JOSE MOURINHO ከማንቸስተር ዩናይትድ መንበራቸው የሚሰናበቱበት ወቅት በግልፅ ተቀምጧል።
አሰልጣኙ በዚህ የውድድር አመት ላይ ቡድኑን ለቻምፒየንስ ሊጉ ውድድር ካላበቁት ይሰናበታሉ።
ዩናይትዶች ባሁን ሰአት በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ 8ተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። በደርቢው ጨዋታ ከተሸነፉ በኃላ ደግሞ ከመሪው ማን.ሲቲ ደግምም በ12 ነጥብ እርቀዋል።
በቀጣዩ የውድድር አመት ቡድኑ በቻምፒየንስ ሊግ የማይሳተፍ ከሆነ ሞሪንዎ መሰናበቱ እርግጥ ነው። የኦልትራፎርዱ ክለብ አሁንም ሞሪሲዮ ፖቼቲንዎን ከልብ ያደንቃሉ። ሆኖም አርጀንቲናዊው አለቃ በቶተንሃም በፈረመው ውስብስብ ኮንትራት ሳቢያ ክለቡን የመልቀቅ እና ቀያዮቹን የመቀላቀል እድሉ የጠበበ እንዲሆን አድርጎታል።
ሁለቱም ማንቸስተር ዩናይትድ እና ሪያል ማድሪድ አርጀንቲናዊውን አለቃ ለማምጣት በጥብቅ ይፈልጋሉ ሆኖም የስፐርሱ አስተዳዳሪ ዳንኤል ሌቪ አሰልጣኙን ሞሪሲዎ ፖቸቲንዎ ላለመነጠቅ የማያደርገው ነገር አይኖርም።
ማድሪዶች ጊዜያዊ አሰልጣኝ ያደረጉት ሳንቲያጎ ሶላሪ ለአራት ተከታታይ ጨዋታዎች ካሸነፉ በኃላ የክለቡ ቋሚ አሰልጣኝ በማድረግ የሁለት አመት ኮንትራት ሰጥተውት ቋሚ አሰልጣኝ አድርገውታል።
ሆኖም ሶላሪ የቀድሞው የአርጀንቲና ቡድን አጋሩ ፖች በክረምቱ በቶተንሃሞች የሚለቀቁ ከሆነ ቦታውን ለሃገሩ ልጅ አስረክቦ ለመነሳት አያቅማማም።
ሞሪንዎ ባለፈው አመት ላይ በኦልትራፎርድ የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት የተፈራረመው ባለፈው አመት ላይ ነው። ሆኖም እርሱን ለማሰናበት ክለቡ መክፈል የሚጠበቅበት ሂሳብ የአመት ደሞዙ የሆነውን የ£15m ሂሳብ ብቻ ነው።
የቀድሞው የቼልሲ አለቃ ጆዜ ሞሪንዎ ቡድኑን ይበልጥ ለማጠናከር ከቅርብ ጎረቤት ተቀናቃኛቸው ማን.ሲቲ እኩል በዝውውር እንቅስቃሴው በቂ ሂሳብ ክለቡ ማውጣት እንዳለበት በመናገር ቅሬታቸውን ገልፀው ነበር።
እንዲሁም መረጃው እንዳለው ፖርቹጋላዊው በክለቡ ስታንዳርዶች ላይ ጥያቄ ማንሳታቸው የሚታወቅ ሲሆን ለቅርብ ጔደኞቻቸው እንዳሉት ከሆነ ሁሉም ነገር በክለቡ 'ሁለተኛ ደረጃ' የሚሰጠው ነው።
ሞሪንዎ በክለቡ የተጭዋቾች ምልመላ ላይ እና የምልመላው ኔትዎርክ ላይ ጥያቄ ያላቸው ሲሆን ክለቡ ትልልቅ ተጭዋቾችን ለማዛወር የሚጠቀምባቸው የድርድር ስልቶትም ለሞሪንዎ የማይዋጡላቸው ኃላ ቀር መንገዶች ናቸው።
እንዲሁን በክለቡ የጉዞ አሬንጅመንቶች ላይ በተለይ ለቻምፒየንስ ሊጉ ከጁቬንቱስ እና ቫሌንሺያ ጋር ከመጫወቱ በፊት ቡድኑ በተደጋጋሚ በመዘግየት ለቅጣት መዳረጉ ሞሪንዎ ጥያቄ ያነሱበት ጉዳይ ነው።
ምንም እንኳን የክለቡ አስተዳዳሪዎች በቅርቡ ቡድኑ በሊጉ ላይ ያሳየውን መሻሻል በመደገፍ ድጋፋቸውን ለጆዜ የሰጡ ቢሆንም የቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ግን ምንም ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም።

No comments:
Post a Comment
አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦