✔ ማንቸስተር ዩናይትዶች ቶተንሃምን በኦልትራፎርድ አጥቅተው ይጫወቱ ይሆን ወይንስ ላለመሸነፍ ብቻ ይገባሉ?
ቶተንሃሞች ባለፈው ዲሴምበር ወር ላይ ወደ ኦልትራፎርድ መጥተው ሲሸነፉ ሽንፈታቸው በሜዳው ካደረጔቸው ስምንት ተከታታይ ጨዋታዎች የመጀመሪያው ነበር። ይሄ ሪከር
ታሪክ ባለፈው የአንፊልዱ ጨዋታ ላይም ሊቨርፑሎች የዩናይትዶችን ተከታታይ 6ት ጨዋታዎችን የማሸነፍ ሪከርድ አቻ በመውጣት ሲያቋርጡት ታይቷል። በእለቱ ቡድኑ አሰልቺ እና ሳቢ እግርኳስን አለመጫወቱን ተከትሎ የቡድኑ ተጭዋቾች ሳይቀሩ የጠሉት ቢሆንም የአሰልጣኙን ታክቲክ የመተግበር ግዴታ ስላለባቸው ብቻ ግን እየጠሉትም ቢሆን ተጫውተዋል።
ከዛ ቀን አቻ ውጤት በኃላ ቡድኑ በሊዝበን 1ለ0 አሸንፎ በትንሹ ሃድስፊልድ 2ለ1 ከተረታ በኃላ የጆዜ ሞሪንዎ የቁጣ ጩሃት በተጭዋቾቹ መልበሻ ክፍል ውስጥ እንዲሰማ አድርጔል። ደጋፊዎቹም ቢሆኑ በፖርቹጋላዊው አለቃ አጨዋወት ላይ ለመጀመሪያ ግዜ ጥያቄ ማንሳት ጀምረዋል።
ምንም እንኳን ቡድኑ ፖል ፖግባ፣ ኤሪክ ቤይሊ እና ማርዋን ፌላይኒ የመሳሰሉ ቁልፍ ተጭዋቾቹን በጉዳት ሳቢያ ቢያጣም በሊጉ ካደረጔቸው ስድስት ተከታታይ ጨዋታዎች አንድ ጎል ብቻ ብልስቆጠሩት ሃድስፊልዶች ሁለት ጎል አስተናግደው መሸነፋቸው ድንጋጤን መፍጠሩ ግልፅ ነው።
በማክሰኞው የ Carabao Cup ድል ላይ ቡድኑ ማሽነፍ መቻሉ መልካም ሲሆን ጄሲ ሊንጋር ያስቆጠራቸው ግሩም ጎሎች፣ ታዳጊዎቹ አሌክስ ትዋንዜቤ እና ስኮት ማክቶሚናይ ያሳዩት ጥሩ እንቅስቃሴ ቡድኑ ላይ ተስፋ የሚዘራ ቢሆንም ቶተንሃሞች ግን ከባድ ተጋጣሚዎች እንደሚሆኑባቸው እርግጥ ነው።
እንደ ዩናይትዶች ሁሉ 20 ነጥቦችን በመሰብሰብ በሊጉ አንድ ደረጃ አንሰው የተቀመጡት ቶተንሃሞች በማጥቃት እንቅስቃሴ የሚጫወቱ ቡድን መሆናቸው በሊቨርፑሉ ጨዋታ ታይቷል። ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው አመት ላይ በማንቸስተር ሲገናኙ ጆዜ ሞሪንዎ ፖቼቲንዎ ከኔ በተሻለ ቡድኑ ውስጥ በመቆየቱ የሚፈልገውን ቡድን ሰርቶ የመጣ አሰልጣኝ ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረው ነበር።
✔ ተጠባቂው ነገር: ማን.ዩናይትዶች በሜዳቸው እንደሚጠበቀው አጥቅተው ይጫወቱ ይሆን? ወይስ ጆዜ ሞሪንዎ አምና በሊጉ በ17 ነጥቦች በልጦአቸው የጨረሰው ቡድንን ተከላክለው ነጥብ ይዘው ለመውጣት ይገባሉ?
ፖቼቲንዎ በኦልትራፎርድ ያሉ በርካታ አድናቂዎች አሏቸው። ከነዛ መሃከልም አንዱ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ናቸው። አርጀንቲናዊው አለቃ ጆዜ ሞሪንዎ(ምንም እንኳን ቢያስተባብሉትም) ዩናይትድን በመልቀቅ ወደ ፈረንሳዩ ሃብታም ክለብ ፒ.ኤስ.ጂ ካቀኑ ፖርቹጋላዊውን በመተካት የዩናይትድን አሰልጣኝነት መንበር ለመረከብ ቀጣዩ ግለሰብ ናቸው በሚል ስማቸው በድጋሚ ከዩናይትድ ጋር ተያይዟል።
በኃላ ላይ ሞሪንዎ በFrench television ጣቢያ ላይ ቀርበው ቀልጣፋ በተባለ ንፁህ ፈረንሳይኛ ቋንቋ አቀላጥፈው እየተናገሩ ቃለ መጠየቃቸው ላይ ወሬው ሃሰት መሆኑን አጣጥለውታል። ሆኖም ይሄ የጆዜ ሞሪንዎ መለያ በሃሪ ነው። ያም ቢሆን የዩናይትድ ደጋፊዎች ቡድናቸው ነገ በሜዳው ልክ ይ8ሊቨርፑሉ አይነት አሉታዊ የመከላከል ታክቲክ ይዘው ቢገቡ ጆዜ ሞሪኖዎ ክለባቸውን ለቀው እንዲሄዱ ተቃውሞ የሚያሰሙበት በቂ ምክንያት ያላቸው አይመስልም። ሰውዬው የኦልትራፎርዱን መርከብ አነዳድ በሚገባ አጥንተውታል፤ አምና ዋንጫዎችን አሸንፏል እንዲሁም በዝውውር ገበያው ላይ ጥሩ ግዢዎችን ለክለቡ ፈፅመዋል። ከሊቨርፑሉ በተሻለ በነገው ወሳኝ ጨዋታ ላይ ጥንቃቄ የተሞላበት አልፎ አልፎ የማጥቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት ጨዋታ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ሞሪንዎ የቡድኑ ቁልፍ ተጭዋቾች ባሌሉበት ጨዋታዎች ላይ ይታደጉኛል ያሏቸውና ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት የተሳናቸውን ተጨዋቾቻቸውን መተቸታቸው አግባብ ይመስላል። አሰልጣኙ ማን.ዩናይትድን ለሚያክል ትልቅ ክለብ ስትጫወት በወር አንድ ግዜ ምርጥ አቋምህን አሳይተህ መዝናናት ሳይሆን በየጨዋታዎቹ ላይ ከ10/8 ነጥቦች የሚያሰጥህ እንቅስቃሴ የምታሳይ፤ ቢያንስ በየ10 ጨዋታዎች 8ንቱ ላይ አቋምህ ሳይወርድ መጫወት ያለብህ ተጭዋች መሆን እንዳለባቸው እንደሚያምኑ በግልፅ ተናግረዋል። ለዛም ይመስላል እንደነ ሄነሪክ ሚኪተሪያን፣ ሁዋን ማታ እና አንደር ሄሬራ የመሳሰሉ ተጭዋቾቻቸውን የተቹት። አሁንም የግራ ተመላላሽ ቦታቸው ችግር እንዳለ ነው።
ማን.ሲቲዎች ያሉበት ድንቅ አቋም የዩናይትዶችን ትንሽ ችግር ጎልቶ እንዲወጣ በማድረግ በኩል አጋልጧቸው ይሆናል። ሆኖም በክለቡ ጥሩ ነገር እንዳለ ይታያል።
ዩናይትዶች የዛሬ አመት አምና በዚህ ሰአት ካሳዩት አቋም እጅግ የተሻለ ቡድን መገንባታቸው መልካም ነገር ነው። ይሄም አሁን በያዙት ደረጃ፣ በሰበሰቡት የነጥቦች ብዛት፣ ባስቆጠሩት ጎሎች ብዛት እና በተቆጠረባቸው አነስተኛ ጎሎች የሚገለፅና የሚታይ ሆኖአል። በቻምፒየንስ ሊጉ ሶስት ተከታታይ ጨዋታዎችን ማሸነፋቸውም ሌላው ሊጠቀስ የሚገባው ጥሩ ነገር ነው። ሆኖም የነገውን ጨዋታ ጨምሮ ከባባድ ጨዋታዎችን ጥሩ በመጫወት ማሸነፍ የማይችሉ ከሆነ የቡድኑ በራስ መተማመን ሊወርድ ይችላል። ዩናይትዶች ባለፈው ሲዝን ላይ ስፐርስን በሜዳቸው ከጥሩ ጨዋታ ጋር 1ለ0 አሸንፈው ነበር። ነገም ይሄንን መድገም ይጠበቅባቸዋል።
✔ ሃሪ ኬን በደረሰበት መጠነኛ የሃምስተሪንግ ጉዳት ሳቢያ ከጨዋታው ውጪ ሆኑአል
ሃሪ ኬን ክለቡ ባለፈው ሳምንት ላይ ከሊቨርፑል ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ በደረሰበት የሃምስተሪንግ ጉዳት ሳቢያ ለነገው የምሳ ሰአት ጨዋታ እንደማይደርስ ተረጋግጧል።
ኬን ክለቡ በዌምብሌይ 4ለ1 ባሸነፈበት ጨዋታ ላይ በመጨረሻዎቹ ሁለት ደቂቃዎች ላይ ተቀይሮ እንዲወጣ የተደረገ ሲሆን ከጨዋታው መጠናቀቅ በኃላ ሞሪሲዮ ፖቼቲንዎ ሲጠየቁ ግን 'ስለደከመው ነው የቀየርነው' በሚል ምላሽ ሰጥተው ነበር።
ሆኖም ኬን ክለቡ ያደረገውን የካራቦን ካፕ ዌስትሃም ዩናይትድ 3ለ2 ሽንፈት ጨዋታ ላይ ሳይሰለፍ ቀርቶአል። አሁን ደግሞ ለኦልትራፎርዱ ወሳኝ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ የመሰለፉ ተስፋ ሙሉ ለሙሉ ያከተመ መስሏል።
ፖቼቲንዎ ስለ ጨዋታው ተጠይቀው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዲህ ብለዋል:
"ለነገው ጨዋታ ሃሪ ኬንን በማሰለፍ ሪስኩን መውሰድ አንፈልግም። ጉዳቱ የሚካበድ አይደለም። ኬንን ለሪያል ማድሪዱ የመልስ ጨዋታ ከደረሰልን የምናየው ይሆናል። ለነገው ጨዋታ ግን አይታሰብም። የነገውን ጨዋታ አያደርግም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ቶተንሃሞች ከሁለተኛው ማንቸስተር ዩናይትዶች በእኩል 20 ነጥብ በጎል ክፍያ ተቀድመው ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
ፖቼቲንዎ አክለውም የሃሪ ኬን አለመኖር በቡድናቸው እንቅስቃሴ ላይ ተፅህኖ እንደማይኖረውና ቡድናቸው በአንድ ግለሰብ ላይ ጥገኛ ሳይሆን በቡድን እንቅስቃሴ ላይ መሰረት ያረገ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
"እምናምነው በቡድን ስራ ነው። እስከ ሲዝኑ መጠናቀቂያ ድረስ ቡድንህ የተለያዩ ችግሮች ይገጥሙታል። በቡድን ያሉ ሁሉንም ተጫቾች ማመን ይጠበቅብኛል። እነርሱ ማሽን እንዳልሆኑም ነግሬአቸዋለሁ"
"ዩናይትዶች ወደ ጨዋታው የሚገቡት ከኛ በተሻለ አንድ ቀን እረፍት አድርገው ነው። ለዝግጅትና ልተጨማሪ ጉልበት ይረዳቸዋል። እኛም ከዩናይትዱ ጨዋታ በኃላ ሪያል ማድሪድ እና ክሪስታል ፓላስን ስለምንገጥም ከባድ ጨዋታዎች ከፊታችን ይጠብቁናል" ሲሉ ምናልባትም በኦልትራፎርድ ጥንቃቄ የተሞላበት ጨዋታ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

No comments:
Post a Comment
አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦