ክለብ የመፈረም ሙሉ መብት ይኖረዋል።

ባርሴሎናዎችም ከፈላጊ ክለቦቹ መሃከል አንዱ ሲሆኑ ከነርሱ በተጨማሪም ቼልሲዎች እና ማንቸስተር ሲቲዎች ባለፈው አመት ከተጭዋቹ ዝውውር ጋር ስማቸው የተነሱ ክለቦች ነበሩ።

No comments:

Post a Comment

አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦

Featured Post/ቀጣይ ልጥፍ

የዝውውር ዜናዎች

  ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር...