Saturday, November 10, 2018

ዕለተ እሁድ በሳምንቱ መጨረሻ የወጡ አዳዲስ ከ30 በላይ የዝውውር እና ሌሎችም ዜናዎች


➣ ፖል ፖግባ እና ሮሚዮ ሉካኩ ከዛሬው የማንቸስተር ደርቢ ጨዋታ በፊት ለጨዋታው ብቁ መሆን አለመሆናቸውን የአካል ብቃት ምርመራ ያደርጋሉ።   [Mail]

.

➣ የአያክሱ መሃል ተከላካይ ማቲያስ ዲ ሊዥት ወደ ጁቬንቱስ ለመዛወር ሲል ከማንቸስተር ሲቲ እና ከባርሴሎና የቀረቡለትን ጥያቄዎች ውድቅ ለማድረግ ዝግጁ ነው።  (Calciomercato)

.

➣ ጆዜ ሞሪንዎ: "ሉካኩ ዝግጁ ነኝ ካለ የምፈልገው ያንን ነው። የቡድኑ መልሶ ማገገም አባላትም እየሰሩልኝ ያሉት በዚህ ዙሪያ ነው"  [Mail]

.

➣ ስፔናዊው የማንቸስተር ዩናይትድ አማካይ ዩሃን ማታ በክረምቱ የተጭዋቾ የዝውውር መስኮት ላይ ክለቡን በነፃ በመልቀቅ ወደ አርሰናል ለመዛወር ተዘጋጅቷል።  (Source: talkSPORT)

.

➣ ኦስማኔ ዴምቤሌይ ባርሴሎናዎች ሪያል ቤቲሲን ከሚገጥመው ቡድን ስብስብ ውጪ ሆኑአል። ቫልቬርዴ በቅርቡ ማልኮምን "ትልቅ የሆነ የግል አቲቲውድ አለው" በማለት ብራዚላዊውን አድንቆ ዴምቤሌይን ያሳነሰበትን አስተያየት ሰጥቷል። አሰልጣኙ ፈረንሳዊውን ኮከብ ከቡድኑ ውጪ ማድረጉ በሁለቱ መካከል ያለው ግንኙነት መበላሸቱን ያመላከተ ነው ተብሏል።  ተጭዋቹ ከአሰልጣኙ ጋር ግጭት ውስጥ የገባው ጉዳት ላይ እንደሆነ እየታወቀ ለቡድኑ በጊዜ ሪፖርት ባለማድረጉ ሲሆን ለልምምድ በመጣበት ሰአት ከዋናው ቡድን ውጪ ለብቻው ጂም እንዲሰራ ታዟል። ተጭዋቹ በጥር የዝውውር መስኮት ላይ ወደ ቼልሲ አልያም አርሰናል ሊዛወር እንደሚችል ተነግሯል።  (ArsenalNexus)
.

➣ ዛሬ እንደወጡ በርካታ ሪፖርቶች ከሆነ አርሰናሎች ፓትሪክ ሺክን በጥር ወር ላይ ለማዛወር እያደረጉት ያለው ሙከራ አሮን ራምሴይን የዝውውሩ አካል ሊያደርግ ይችላል። ያም ሆኖ ክለቡ በዳኒ ዌልቤክ ጉዳት ሳቢያ መድፈኞቹ የተጭዋቹን ፓትሪክ ሺክ ለማዛወር የሚያደርጉትን ጥረት ለግዜው በመግታት የሊሉን ኒኮላስ ፔፔን ለማዛወር የሚያደርጉትን ጥረት ቅድሚያ በመስጠት ይገፉበታል።

.

➣ ማንቸስተር ዩናይትዶች ማቲዮ ዳርሜይን በጥር ወር ለመሸጥ ከኢንተር ሚላን እና ሮማዎች ጋር ድርድር ማድረግ ጀምረዋል።   (Sun)

.

➣ የVAR ቴክኖሎጂ በዚህ አመቱ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ጫወታዎች ላይ ስራ ላይ ይውላሉ። UEFA በመስከረም ወር 2019 ላይ ይሄንን ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀሙበት ገልፀው የነበረ ቢሆንም መልሰው የቫርን በጨዋታዎች ላይ በፍጥነት ተግባራዊ ስለማድረግ ለሳምንታት ያህል ሲወያዩበት ቆይተው ካሰቡበት ቀን ቀደም ብለው ሊጠቀሙበት አስበዋል።  [BBC Sport]

.

➣ አሌክሲስ ሳንቼዝ ማንቸስተር ዩናይትድን በመልቀቅ ወደ ፒ.ኤስ.ጂ መዛወር ይፈልጋል። ተጭዋቹ በደቡብ ምዕራቡ የእንግሊዝ ክለብ መላመድ የተሳነው ሲሆን ተጭዋቹ በካሪንግተን የልምምድ ማዕከል ላይ ደስተኛ አለመሆኑን በተደጋጋሚ የሚያሳያቸው በሃርያት ያመላክታሉ።  (Times)

.

➣ ፖል ፖግባ በበኩሉ ትላንትና በካሪንግተን የተደረገው ልምምድ ላይ አልተካፈለም። ተጭዋቹ ለብቻው በቤት ውስጥ ቀለል ያለ ልምምድ ያደረገ ሲሆን መጠነኛ የሆነ ጉዳት አስተናግዷል። እሁድ ለሚደረገው የደርቢው ጨዋታ መሰለፉም ያጠራጥራል።   (Mail)

.

➣ ፒር ኤምሬክ ኦበምያንግ ከ2015 ማርች ወር ኦሊቨር ዥሩድ ከተመረጠ በኃላ የወሩ የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ተጭዋች በሚል ሲመረጥ የመጀመሪያው የአርሰናል ተጭዋች ነው። ሌላኛው የቡድን አጋሩ አሮን ራምሴይ ደግሞ ፉልሃም ላይ ያገባት ጎል የወሩ ምርጥ ጎል ተብላ ተመርጣለታለች።

➣ በአርሰናል ክለብ በቅርብ አመታት የወሩ ምርጥ የሊጉ ተጭዋች በመባል የተመረጡ ተጭዋቾች ..

• October 2018: Pierre-Emerick Aubameyang
• March 2015: Olivier Giroud
• September 2013: Aaron Ramsey
• October 2011: Robin Van Persie
• December 2010: Samir Nasri
• October 2009: Robin Van Persie

.

➣ ፔፕ ጋርዲዮላ ከጆዜ ሞሪንዎ ጋር ስላለው ባላንጣነት:

"አሁን ባላንጣነታችን ተሻሽሏል። ሆኖም ልክ ከጫወታው መጠናቀቅ በኃላ ሁለታችንም መልካም ሰዎች እንሆናለን። እናንተ ከምታስቡት በላይ እኛ እንግባባለን"

.

➣ ኬርሎ አንቼሎቲ ጆዜ ሞሪንዎ በጁቬንቱሱ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ፍፃሜ ላይ ስላደረጉት ነገር በጋዜጠኞች ሲጠየቁ እሳቸውም ጆሮአቸውን በመያዝ እንዲህ ሲሉ መልሰዋል:

“Sorry I didn’t hear you ይቅርታ አልሰማዋችሁም” -  ሁሉም ጋዜጠኞች ሳቁ።

.

➣ ሲሞን ሚኞሌት በቀድሞው የአርሰናል ተጫዋች ፓትሪስ ቪየራ ሁለተኛ እድል ሊሰጠው ይችላል። ተጭዋቹ በሊቨርፑል ፍፁም ደስተኛ ያልሆነ ሲሆን። አኒንሱ አለቃ የቀድሞው መድፈኛ ክለብ ኒስ ለዝውውር ተፈልጓል። ኒንስ በሊግ ዋን ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።    (mirror)

.

➣ ጄሚ ካራገር እንደሚያምነው ከሆነ ራሂም ስተርሊንግ ሊቨርፑልን በመልቀቅ ወደ ማንቸስተር ሲቲ ለመዛወር ያሳለፈው ውሳኔ ድንቅ ነው። "የለቀቀው በእግርኳሳዊ ምክንያቶች ነው። በወቅቱ ሊቨርፑሎች ጥሩ ቁመና ላይ አልነበሩም። በተቅቃራኒው ሲቲዎች እየሄዱበት ያለው አቅጣጫ ግን ጥሩ ነበር"    (liverpoolecho)

.

➣ ዤርዳን ሻቂሪ እንደ ሊቨርፑል ተጭዋችነት በክለቡ በፍጥነት መልመዱን እንደወደደው በይፋ ተናግሯል። "እኔ እዚህ በመሆኔ እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ። በጣም በፍጥነት ክለቡን መላመድ ችያለሁ። ሆኖም ከዚህም በላይ ገና በደንብ መሻሻል እችላለሁ። አሁን ባለሁበት ሁኔታ ግን ደስተኛ ነኝ"  (liverpoolfc)

.

➣ የሌስተር ሲቲ እግርኳስ ክለብ ይፋ እንዳደረጉት ከሆነ በክለቡ ኪንግ ፓወር ስታዲየም የውጪኛው ክፍል ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸውን ላጡት የክለቡ ባለቤት Vichai Srivaddhanaprabha መታሰቢያ የሚሆን ሃውልት እንደሚገነቡ አሳውቀዋል።

.

➣ ቦሩሲያ ዶርትመንዶች ግብ ጠባቂያቸው ሮማን ቡርኪ ትላንትና ልምምድ ላይ ሳይካፈል ቀርቷል። መጠነኛ የጡንቻ ህመም የገጠመው ሲሆን ዛሬ ከባየር ሙኒክ ጋር በሚደረገው ተጠባቂ ጨዋታ ላይ ላይሰለፍ ይችላል።   (Bild)

.

➣ አምስት ተጨማሪ አመታት! ራሂም ስተርሊንግ በማንቸስተር ሲቲ እስከ 2023 የውድድር አመት ድረስ የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ተፈራረመ።

➣ ራሂም ስተርሊንግ ፊርማውን ካኖረ በኃላ: “ውሌን በማራዘሜ ተደስቻለሁ። እዚህ ከመጣው ጀምሮ ያሳየውት እድገት የማይታመን ነው። ኢትሃድ ከደረስኩ ጊዜ ጀምሮ ትክክለኛ ምርጫ እንዳደረኩ ይሰማኛል። እጅግ በጣም ተደስቻለሁ።"

➣ ራሂም ስተርሊንግ ለማንቸስተር ሲቲ ከፈረመ በኃላ:
• በ2015/16 Played: 47 Goals: 11 Assists: 10
• በ2016/17 Played: 46 Goals: 10 Assists: 19
• በ2017/18 Played: 46 Goals: 23 Assists: 17
• በ2018/19 Played: 14 Goals: 7 Assists: 7
ባጠቃላይ ተጫወተ: 153 | አገባ 51 | ለጎል አቀበለ 53

.

➣ ሲቪያዎች የሊቨርፑሉን ግራ ተመላላሽ ተከላካይ አልቤርቶ ሞሬኖን ማዛወር ይፈልጋሉ። ተጭዋቹ በቀያዮቹ ቤት ያለው ኮንትራት በአመቱ መጨረሻ ላይ ኮንትራቱ ያበቃል።  (FTransferNews)

.

➣ ማውሪዚዮ ሳሪ ሮዝ ባርክሌይ በቼልሲ የነበረውን የእግርኳስ ህይወቱ በአዲስ መልክ እንዲያንሰራራ ማድረጉን አድንቀዋል። አሰልጣኙ ባርክሌይን ከሩበን ሉፍተስ ቼክ ይበልጥ ታክቲካዊ ጉዳዮችን መረዳትም ይችላል ብለዋል።  (AdamCrafton)

.

➣ አርሰናሎች ዳኒ ዌልቤክ ከስፖርቲንግ ሊዝበን በነበራቸው የዩሮፓ ሊግ ጨዋታ ላይ የደረሰበት የቁርችምጭሚት ጉዳት አጥንት ስብራት ከባድ በመሆኑ ሲዝኑን ሙሉ በጉዳት ከሜዳ ሊያርቀው ይችላል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል። ሆኖም የጉዳቱ ጥልቀት እና መዳኛ የግዜ ገደብ እስካሁን ጥርት ያለ መረጃ አልወጣለትም።    (SamiMokbel81_DM)

.

➣ ቶርጋን ሃዛርድ እንዳለው ከሆነ በእርሱ እና በቼልሲው ኮከብ ወንድሙ ኤዲን ሃዛርድ መሃከል በያመቱ በየክለቦቻቸው 'እኔ ከፍተኛ ጎል በሲዝኑ አስቆጥራለሁ' የሙል የቤተሰባዊ ውርርድ እንደሚያደርጉ ተናግሯል። ሦስተኛው ወንድማቸውም ካይላን ይሄንኑ ፉክክር በቅርቡ እንደሚቀላቀል ተስፋ አለኝም ብሏል። "በእኔ እና በሃዛርድ መሃከል በየአመቱ ተመሳሳይ ፉክክር በመሃላችን አለ"   (dailymail)

No comments:

Post a Comment

አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦

Featured Post/ቀጣይ ልጥፍ

የዝውውር ዜናዎች

  ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር...