የማን ጨዋታ ነው What is it?
ጨዋታው በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ 4ተኛ የሆኑን አርሰናሉች 2ተኛ ከሆኑት ማንቸስተር ዩናይትዶች ጋር የሚያደርጉት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከባዱ ጨዋታ ነው።
ጨዋታው መቼ ይደረጋል When is it?
ጨቃታው ነገ ማለትም ቅዳሜ በኤምሬትስ ስታዲየም ከምሽቱ 2:30 ላይ የሚደርሀግ ይሆናል።
አርሰናሎች የፕሪሚየር ሊጉን ትልቁ ተቀናቃኛቸው ማን ዩናይትዶች በኢምሬትስ ስቴዲየም ሲያስተናግዱ የሳምንቱ ከባድ ጨዋታ የሚደረግ ይሆናል።
ማንቸስተር ዩናይትዶች ባለፈው ማክሰኞ ከሜዳቸው ውጪ ዋትፎርድን ገጥመው 4-2 በሆነ ውጤት ሲያሸንፉ ምስጋና ለአሽሊ ያንግ ብቃት ውና ለአንቶኔ ማርሻል ጎል ይሁንና እረፍቱን 3ለ0 እየመሩ ነበር ያጠናቀቁት። ከረፍት መልስ ትሮይ ዲኔይ እና አብዱላዬ ባስቆጠሩአቸው ጎሎች ዩናይትዶችን ጭንቀት ውስጥ ከቶአቸው የነበረ ቢሆንም ጄሲ ሊንጋርድ ባስቆጠረው ድንቅ የግል ጥረት ጎል 4ለ2 ሆነው እፎይ ብለዋል።
አርሰናሎች የጎል ናዳ አውርደዋል Rampant Arsenal
አርሰናሎች በበኩላቸው በእረቡው የ5-0 ሃድስፊልድ ድል የጎል ናዳ አውርደውባቸዋል። አሌክሳንደር ላካዜቲ የመጀመሪያውን ጎል ሲያስቆጥር ከዛ በኃላ የነበረው ሰአት ለመድፈኞቹ የጭንቅ ሰአት ነበር።
ቡድኑ በሜሱት ኦዚል በአምስት ደቂቃዎች ውስጥ ሁለት አሲስት እና አንድ ጎል ምስጋና ይግባና ውጤቱን ወደ 5ለ0 ቀይረውታል። ኦሊቨር ዝሩድ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር አሌክሲስ ሳንቼዝ በበኩሉ አንድ ጎል ከመረብ አዋህዷል።
አርሰናሎች የቅዳሜውን ጨዋታ ሜዳቸው ላይ የሚያደርጉ በመሆናቸው የተሻለ የማሸነፍ እድል ይኖራቸዋል።
አርሰናሎች በዚህ አመት ላይ በኤምሬትስ ድንቅ ውጤት እያስመዘገቡ ይገኛሉ።
መድፈኞቹ በዚህ አመት በኤምሬትስ ያደረጓቸውን ሰባቱንም ጨዋታዎች ማሸነፍ ችለዋል። (ማንቸስተር ዩናይትዶችም እንደዛው)
ማን.ዩናይትዶች በበኩላቸው በሁሉም ውድድሮች ላይ ከሜዳቸው ውጪ ያደረጔቸውን ያለፉት 5ት ጨዋታዎች ላይ 3ቱን ተሸንፈዋል።
ጆዜ ሞሪንዎ ይሄንን በመሳሰሉ ትላልቅ የሊጉ ጨዋታዎች ላይ ይዘው የሚገቡት የመከላከል አጨዋወት ስልት ቡድኑን እንዲተች ያደረጉት ነገሮች ናቸው። ልክ ሊቨርፑል እና ቼልሲ ላይ ይዘው የገቡት አይነት ታክቲክ ይዘው እንደሚገቡ ይጠበቃል።
አርሰናሎች ሦስቱ ተከላካዮቻቸው ማለትም ሎረንት ኮሽሌይኒ ፤ ሽኮድራን ሙስታፊ እና ናቾ ሞንሪያል አንድ ላይ በተሰለፉባቸው ስድስት ጨዋታዎች ላይ ምንም ጎል ሳይቆጠርባቸው ጨርሰዋል።
የአርሰናል የቡድን ዜናዎች Arsenal team news
አሌክሳንደር ላካዜቲ በእሮቡ ጨዋታ ላይ በእረፍት ጊዜ ተቀይሮ የወጣ ሲሆን የGroin ጉዳት ደርቦበታል። አርሰን ዌንገር ከጨዋታው በኃላ ስለ ተጭዋቹ እንዲህ ብለዋል..
“ጥቂት ጨዋታዎች ያመልጡታል”
ኦሊቨር ዥሩድ ቦታውን በመተካት ቋሚ ተሰላፊ እንደሚሆን ይጠበቃል።
አልምክስ ኢዎቢ ከደረሰበት የDead leg ህመም በማገገሙ በድጋሚ ወደ ጨዋታ ለመመለስ ዝግጁ ሆኖአል።
ዳኒ ዌልቤክም የቀድሞ ክለቡን ለመግጠም ዝግጁ ነው። እንግሊዛዊው ኢንተርናሽናል አጥቂ ከቀድሞ ክለቡ ጋር ባደረጋቸው ጨዋታዎች ላይ ለ3ት ተከታታይ ጊዜ ጎሎችን አስቆጥሮአል።
የሳንቲ ካዞርላ ጉዳት ግን አሁንም አላገገመም። ተጫቹ ከደረሰበት የቁርጭምጭሚት ጉዳት ለመዳን ሌላ ቀዶ ጥገና ማድረጉን ከቀናት በፊት ይፋ አድርጔል።
የማንቸስተር ዩናይትድ የቡድን ዜናዎች Manchester United team news
ማርዋን ፌላይኒ በደረሰበት የጉልበት ጉዳት ሳቢያ ከጨዋታው ውጪ ሆኑአል። ቤልጂየማዊው ስለማይኖር የዩናይትዶች የመሃል ሜዳ ክፍል አማራጭ ይጠባል።
ኒማንያ ማቲች በደረሰበት የጡንቻ ችግር ሳቢያ ተቀይሮ ወጥቶ የነበረ ቢሆንም ለነገው ጨዋታ ግን እንደሚመለስ ይጠበቃል።
ማይክል ካሪክ ግን ከጨዋታው ውጪ መሆኑ ታውቋል።
ፖል ፖግባ በበኩሉ ከጉዳት ከተመለሰ በኃላ በሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ሙሉ 90 ደቂቃዎችን መሰለፍና መጫወት ችሏል።
ሞሪንዎ እንደሰጡት ፍንጭ ከሆነ ደግሞ አንቶኔ ማርሻል የጨዋታ መደራረብ ስላለበት ድካም ሳይሰማው አይቀርም በሚል ለጨዋታው ቄሚ ተሰላፊ ላያደርጉት እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
ምንም እንኳን ፊል ጆንስ ከጨዋታው ውጪ ቢሆንም ኤሪክ ቤይሊ ግን ከደረሰበት የ thigh injury አገግሞ እንደሚሰለፍ ይጠበቃል።
Wenger ስለ ጨዋታው: "ማን.ዩናይትዶች ጠንካራ ቡድን ናቸው። ከሚያደርሱብን ችግር ለመውጣት እንደምዘጋጅ አምናለው። ለመከላከል ብቻ ሳይሆን ለማጥቃትም ጭምር ይመጣሉ።
“አደገኛ ቡድን ናቸው። በባለፉት ጨዋታዎቻቸው ላይ ድንቅ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል። ስለዚህ እነርሱን ለማሸነፍ በድንቅ አቋማችን ላይ መገኘት ይገባናል። ማተኮር የምፈልገው ማሸነፍ ላይ ብቻ ነው።
“ሳንቼዝ መጠነኛ የhamstring ችግር ነበረበት
– ሆኖም ለክፉ ሚሰጠው አይደለም”
ግምታዊ አሰላለፎት Predicted Line-Ups ..
አርሰናል...
ግብ ጠባቂ ፦ ፒተር ቼክ
ተከላካዮች ፦ ሞንሪያል ፣ ሙስታፊ ፣ ኮሽሌይኒ
አማካዮች ፦ ኮላሲኒች ፣ ራምሴይ ፣ ዥካ ፣ ቤለሪን
አጥቂዎች ፦ ዥሩድ ፣ ኦዚል ፣ አሌክሲስ
(ፎርሜሽን፦ 3-4-2-1)
ማንቸስተር ዩናይትድ ..
ግብ ጠባቂ ፦ ደ ሂያ
ተከላካዮች ፦ ሮሆ ፣ ስሞሊንግ ፣ ሊንደሎፍ ፣ ያንግ ፣ ቫሌንሺያ
አማካዮች ፦ ሄሬራ ፣ ማቲች ፣ ፖግባ
አጥቂዎች ፦ ሉካኩ ፣ ራሽፎርድ
(ፎርሜሽን፦ 5-3-2)
የቀቋማሪ ድርጅቶች ግምት What are the odds?
አርሰናል ያሸንፋል - 6/4
ማን.ዩናይትድ ያሸንፋል - 9/5
አቻ - 23/10
No comments:
Post a Comment
አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦