TEAM NEWS - የሁለቱ ቡድኖች ዜናዎች፦
▪ የማንቸስተር ዩናይትዱ ኮከብ ፖል ፖግባ በእሁዱ ጨዋታ ላይ በቅጣት ምክንያት አይሳተፍም።
▪ የቡድን አጋሮቹ ኒማንያ ማቲች ምንም እንኳን ሙሉ ለሙሉ ጤነኛ ባይሆንም የደርቢው ጨዋታ ላይ ይሰለፋል። ዝላታን ኢቭራሞቪችና ፊል ጆንስ ወደ ሜዳ ይመለሳሉ።
▪ ማርዋን ፌላይኒ በበኩሉ የመጨረሻ የጤንነት ምርመራውን ከጨዋታው በፊት ያደርጋል።
▪ የማንቸስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በበኩላቸው በቪሰንት ኮንፓኒ አካል ብቃት ላይ በመጨረሻ ውሳኔ ያሳልፋሉ። ተጭዋቹ ከሻክታር ዶኔትስኩ ጨዋታ ውጪ ተደርጎም ነበር።
▪ ዴቪድ ሲልቫ ለደርቢው ጨዋታ እንደሚመለስ እርግጥ ሆኑአል። ፋቢያን ዴላፕ ግን የሚሰለፍ አይሆንም።
MANCHESTER DERBY - የቡድኖቹ ወቅታዊ ብቃት
★ የEPL መሪወች የሆኑት የማንችስተሮቹ ሀያላን ክለቦች ዩናይትድና ሲቲ እሁድ ከምሽቱ 1፡30 በግዙፉና በማራኪው ኦልትራፎርድ ስታዲየም ይፋለማሉ፡፡ የ ሞሪኒሆው ዩናይትድ ባሳለፍነው ሳምንት አስደናቂ የመከላከል ስትራቴጂ ተጠቅሞ ያገኛቸውን አጋጣሚ በአግባቡ ተጠቅመው የሰሜን ለንደኑን አርሰናልን በሜዳውና በደጋፊው ፊት 3ለ1 አሸንፈዋል፡፡ ምስጋና ለ ዴቪድ ዴህያ ይሁንና
በዚያ ጨዋታ ላይ የመሀል ሜዳው ሞተር ፖግባ በፈፀመው አላስፈላጊ ፋወል ቀይ ካርድ በማየቱ የሲቲውን ጨምሮ 3 ጨዋታዎች ያልፉታል፡፡ ዩናይትድ በ 15 ጨዋታዎች 35 ነጥብ በመሰብሰብ ከሲቲ በ 8 ነጥብ ርቆ 2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
★ በተመሳሳይ ማን ሲቲ ባሳለፍነው ሳምንት ዌስትሀምን ጋብዞ በ83ኛው ደቂቃ ሲልቫ ባስቆጠራት ጎል ሙሉ 3ነጥብ ይዞ መውጣት ችላል፡፡ የጋረዲወላው ማን ሲቲ በ 15ጨዋታዎች 43 ነጥብ በመሰብሰብ ሊጉን በ 1ኛ ደረጃ እየመራ ሲገኝ
ነገ ካሸነፈ 14 የEPL ጨዋታዎችን በማሸነፍ በአርሰናል እና በቸልሲ ተይዞ የነበረውን ያለመሸነፍ ጉዞ ከፍ ያረጋል፡፡
★ ሁለቱም የማንቸስተር ክለቦች በሳምንቱ አጋማሽ በተካሄደው የ UCL ውድድር ምድባቸውን በበላይነት ማጠናቀቃቸው የሚታወስ ነው፡፡
Your Questions - ስለ ደርቢው ተጠይቀው የተመለሱ 3ቱ ጥያቄዎች!
1. እሁድ በሁለቱ ማንችስተሮች መካከል የሚደረገው ጨዋታ በታሪካቸው ውስጥ ለስንተኛ ጊዜ ነው የሚገናኙት?
መልስ ፦ የእሁዱን ጨዋታ ሳይጨምር እስካሁን በሁሉም ውድድሮች ለ174 ጊዜ መገናኘት ችለዋል, እሁድ የሚደረገው ጨዋታ 175ተኛ የደርቢ ጨዋታቸው ነው።
2. በማንችስተር ደርቢ ላይ ብዙ ጨዋታዋችን በመሰለፍ ቀዳሚው ተጫዋች ማን ይባላል? ስንት ጨዋታዋችን ማድረግግ ችሏል?
መልስ ፦ ሪያን ጊግስ ነው, 36 ጨዋታዋችን ማድረግ ችሏል።
3. በማንችስተር ደርቢ ላይ ብዙ ጎል በማስቆጠር ቀዳሚው ተጫዋች ማን ይባላል? ስንት ጎል ማግባት ችሏል?
መልስ ፦ ዋይን ማርክ ሩኒ 11 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።
Who Said What? - ተጭዋቾችና አሰልጣኞች ምን አሉ?
▪ ስፖንያርዱ ኮከብ ዴቪድ ዴህያ ከቀድሞ የአርሴናል ተጨዋች ሄነሪ ጋር በስካይ ስፖርት ባደረገው ቆይታ ስለ ደርቢው ጠይቆት የሰጠው ምላሽ ፦
" የምንጫወተው በሜዳችን ነው። በደጋፊያችን ፊት የምናደርገው ልዩ ጨዋታ ነው። ደርቢ ነው እኛ በራሳችን እንተማመናለን። ጥንካሬ ይሰማናል ማሸነፍ
እንፈልጋለን"
"ቡድኑ አሁን በጣም ጥሩ ነው። ከሜዳችን ውጭ ሁለት አስቸጋሪ ጨዋታዋችን ማሸነፍ ችለና። ጠንካሮች ነን ማሸነፍ እንፈልጋለን"
▪ ማታ ስለ ፖግባ ተጠይቆ የመለሰው ፦
"ማክሰኞ እለት ቆንጆ የሆነ ኳስ አሲስት ማድረግ ችሎ ነበር። እሱ ሙሉ የሆነ ተጨዋች ነው። ሁሉንም ነገር ማድረግ የሚችል ተጨዋች ነው። የእሱ አለመኖር ክፍተት ይፈጥራል። ነገር ግን በቦታው ላይ ሌላ ተጨዋቾች መጫዋትና መሸፈን ይችላል"
▪ የማንቸስተር ሲቲው አለቃ ፔፕ ጋርዲዮላ ስለ ጨዋታው፦
"ወደ ኦልትራፎርድ ተጉዞ መጫወት ደስታ ነው። ለዛም ነው እዚህ የተገኘነው። በጨዋታው ያለጥርጥር እዝናናለሁ።
"ወደዛው አምርቼ ለመጫወት ዝግጁ ነኝ። እዛ መሆንን በጣም እወደዋለሁ። ከነርሱ ጋር ገጥመን ምን እንደሚፈጠር ለማየት እፈልጋለሁ።
"ከዛ በኃላ ከሞሪንዎ ጋር እንደምንጨባበጥ ተስፋ አደርጋለሁ።"
MATCH Facts - የጨዋታው እውነታዎች እና ታሪካዊ ኩነቶች
▪ ሞሪንሆ በኦልትራፎርድ የተሸነፉት ከ42 ጫወታ 1 ብቻ ነው።
▪ ጋርዲዮላ በሞሪንሆን የተሸነፈው ከ19 ጫወታ 4 ግዜ ብቻ ነው።
▪ ዋይኒ ሮኒ በዚህ ደርቢ 11 ጎል በማስቆጠር ቀዳሚ ነው።
▪ ሲቲ በፕ.ሊጉ በርካታ ጎል ያስቆጠረው ኦልትራፎርድ ላይ ነው።
▪ የማንችስተር ደርቢን የጊግስን ያህል 36 ግዜ የተጫወተ የለም።
▪ ሞሪንሆ ለ51 ዓመታት በዩናይትድ ያልታየ ሪከርድ አምጥተዋል።
136 ዓመታት በፊት በኖቬምበር ወር ማንችስተር ዩናይትድ St. Mark's የሚባል ቡድንን በሜዳው ገጥሞ 3ለ0 አሸንፎ ተመለሰ ይህ ቡድን ባሁኑ
መጠሪያ ማንችስተር ሲቲ ነው። ይህ ጫወታም በሁለቱ ቡድኖች ለመጀመሪያ ግዜ የተደረገ በመባል በታሪክ መዝገብ ሰፍሯል።
ከዛ በኋላ በሁሉም ውድድሮች ለ174 ግዜ ተፋልመዋል። ዩናይትድ 72 ግዜ በማሸነፍ የበላይ ሲሆን ሲቲ 50 ግዜ ማሸነፍ ችሏል ቀሪውን 52 ጫወታ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
በ1947 በሊግ ውድድር በሲቲ ሜዳ 0ለ0 ሲለያዩ ጫወታውን የታደሙት 78,000 ተመልካቾች ነበሩ። ይህም በማንችስተር ደርቢ በርካታ ተመልካች
የተከታተለው ጫወታ በመሆን እስካሁን ድረስ ለ70 ዓመታት በሪከርድነት ዘልቋል።
በተጫዋችነት እና በአሰልጣኝነት ሁለቱንም ክለቦች ያገለገሉ ባለታሪኮች ሁለት ናቸው። አሌክስ ፈርጉሰን ኦልትራፎርድ ከመድረሳቸው በፊት ዩናይትዶችን ያጀገነው የምንግዜም ምርጡ አሰልጣኝ Matt Busby ነበር። በ1920ዎቹ እና 30ዎቹ
ግን ከ200 በላይ ጫወታዎችን ለሲቲ መጫወት ችሏል በ1934 የFA CUP ማዳሊያንም ከሲቲ ጋር አጥልቋል። ከሁለተኛው አለም ጦርነት በኋላ ግን ማት ቤስቢ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ በቆይታውም 5 የሊግ ዋንጫ ፣ 2 FA CUP ፣ እና የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግን በማሸነፍ ወርቃማ
ታሪክን መፃፍ ችሏል።
Steve Coppell በ1970ዎቹ በዩናይትድ ማልያ በቀኝ ክንፍ በኩል 300 ጫወታዎችን ማድረግ ችሏል በ1977 FA CUP ዋንጫንም መሳም ችሏል።
በ1996 ግን የሲቲ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ ሆኖም ስልጣን ላይ መቆየት የቻለው ለ32 ቀናት ብቻ በመሆኑ በሲቲ ቤት አጭር የአሰልጣኝነት ቆይታ ያደረገ በሚል በሪከርድነት ሰፍሯል።
በፕሪምየር ሊጉ የእርስ በእርስ ግንኙነት
▪ በተወዳጁ ሊግ ለ40 ግዜያት የተገናኙ ሲሆን 20 ግዜ በማሸነፍ ዩናይትድ የበላይ ነው። ሲቲ ደግሞ 12 ግዜ ማሸነፍ ችሏል 8 ግዜ አቻ ተለያይተዋል።
▪ ዩናይትድ 59 ጎል ያስቆጠረ ሲሆን ሲቲ 51። መረባቸውን ከጎል በመታደግ ዩናይትዶች አሁንም የተሻለ ሪከርድ አላቸው 15 ሲቲ 8 በዲሲፕሊን በኩል ዩናይትድ ደካማ ሪከርድ ነው ያለው 66 ቢጫና 7 ቀይ ካርድ የተመዘዘበት ሲሆን ሲቲ 87 ቢጫና 1 ቀይ ካርድ ተመልክቷል።
▪ ዩናይትድ ከሲቲ ጋር ባደረጋቸው ያለፉት 12 የሊግ ጫወታ በ7ቱ ተሸንፏል። ይህም ከዚያ በፊት ካደረጋቸው 45 ግንኙነቶች ይልቃል ሲቲ በፕ.ሊጉ ታሪክ ከሜዳው ውጪ በርካታ ጎል ያስቆጠረው ኦልትራፎርድ ላይ ነው። (27)
▪ ዩናይትድ በጆሴ ሞሪንሆ ስር በሜዳው ባደረጋቸው 42 ጫወታዎች የተሸነፈው 1 ግዜ ብቻ ነው። (30 አሸንፎ 11 አቻ)
▪ ሞሪንሆ በሜዳቸው ባደረጉት ያለፉት 40 ጫወታዎች ሽንፈትን ባለማስተናገድ በ1966 በማት ቤስቤይ የተያዘውን ሪከርድ ተጋርተዋል።
▪ ዩናይትድ በዚህ ሲዝን አስገራሚ የመከላከል ሪከርድ አለው ከተቆጠሩበት 9 ጎሎች ውስጥ በሜዳው ያስተናገደውም 1 ጎል ብቻ ነው።
▪ ሞሪንሆ ከጋርዲዮላ ጋር ባደረጋቸው 19 ጫወታዎች ማሸነፍ የቻለው 4 ግዜ ብቻ ነው። (8 ተሸንፎ 7 አቻ) ጄሲ ሊንጋርድ ባለፉት 2 የፕ.ሊግ ጫወታ 3 ጎሎችን ማስቆጠር ሲችል ከዛ በፊት በ51 ጫወታ ካስቆጠረው ይልቃል።
▪ አጉዌሮ ከሜዳው ውጪ ባደረጋቸው ያለፉት 9 የፕ.ሊግ ጫወታዎች ጎል ማስቆጠር ችሏል። እሁድስ?
▪ በዚህ ሲዝን በፕ.ሊጉ በርካታ ኳስን ለጎል በማቀበል የሲቲ ተጫዋች የሆኑት ዴብሬይን እና ሲልቫ በእኩል 8 ይመራሉ።
▪ ሲቲ ዩናይትድ ላይ በታሪክ አጋጣሚ ሁለት ግዜ 6 ጎሎች ያስቆጠረበት ሲሆን ዩናይትድ ግን አንድም ግዜ 6 ጎል አስቆጥሮ አያውቅም።
ዩናይትድ 1–6 ሲቲ (1926)
ዩናይትድ 0–5 ሲቲ (1955)
ዩናይትድ 5–0 ሲቲ (1994)
ዩናይትድ 1–6 ሲቲ (2011)
ግምታዊ አሰላለፎች How they could line up፦
ማን.ዩናይትድ XI: De Gea; Lindelof,
Smalling, Rojo; Valencia, Matic, Herrera,
Young; Lingard, Martial, Lukaku
ማንቸስተር ሲቲ XI: Ederson; Walker,
Otamendi, Kompany, Delph; De Bruyne,
Fernandinho, Silva, Sterling, Aguero, Sane
የቢቢሲው ገማች - LAWRO'S PREDICTION
የቪሰንት ኮምፓኒ ጨዋታው ላይ መሰለፍ አለመሰለፍ አጠራጣሪ መሆን የሲቲን የሲዝኑ የመጀመሪያ ጨዋታ ድል እንድገምት አድርጎኛል።
እንደማስበው ማንቸስተር ዩናይትዶች አራት ተከታታይ ጨዋታዎችን በማሸነፍ የብቃታቸው ጫፍ ላይ ይገኛሉ። አርሰናልን ተከላክለው ያሸነፍበት መንገድ ድንቅና አሳማኝ ነበር።
ግምቴ Prediction: 2-0
የሱፐር ኮምፒተሩ ግምት - SAM's verdict
ሊቆጠር የሚችለው የጎል ብዛት: 1-1
አቻ የመውጣት እድላቸው: 27%
የባለሜዳው የማሸነፍ እድል: 29%
ከሜዳ ውጪ የማሸነፍ እድል: 44%
SAM ሱፐር ኮምፑይተር ሲሆን (Sports Analytics Machine) በመባል ይታወቃል። ማሽኑን የፈጠረው የሊቨርፑል ዩንቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆነው ProfIan Mc Hale ነው።
ዘንድሮስ ማን የበላይ ይሆን ይሆን በሜዳው አይበገሬ የሆነው የሞሪንሆው ዩናይትድ ወይስ ያለፉትን 13 የፕ.ሊግ ጫወታን ያሸነፈው የጋርዲዮላው ሲቲ እሁድ ምሽት የምናየው ይሆናል!