Thursday, November 22, 2018

ቼልሲዎች አንቶኒ ማርሻልን በጥር የዝውውር መስኮት በልውውጥ ውል ሊያስፈርሙት አቅደዋል



CHELSEAዎች አንቶኔ ማርሻልን በጥር የዝውውር መስኮት ላይ ለማዛወር ወጥነዋል። ማውሪዚዮ ሳሪ የጆዜ ሞሪንዎን ባለተሰጥዎ የፊት መስመር ተጫዋች ለማስፈረም ሲሉ ዊሊያንን ያካተተ የልውውጥ ዝውውር ለማድረግ አስበዋል።

ቀያይ ሰይጣኖቹ የአንቶኔ ማርሻልን ኮንትራት በአንድ አመት ተጨማሪ ውል ለማራዘም አክቲቬት ያደረጉት ሲሆን ፈረንሳዊው የክንፍ መስመር ተጫዋች የቀረበለትን የረጅም አመት ውል ሳይቀበለው መቅረቱ ይታወሳል።

ዩናይትዶች አሁን በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኘውን የቡድኑ ባነተሰጥዎ ተጭዋች በክለቡ እንዲቆይላቸው አዲስ በድምሩ የጉርሻ ክፍያዎችን ጨምሮ የ£45 million አምስት አመት ውል ሊያቀርቡለት ተሰናድተዋል።

ሆኖም እንደ Sky Sports ተረዳውት ብሎ እንደዘገበው ከሆነ በቡድኑ እና በተጭዋቹ መሃከል ከስምምነት ላይ ለመድረስ ከጫፍ አልተደረሰም። እናም ቼልሲዎች ለዝውውሩ አማራጭ ተጭዋች ለዩናይትዶች በመስጠት በጥር የዝውውር መስኮት ላይ ወደ ለንደን ሊያስኮበልሉት አቅደዋል።

ማርሻል በቅርቡ በክለቡ የቀረበለትን ሳምንታዊ የ£160,000 ደሞዝ ሂሳብ ውል ውድቅ አድርጎታል። ሆኖም ክለቡን መልቀቅ እንደማይፈልግና አሁን በማንቸስተር እንደተረጋጋ ገልፆአል።

ምንም እንኳን ከጆዜ ሞሪንዎው ቡድን ባለፈው አመት አብላጫውን ጨዋታዎች ከቄሚ አሰላለፍ ውጪ ቢደረግም አዲስ ውል ስለሚፈርምበት ሁኔታ ከክረምቱ የዝውውውር መስኮት ግዜ ጀምሮ በክለቡና በተጭዋቹ መካከል ንግግር ከጀመሩ ቆይተዋል። ከዛ ጊዜ በኃላ ደግሞ የተጭዋቹ የግል ብቃት ከምንግዜውም በላይ ጨምሮ ታይቷል።

ቼልሲዎች በአሁኑ ወቅት የማንቸስተር ዩናይትዱን ክንፍ ማርሻል በክንፍ ተጭዋቻቸው ዊሊያን መቀያየር እንደሚፈልጉ ጭምጭምታዎች መሰማት ከጀመሩ ቆየት ብለዋል።

ዊሊያን በበኩሉ ከቀድሞው የቼልሲ አለቃው ጆዜ ሞሪንዎ ጋር በድጋሚ የመስራት እድሉን ቢያገኝ ፖርቹጋላዊውን ከመቀላቀል እንደማያቅማማ ተናግሮ ነበር። ሞሪንዎ በበኩላቸው የብራዚላዊው የረጅም ግዜ አድናቂ ናቸው።

ዊሊያን እንዳለው ከሆነ: "ሞሪንዎ እስካሁን አብሬ ከሰራሁአቸው አሰልጣኞች መሃከል ምርጡ ነው። ጥሩ ግንኙነት አለን። ጓደኛሞች ነን።

"አንዳንዴ እናወራለን። መልዕክቶችን በስልክ እንድለዋወጣለን። በWhatsApp በደንብ እናወራለን። እርሱ ታላቅ አሰልጣኝ ነው። በእርሱ የሰለጠንኩባቸውን ግዝያቶች ተዝናንቼባቸዋለሁ። አንድ ቀን አብሬው እንደምሰራም ተስፋ አለኝ"

(ምንጭ፦ Thesun)

No comments:

Post a Comment

አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦

Featured Post/ቀጣይ ልጥፍ

የዝውውር ዜናዎች

  ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር...