MOURINHO'S FELLAINI CONCERN
ጆዜ ሞሪኖ ስለ ማሩዋን ፌላኒ ኩንትራት ተጠይቀዉ አሁን ኩንትራቱ አልጨረሰም ኩንትራቱ በክረምቱ ነዉ የሚያበቃዉ፣ እስከዛ ባለዉ ከሱ ጋር አዲስ ኩንትራት ለማስፈረም ንግግር አደርጋለን።
ጨምረዉም ጆዜ ስለ ሉክሸዉ ሲጠየቁ እኔ ስለሱ ምንም ማዉቀዉ ነገር የለም ብለዋል። (sky sport)
በዘመናዊው አይቴል S11 ስልክ ህይወትዎን አኗኗርዎን ቀለል ያድርጉ!
PASTORE ON THE MOVE?
ጃቪየር ፓስትሮይ በጥሩ የዝውውር መስኮት ክለቡን ፓርሴን ጀርሜን በመልቀቅ ወደ ሌላ ክለብ ማምራት ይፈልጋል ተብሎል።
የመልቀቁ ምክንያት ደግሞ በፒኤሲጂ በቂቦታ መግኝ አለመቻሉ ነዉ። በክረምቱ የዝውውር ጊዜ ፒኤሲጂ ኔይማር ጁኔርን ከባርሴሎና ኬሊያን ሞፓፔን ከሞናኮ በማስፈረሙ ቦታዉ በሁለቱ ኮክብት በመያዙ የመሰለፍ እድሉ አንሶል።
አርጀንቲናዊዉ አጥቂ በዚህም ምክንያት ክለብ መልቀቅ እንደሚፈልግ ታዉቆል። (bbc)
'SPURS WANT GOMES'
ቶተንሃም ከባርሴሎናዉ አማካኝ አንድሬ ጎሜዝ ላይ አነጣጥሮል።
ፖርቹጋላዊዉ አማካኝ ጎሜዝ በባርሴሎና ከመቀመጫ ወንበር ተነስቶ ወደ ሜዳ መግባትን አልመዉደዱ ክለቡን የመልቀቁ ጉዳይ እዉን እንደሚሆንላቸዉ ለቶተንሃሞች ልጁን ለማስፈረም ጥሩ እድል ነዉ እየተባለላቸዉ ይገኛል።
በዚህም ጎሜዝ በሴሪያዉ ክለብ ጁቬንትስም ይፈለጋል። ሁኖም ቶተንሃም ከጁቬንትስ ልጁን ለማስፈረም ትልቅ ፈተና ይገጥመዋል ተብሎል። (mundov deportivo)
MASCHERANO TO LEAVE?
የቀድሞዉ የቀዩቹ ሊቨርፑሎች የተከላካይ አማካኝ የአሁኑ የባርሴሎና ተጫዋች የሆነዉ አርጀንቲናዊዉ ጃቪየር ማሻራኖ ስለወደፊት ነገር ከአሁኑ ልናገር አልችልም ምክንያቱም አለ እኔ በባርሴሎና ደስተኛ ነኝ፣ በባርሴሎና ከተማ በዙ ግዜ ቆይቻለሁኝ፣ እስካሁን ከክለብ አጋሮቸ ጎደኞቸ ጋር በጣም በፍቅር ቆይተናል።
የአሁኑን አመት ሲዝን በድል ለማሳለፍ ከአሁኑ ጠንክረን እየሰራን ነዉ። በተለይ ከሀገሬ ልጅ ሊዩነል ሜሲ ጋር በመጫወቴ ከህይወቴ ስኬቶች መካከል አንዱ ነዉ ብሎል።
ማሻራኖም በመጨረሻም እኔ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ግድ የለኝም በማለት ሳቅ በሞላዉ ንግግሩ ተናግሮል። ማሻራኖም የአስተያየት መቆጫዉ ላይ ላደረጉለት አስተያየት ራዲዩ 5 አመስግኖል። (marca)
COUTINHO UPDATE
ኮንቲኒሆ ወደ ባርሴሎና ዝውውሩን ጨርሶል እየተባለ ነዉ። ፊሊፕ ኮንቲንሆ ሊቨርፑል በ€150 million ለባርሴሎና ሽጦታል የሚሉ ዜናወች ተበራክተዋል። ጉዳዩ በግልፅ ባይታወቅም ባርሴሎና ኮንቲኒሆን አዘዋዉሮል ተብሎል።
ጉዳዩም በግልፅ በቅርቡ ይፋ ይሆናል ተብሎል ሲል AS ዘግቧል።
MAN UTD EYE MEUNIER
ማንቸስተር ዩናይትዶች £30 million ሂሳብ ወጪ በማድረግ የፓሪሰን ዥርሜዩን ተመላላሽ ተከላካይ ቶማስ ሚውነርን ለማዛወር አቅደዋል ብሏል Sunday Express ጋዜጣ።
ሙኒየር ባፓርክ ደ ፍራንስ ዳኒ አልቬስ ክለቡን ከተቀላቀለ በኃላ በቋሚነት የመሰለፍ እድል ተነፍጎታል።
እናም ጆዜ ሞሪንዎ የቤልጂየሙ ኢንተርናሽናል የረጅም ጊዜ አድናቂ በመሆናቸው በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ ወደ ኦልትራፎርድ ሊያዛውሩት ፈልገዋል።
NO MAN CITY MOVE FOR ALEXIS IN JANUARY
ማንቸስተር ሲቲዎች አሌክሲስ ሳንቼዝን ለማዛወር በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ ምንም አይነት ጥያቄ አያቀርቡም ፤ ይልቁንም በነፃ የዝውውር ሂሳብ በቀጣዩ ክረምት ሊያመጡት ጥረት ያረጋሉ ያለው የDaily Mirror ዘገባ ነው።
ሲቲዎች የ28 አመቱን አጥቂ ባለፈው ክረምት ሊያዛውሩት ሙከራ አድርገው ያቀረቡት የ£60 million ሂሳብ በመድፈኞቹ ውድቅ ተደርጎባቸዋል።
በቅርቡ በተሰሙ ሪፖርቶች መሰረት የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ቺሊያዊውን አጥቂ ለማስፈረም በጥሩ የዝውውርች መስኮት ላይ ጥያቄ ያቀርባል ተብሎ ቢጠበቅም ሲቲዎች በክረምቱ ዝውውር ድርድር ወቅት አርሰናሎች ባሳዮአቸው ድርቅ ያለ አቋም ደስተኛ አልነበሩም ሲል ሚረር ዘግቧል።
ARSENAL & MAN UTD CHASE BARCA WINGER
ማንቸስተር ዩናይትድ እና አርሰናሎች የባርሴሎናውን የክንፍ መስመር ተጫዋች ጆዜ አርናይዝን ማዛወር ይፈልጋሉ ሲል Mundo Deportivo ዘግቧል።
አርናይዝ ባርሴሎናን በክረምቱ የተቀላቀለው ከሪያል ቫላዶሊድ ሲሆን እስካሁን እየተጫወተ ያለው በባርሴሎና ቢ ቡድን ውስጥ ነው። ያም ሆኖ በኢርኔስቶ ቫልቫርዴ ባሰለፉት የመጀመሪያ ጨዋታው ላይ ሪያል ሙርሲያ ላይ በኮፓ ዲ ላሬይ ጎል አስቆጥሮአል።
ተጭዋቹ ባሁን ሰአት የ€20 million ውል ማፍረሻ ሂሳብ አንቀፅ ኮንትራቱ ላይ ያለው ሲሆን አርሰናል እና ማንቸስተር ዩናይትዶች ከባየር ሙኒክ ጋር በመሆን የአርናይዝን እድገት በቅርበት እየተከታተሉት ይገኛሉ።
LIVERPOOL PLAN €25M LEFT-BACK BID
ሊቨርፑሎች በ€25 million ሂሳብ የሮማውን ግራ ተመላላሽ ኤመርሰን ፓልሜሪን በጥር የዝውውር መስኮት ላይ ለማዛወር ጥያቄ ሊያቀርቡለት ተዘጋጅተዋል ብሏል GazzaMercato.
ፓልሜሪ አሁን ከደረሰበት የጉልበት ጉዳት እያገገመ ሲሆን ሊቨርፑሎች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ላይ ጥያቄ ያላቀረቡለት ምን ያህል እንደሚያገግም ለማየት ነበር። ምንም እንኳን ሙሉ ለሙሉ ባይሻለውም አሁንም ብራዚላዊው የየርገን ክሎፕ የዝውውር ኢላማ ነው።







No comments:
Post a Comment
አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦