MAN CITY READY BIG ALEXIS BID
ማንቸስተር ሲቲዎች ለአርሰናሉ አጥቂ አሌክሲስ ሳንቼዝ በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ ትልቅ ሂሳብ ለማቅረብ ተሰናድተዋል ሲል የእንግሊዙ ጋዜጣ Independent ዘገበ።
ቺሊያዊው አጥቂ የፔፕ ጋርዲዮላውን ቡድን ለመቀላቀል ተቃርቦ የነበረ ሲሆን በ2018 ላይ ከኮንትራቱ ነፃ ይሆናል። ማን.ሲቲዎች ለዝውውሩ በ£50 million ሂሳብ ሊያዛውሩት ቆርጠዋል።
WALCOTT EYED AS LUKAKU REPLACEMENT
ኤቨርተኖች ቲዎ ዋልኮትን በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ ቲዎ ዋልኮትን ለማዛወር እና ሮሚዮ ሉካኩን ቦታ ለመሸፈን ንግግር ማድረግ መጀመራቸው ታውቋል። ከወዲሁ በዝውውሩ ላይ ከክለቡ አርሰናል ጋር ንግግር ማድረግ እንደጀመሩ የእንግሊዙ Daily Mail ዘገበ።
ሉካኩ ጉዲሰን ፓርክን በመልቀቅ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ በክረምቱ የ£75 million ሂሳብ የተዛወረ ሲሆነ እስካሁን ድረስ ምትኩን አላዛወሩም።
ዋልኮት በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ ለሽያጭ የቀረበ ሲሆን በዚህ የውድድር መስኮት ላይ በክለቡ ለሽያጭ የሚቀርብ ሲሆን አንድም የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ማድረግ አልቻለም። በኤቨርተኑ አዲስ አለቃ ሳም አላርዳይስ ለዝውውር በጥብቅ ይፈለጋል።
MAN CITY'S INCREDIBLE MESSI BID
ማንቸስተር ሲቲዎች ለሊዮኔል ሜሲ የ€100 million የዝውውር ሂሳብ እና አመታዊ የ€50m አመታዊ ደሞዝ ሊያቀርቡለት አስበዋል ሲል የስፔኑ ጋዜጣ Marca ዘገባ ጠቁሟል።
የተጭዋቹ የካምፕ ኑ ቆይታ አዲሱን ኮንትራት በቅርቡ ከመፈረሙ በፊት ጥርጣሬ ውስጥ ገብቶ የነበረ ሲሆን ከዛ በፊት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ክለብ ኢትሃድ ይዛወራል በሚል ስሙ በተደጋጋሚ ግዜ ሲነሳ ቆይቶአል።
ያም ሆኖ ሜሲ ኑ ካምፕን ለቆ የመጔዝ ምንም አይነት ፍላጎት የሌለው ሲሆን አሁንም ምንም እንኳን አዲስ ኮንትራት ቢፈርምም ሲቲዎች ካቀረቡለት ደሞዝ በእጅጉን ያነሰ ሂሳብ ነው። ሲቲዎች ያቀረቡለት ደሞዝ ደግሞ ከአለን እግርኳስ ተከፋዮች ሁሉ ሪከርድ የሚሆን የክፍያ ሂሳብ ነው። ከኔይማር ክፍያም የሚበልጥ ነው።
MAN UTD WATCH €80M-RATED LAZIO STAR
አማካዩ በጨዋታው ላይ አንድ ጎል ያስቆጠረ ሲሆን ለሌላኛው ጎል መቆጠርም አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። ተጭዋቹን ላዚዎዎች በክረምቱ የዝውውር መኮት ላይ ሰርቢያውን ተጭዋች የሚለቁት ከሆነ ለዝውውሩ ከማን.ዩናይትድ የ €80 million ሂሳብ ይፈልጋሉ ተብሏል።
BARCELONA MAKE AOUAR CONTACT
ባርሴሎናዎች የሊዮኑን ታዳጊ ኮከብ ሆሴም አውራስ ወኪል ጋር የተነጋገሩ ሲሆን የማዛወር ፍላጎት ፍላጎት እንዳላቸው በመግለፅ ለወኪሉ ነግረውታል ሲል የፈረንሳዩ ጋዜጣ L'Equipe ዘግቧል።
አውራ በዚህ የውድድር አመት ላይ በሊግ 1 ውድድር ላይ ምርጥ ብቃቱን እያሳየ ያለ ተጭዋች ሲሆን ባርሴሎናዎች የ19 አመቱን ተጫዋች እንደ መጠባበቂያ የዝውውር ኢላማ ያልሆነ ሲሆን በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ ተጣድፈው እንደማያዛውሩት ተሰምቷል።
ARSENAL IN N'ZONZI TALKS
ሲቪያዎች ስቲቭ ንዞንዜ በጥር የዝውውር መስኮት ላይ ወደፈለገበት ክለብ እንዲዛወር በሚል ወደ ለንደን ተጎዞ ከአርሰናል ጋር ንግግር እንዲያደርጉ ፈቅደውለታል። ተጭዋቹ ከአሰልጣኝ ኢድዋርዶ ቤሪዞ ጋር ሜዳ ላይ መጋጨቱ የሚታወስ ነው ሲል COPE ዘግቧል።
ንዞንዜ ክለቡ ሲቪያ ባለፈው ወር ላይ በቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ላይ ሊቨርፑል ጋር 3-3 ከተለያዩ በኃላ ለክለቡ ተጫውቶ አያውቅም ሲል ዘገባው አክሎ ገልፆአል። ሊቨርፑሎች የቀድሞውን የብላክበርን ተጭዋች ለማዛወር በሚደረገው ፉክክር ላይ ከአርሰናሎች ጋር ፉክክር የሚያደርጉ ሲሆን ኤቨርተኖችም ሌላኞቹ ፈላጊ የሆኑ የሊጉ ክለብ ናቸው።




No comments:
Post a Comment
አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦