ማስታወቂያ ...
እምር ፅድት ያሉ ፎቶዎችን የሚፈጥሩባቸው በ5ት የኤዲቲንግ አማራጮች በአይቴል S11 ስልክ ላይ ያገኙአቸዋል!
ጆዜ ሞሪንዎ በ4ት ቀናት ውስጥ ብቻ ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎችን ተችተዋል: "በቶተንሃሙ ጨዋታ ያልተዝናናችሁ አንዳንድ ደጋፊዎች፤ በዛሬው ጨዋታ ላይ 'ዘና' ትላላችሁ"
በአራት ቀናት ውስጥ አሰልጣኙ የዩናይትድ ደጋፊዎችን ሲተቹ ለሦስተኛ ግዜአቸው ነው። ይሄንን አዲስ ትችቶች ጆዜ ሞሪንዎ በደጋፊዎቹ ላይ ያዘነቡት ደግሞ አንዳንድ ደጋፊዎች በቶተንሃሙ የ1ለ0 ድል ጨዋታ ወቅት በቡድኑ እንቅስቃሴ ደስተኞች አልነበሩም መባሉን ተከትሎ ነው።
ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ከዛሬው የኦልትራፎርድ የ4:45 ቤኔፊካ ሻምፒየንስ ሊጉ ጨዋታ በፊት በክለቡ በሚታተም የUnited Review መፅሄት ላይ በሰጡት አስተያየት ደጋፊው ላይ የሰላ ትችት ሰንዝረዋል። ሞሪንዎ እንዳሉት ከሆነ...
"በቶተንሃሙ ጭዋታ ላይ ደስተኛ ያልነበራችሁ በሙሉ በዛሬው ጨዋታ ትደሰታላችሁ" በሚል በክለቡ እውቅ ከጨዋታ በፊት መፅሄት United Review ላይ የፃፉት ሞሪንዎ ደጋፊዎቹ በቶተንሃሙ ጨዋታ ላይ ለቡድኑ ሙሉ ድጋፍ አልሰጡም ሲሉም ወቅሰዋቸዋል።
"ዳጋፊዎቹ ለምን ሮሚዮ ሉካኩ ሙሉ ለሙሉ ጨዋታዎች ላይ ያለውን እየሰጠ እየተጫወተ ሳለ ድጋፋቸውን እንዳልሰጡት ቢያብራሩልኝ ደስ ይለኝ ነበር" ሲሉ ሞሪንዎ ከጨዋታው በፊት አስተያየታቸውን በመፅሄቱ ማስፈራቸውን ቀጥለው..
"እንደማስበው በጨዋታው ላይ ጎልም አስቆጠረ ወይም አላስቆጠረ ይሄን ያህል እሚያስተች ነገር ያለ አይመስለኝም። ስላላገባ ብቻ ድጋፍ መንፈግ ተገቢ አይመስለኝም። ስለዚህ በመጠኑም ቢሆን በደጋፊው ተከፍቻለሁ። በእርሱ ግን አልተከፋሁም ደስተኛ ነኝ"
"ለኔ ሉካኩ በቡድኔ ውስጥ የሚነካ ተጭዋች አይደለም። እናም ድጋፍ ሊለየው አይገባም። ከደጋፊዎች ከበሬታ ሊቸረው ይገባል" ሲሉ በአምስት የተለያዩ ውድድሮች ላይ ያለምንም ጎል የጨረሰውን ቤልጂየማዊ አጥቂ ትችት ተከላክለዋል።
የሮማ ደጋፊዎች በፐብ ብራውል ስፍራ ተሰባስበው በነበሩ የቼልሲ ደጋፊዎች ላይ ጥቃት አደረሱ
የቼልሲ እና ሮማ ደጋፊዎች በፐብ ብራውል በሮሙ እውቅ ኮሊሲየም አካባቢ ትላንትና ምሽት ተጋጭተዋል ሲል የዘገበው Corriere dello Sport ነው።
የጣሊያኑ ጋዜጣ አክሎ እንደዘገበው ከሆነ 40 የሚጠጉ የሮማ ደጋፊዎች ፊታቸውን በመሸፈን ጭምብል አድርገው በጣሊያኖ ዋና ከተማ ማዕከላዊ ክፍል በሚገኝ ፐብ ውስጥ በመግባት በያዙት የብረት ቁራጭ (Metal Bars) በቼልሲ ደጋፊዎች ላይ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ ቢያደርጉም ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ፖሊስ ወደ ስፍራው በመድረሱ ግርግሩ በርዷል። ሁለት የሮማ ደጋፊዎችም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
እንደ ዘገባው ከሆነ በግጭቱ ሳቢያ ከቼልሲም ሆነ ከሮማ ደጋፊዎች ከባድ የሚባል አይነት ጉዳት ያልደረሰባቸው ሲሆን የጣሊያን እና የእንግሊዝ ኢምባሲዎች በጋራ በመሆን ተጨማሪ ግጭቶች በቻምፒየንስ ሊጉ ጨዋታው ላይ እንዳይፈጠሩ በትብብር እየሰሩ እንደሆነም ተገልፆአል።
ለምሽቱ ጨዋታ ወደ 1,750 የሚደርሱ ትኬቶች ለተቃራኒ ቡድን ቼልሲ ደጋፊዎች የተሸጡ ሲሆን እነኛ የተሸጡት ትኬቶች ዛሬ በሮሙ የPalatino Hotel ውስጥ ለፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒየኖች ቼልሲ ደጋፊዎች ይሰጣሉ ተብሏል።
የማንቸስተር ሲቲ ደጋፊዎች በናፖሊው የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ላይ የቡድናቸውን አርማ ቤልት ይዘው ስቴዲየም እንዳይገቡ ታግደዋል!
የሲቲ ደጋፊዎች በናፖሊው የስታዲዎ ሳን ፓዎሎ የነገ ምሽት የሻምፒየንስ ሊግ ወሳኝ ጨዋታ ላይ የቡድናቸውን አርማ ቤልት ይዘው በስቴዲየም እንዳይገቡ በናፖሊ ተከልክለዋል።
ደጋፊዎቹ ብቻ ሳይሆኑ የቡድኑ አባላት ስታፎችና የሚዲያ ሰዎችም ይሄንን ቤልት በቻምፒየንስ ሊጉ ጨዋታ ምሽት ወደ ሜዳው ይዘው እንዳይመጡ ከወዲሁ ታግደዋል። ያም ሆኖ እገዳው በማንቸስተር ሲቲ ተጭዋቾች እና አሰልጣኙ ፔፕ ጋርዲዮላ ላይም ጭምር ይስራ አይስራ የታወቀ ነገር የለም።
ለእገዳው መንስኤ የሆነው ድርጊት የተፈጠረው የናፖሊ ደጋፊዎች በባለፈው ኦክቶበር 17ቱ ጨዋታ ላይ ወደ ኢትሃድ ስቴዲየም በመጡ ሰአት አንዳንዶቹ በያዙት የክለቡ አርማ ቤልት የሲቲ ደጋፊዎችን ሳያስቡት 'ከኃላ በማነቅ' በፈጠሩት ግርግር እና ጥቃት ሳቢያ ነው።
በወቅቱ በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ ቢያስ በሦስት ደጋፊዎች ላይ ጉዳት የተከሰተ ሲሆን አንድ የናፖሊ ደጋፊ በበኩሉ ወደ እስር ቤት ካመራ በኃላ ለአምስት ወራት ያህል ምንም አይነት እግርኲስ ጨዋታዎችን እንዳይመለከት እገዳ ተጥሎበታል። ያም ሆኖ የማንቸስተር ክለብ ደጋፊዎች ጀነራል ሴክሬተሪያት Kevin Parker እንዳሉት ከሆነ ከGroup F የነገው ምሽት ምድብ ጭዋታ በፊት የተጣለውን የናፖሊዎች የቤልት እገዳ እርባና ቢስ "ridiculous" ሲሉ በማጣጣል ገልፀውታል።
ፓርከር እንደተናገሩት ከሆነ: "በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊጉ ጨዋታዎች ላይ በሲቲ ላይ ሁሌም እገዳዎች አሉ። በመጀመሪያ በጨዋታዎች ላይ ተቃውሟችንን እንዳንገልፅ (booing) ታገድን። በሁለተኛው ከስቴዲየም ታገድን። አሁን ደግሞ የክለባችንን አርማ ቤልቶች እንዳናደርግ ታግደናል" ሲሉ ሁኔታውን በምሬት ገልፀውታል።
ዛሬ ምሽት በሻምፒዮንስ ሊግ የሚደረጉ ጨዋታዎች፦
⬛ ምሽት 3:45 ላይ ወደ ጣሊያን በመጓዝ የአንቶኒዮ ኮንቴ ስብስብ የሆነው ቸልሲ ከ ሮማ ጋር ይፋለማሉ።
⬛ ፒኤስጂ በሜዳው አንደርሌክትን ምሽት 4:45
ላይ ይገጥማል።
⬛ ባርሴሎና ከሜዳው ውጪ ምሽት 4:45 ላይ
ኦሎምፒያኮስን ይገጥማል።
⬛ ማንችስተር ዩናይትድ በኦልትራፎርድ ምሽት 4:45 ላይ ቤነፊካን ይገጥማል።
⬛ የብሬንዳን ሮጀርስ ስብስብ ሴልቲክ በሜዳው
የጀርመኑን ክለብ ባየርሙኒክን 4:45 ላይ ይገጥማል።
⬛ ባዜል በሜዳው የሩስያውን ክለብ ሲኤስኬ ሞስኮን ምሽት 4:45 ላይ ይገጥማል።
⬛ አትሌቲኮ ማድሪድ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ካራባግን 4:45 ላይ ይገጥማል።
⬛ የጣሊያኑ ክለብ ጁቬንትስ ወደ ፖርቹጋል በማቅናት ስፖርቲንግ ሊዝበንን ምሽት 4:45 ላይ ይገጥማል።