Tuesday, December 5, 2017

ማክሰኞ አመሻሽ ላይ የወጡ ሠፊ የዝውውር ዜናዎች አስተያየቶች እና ሌሎችም አጫጭር ትኩስ የእግር ኳስ መረጃዎችን ያንብቡ - Latest Transfer News Update



MAN UTD CONFIDENT OF £50M ROSE
DEAL


የማንቸስተር ዩናይትዱ አለቃ ጆዜ ሞሪንዎ የቶተንሃሙን ግራ ተመላላሽ ዳኒ ሮዝ በጥር የዝውውር መስኮት ላይ በ£50 million ሂሳብ እንደሚያዘዋውሩት እርግጠኞች ሆነዋል ሲል Daily Mail ዘገበ።

ሞሪንዎ አዲስ ግራ ተመላላሽ ለማስፈረም ወደ ገበያው የሚወጡ ሲሆን ቦታው አሁንም ክፍት እንደሆነና ተጭዋቹ ሁነኛ የረጅም ግዜ የቦታው ትክክለኛ ሰው እንደሆነ ያምናሉ ሲል ዘሰን ዘግቧል። ተከላካዩ በቶተንሃም እንደማይቆይ ፍንጮች ታይተዋል።

አሁን ማን ዩናይትዶች ምንም እንኳን ቶተንሃሞች ተጫቹን ላለመልቀቅ ከፍተኛ ትግል ላይ የነበሩ ቢሆንም በጥር ላይ ካልሆነም በክረምቱ የዝውውር መኮት ላይ ከጃቸው እንደሚያስገቡት እርግጠኞች ሆነዋል።


የዜናዎቹ ስፖንሰር ጆርካ ኢቭንትስ ነው!



★★★★★★⚡(ማስታወቂያ)⚡★★★★★★

👏👌ጆርካ ፌስት 📅ቅዳሜ_ሚያዝያ_06_2010  ⌚ ከቀኑ 6:00 ጀምሮ በጊዮን ሆቴል 

🍻🍹🍺 በርካታ የከተማችን ታዋቂ ምግብ ቤቶች የሚሳተፉበት በአይነቱ ልዩ የሆነ የምግብ እና የመጠጥ ፌስቲቫል። እንዲሁም በዕለቱ ...

🎤 አበበ ከፈኒ(ጀኒና) 
🎤 ሰለሞን ሀይለ 
🎤 እሱባለው ይታይህ 
🎤 ያሬድ ነጉ 
🎤 ጌትሽ ማሞ እና 
🎤 ሮፍናን ስራቸውን ያቀርባሉ። 

💰 መግቢያ 200ብር 

📞 ለበለጠ መረጃ: 0975 06 06 06 / 0911 15 00 13 / 0974 07 07 07


HAZARD HOLDING OUT FOR MADRID OFFER


ቤልጂየማዊው ኮከብ ኤዲን ሃዛርድ የሪያል ማድሪድን የዝውውር ጥያቄ እየጠበቀ በመሆኑ ከክለቡ ቼልሲ ጋር ሲያደርግ የቆየውን የአዲስ ኮንትራት ንግግር ድርድር ለግዜውም ቢሆን አቁሞታል ሲል The Times ገለፀ።

የሰማያዊዎቹ ቦርድ ሃላፊዎች ኤዲን ሃዛርድን የክለቡ የምንግዜውም ከፍተኛ ተከፋይ ሊያደርጉት ያቀዱ ሲሆን ሳምንታዊ የ£300,000 ደሞዝ ሊያቀርቡለት ይፈልጋሉ።

ያም ሆኖ ኢደን ሃዛርድ በቼልሲ የሚያቆይ ቀሪ የሁለት አመት እና ስድስት ወራት ኮንትራት ያለው ቢሆንም ክለቡ ያቀረበለትን አዲስ ውል ለመፈራረም እያመነታ ይገኛል። የሎስ ብላንኮዎቹን የእናዛውርህ ጥያቄም በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።


ARSENAL TO SELL WALCOTT


አርሰናሎች በመጨረሻም ቲዎ ዋልኮትን በጥር የዝውውር መኮት ላይ ለመሸጥ ወስነዋል ሲል ዘ ሰን ጋዜጣ ዘገበ።

ዋልኮትን ለማዛወር የቀድሞ ቡድኑ ሳውዛምፕተን እና ዌስትሃም ዩናይትዶች እንግሊዛዊውን ኢንተርናሽናል ጥር ላይ ለማዛወር ይፎካከራሉ ሲል ጋዜጣው አክሏል። ከተጫዋቹ ሽያጭ በሚያገኙት ገንዘብ በምትኩ የሊዮኑን አጥቂ ናቢ ፊከርን ለማዛወር ይሞክራሉ።


MOURINHO TO BE GIVEN £80M IN JANUARY


እንደ እንግሊዙ ተነባቢ ጋዜጣ The Sun ሃተታ ከሆነ ጆዜ ሞሪንዎ ለጥሩ የዝውውር መስኮት የሚሆን የ£80 million የዝውውር ሂሳብ ክለቡ የሚሰጣቸው ሲሆን ገንዘቡን ከሉክ ሾው እና ማቲዎ ዳርሜይን ሽያጭ የሚያገኙት ይሆናል።

ማንቸስተር ዩናይትዶች በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ከማን.ሲቲዎች እኩል እግራቸውን በመያዝ ለመከታተል እያሰቡ ሲሆን ጆዜ ሞሪንዎም በመጪው ጥር የዝውውር መስኮት ላይ ግራ ተመላላሽ፣ ቀኝ ክንፍ መስመር እና የ10ቁ ተጭዋች በማዛወር ቡድናቸውን ማጠናከር ይፈልጋሉ።


EVERTON JOIN RACE FOR EVANS


አዲሱ የኤቨርተን አሰልጣኝ ሳም አላርዳይስ የዌስት ብሮሙን መሃል ተለላካይ ጆን ኢቫንስን ለማዛወር የሚደረገውን ፉክክር ተቀላቅለውታል ሲል ESPN FC ዘገበ።

የቶፌሶቹ ተከላካይ ክፍል በዚህ የውድድር አመት ላይ በመጥፎ ብቃት ላይ የሚገኙ ሲሆን የ29 አመቱን የሰሜን አየርላንድ ኢንተርናሽናል ለማዛወር ከአርሰናል ፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ሌሎች ክለቦች ጋር ፉክክር ለማድረግ ተሰናድተዋል።

No comments:

Post a Comment

አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦

Featured Post/ቀጣይ ልጥፍ

የዝውውር ዜናዎች

  ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር...