Thursday, October 26, 2017

አይቴል ሞባይል ኢትዮጵያ ጥቅምት 14 2010 ዓ.ም የሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበርን በመጎብኘት የተለያዩ ስጦታዎችን አበረከተ

አይቴል ሞባይል ኢትዮጵያ ጥቅምት 14 2010 ዓ.ም የሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበርን ጎበኘ፡፡




በጉብኝቱ ወቅትም አይቴል ሞባይል ለሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር መስራች ለሆኑት ለወ/ሮ ሙዳይ 20,000 ( ሀያ ሺህ ) ብር በጥሬ እና 30,000 ( ሰላሳ ሺህ ) ብር የሚያወጣ የትምህርት መሳርያ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡




በቦታዉ የአይቴል ሞባይል ብራንድ ማናጀር፣ የመገናኛ አካባቢ የአይቴል ነጋዴዎች እንዲሁም ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡





የትምህርት መሳርያ ቁሳቁስ ለ305 ተማሪዎችና መምህራን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን አይቴል ሞባይል በያዝነዉ ወር 10ኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በጎንደር፣ ባህር ዳር እና ኮምቦልቻ ከተሞች ተመሳሳይ የበጎ አድራጎት ስራዎችን መስራቱ
የሚታወስ ነዉ።


 ይህን መሰሉ ሰናይ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በዕለቱ የአይቴል ሞባይል ብራንድ ማናጀር ገልፀዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

አስተያየት ካልዎት ከታች ያስቀምጡ ፦

Featured Post/ቀጣይ ልጥፍ

የዝውውር ዜናዎች

  ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር...