Monday, September 28, 2020

የዝውውር ዜናዎች

 



ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር ዩናይትድን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል።  [mufcMPB]


እንዲሁም ማንቸስተር ዩናይትዶች ለእንግሊዛዊው የቦሩሲያ ዶርትመንድ ክንፍ ጃደን ሳንቾ ዝውውር የመጨረሻ ያሉትን የ90 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ እሚያቀርቡት በዚህ ሳምንት ነው።  [Liam Bradford84]


አርሰናሎች ለሁሴም አዋር ያቀረቡት የ €36m ሂሳብ ውድቅ ከተደረገባቸው በኃላ አዲስ በድጋሚ ያቀረቡት የ€38m, ሂሳብም በሊዮኖች ወዲያው ውድቅ ተደርጓል። ሊዮኖች ተጭዋቹን ለመልቀቅ እስከ €50m ድረስ እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል።  [mohamedbouhafsi]


ሆኖም ሁለቱ ክለቦች በተጭዋቹ ዝውውር ዙሪያ አሁንም ድርድር ላይ ናቸው። ሁሴም አዋር አርሰናልን መቀላቀል ይፈልጋል።  [DiMarzio]


አሁን መድፈኞቹ የመጨረሻ ያሉትን የ€40m +  €10m በጉርሻ መልክ አዲስ ሂሳብ ለፈረንሳዩ ክለብ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል።  [jamesbeng)


ማንቸስተር ዩናይትዶች ከፈረንሳዊው የቻልሲ አማካይ ንጎሎ ካንቴ ወኪሎች ጋር በዝውውሩ ዙሪያ ንግግር አድርገዋል። ሆኖም ዝውውሩ እንዲሳካ ንጎሎ ካንቴ በቼልሲ ቤት ይከፈለው የነበረውን ሳንታዊ የ£300,000 ደሞዝ ከቀነሰ ብቻ ነው። (Mirror)


ፒኤስዤዎች የ28 አመቱን ጣሊያናዊ አማካይ ጀርጊንዎ በአመት ውሰት ውል ከቼልሲ ስለሚያስፈርሙበት ሁኔታ ንግግር ላይ ናቸው። 

 (Telefoot, via Mail)


ላዚዎዎች ለስፔናዊው የ32 አመት አማካይ ዩሃን ማታ እና ለ24 አመቱ ብራዚላዊ አማካይ እንድርያስ ፔሬራ የዝውውር ለእንግሊዙ ክለብ ጥያቄ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል።  (Sun)


ቶተንሃሞች የቤኔፊካውን ሲውዘርላንዳዊ አጥቂ ሃሪስ ሴፍሮቢችን በውሰት ውል ለማስፈረም ጥያቄ አቅርበዋል። (Football Insider)


ሲቲዎች አንዴ የቤኔፊካውን የ23 አመት ተከላካይ ሩበን ዲያዝን ዝውውር ካጠናቀቁ በኃላ የ19 አመቱ ስፔናዊ ተከላካይ ሉዊስ ጋርሺያ ወደ የሚፈልገው ባርሴሎና እንዲዛወር ፍቃዳቸውን የሚሰጡት ይሆናል።  (Sport - in Spanish)


ሌዝስተር ሲቲዎች የቶሪኖውን ብራዚላዊ የ23 አመት መሃል ተከላካይ ግሊሰን ብሬመርን ለማዛወር ጥያቄ ያቀርባሉ። ተጭዋቹ የኤቨርተን የዝውውር ኢላማም ነው።  (Football Insider)


ባርሴሎናዎች የኢንተር ሚላኑን የ23 አመት አርጀንቲናዊ አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ ለማስፈረም ሲያደርጉት የነበረውን ጥረት አቋርጠዋል። 

(Calciomercato - in Italian)


ማንቸስተር ሲቲዎች በግራ ተመላላሽ ወይም በግራ ክንፍ ቦታ መጫወት የሚችለውን የ23 አመቱን ዩክሬናዊ ተከላካይ አሌክሳንደር ዚቼንኮን ባርሴሎናዎች እንዲያስፈርሙት አቅርበውላቸዋል። 

 (Mundo Deportivo - in Spanish)


ባርሴሎናዎች የ 19 አመቱን ሆላንዳዊ የአያክስ ቀኝ ተመላላሽ ተከላካይ ሰርጂኖ ደስትን ለማስፈረም ተቃርበዋል። ተጭዋቹ ዛሬ የህክምና ምርመራውን በስፔን እንደሚያደርግ ይጠበቃል።  (Mundo Deportivo - in Spanish)


ሆኖም ባየር ሙኒኮች በቅድስት ዝውውር ላይ በአያክስ እንደተከዱ ያምናሉ። ለዝውውሩ ከተጭዋቹ ጋር ከስምንት በፊት ከስምምነት ቢደርሱም ከሆላንዱ ክለብ ጋር ግን በሌሎች ጉዳዮች ላይ መስማማት አቅቷቸው ቆይቷል። 

 (Sport - in Spanish)

Sunday, September 27, 2020

እሁድ ምሽት የወጡ የዝውውር ዜናዎችና መረጃዎችን ያንብቡ - Latest Transfer News Update!

 



ሊዮን ለአማካዩ ሆሳም ኦዋር የቀረበውን የ32.8 ሚ. ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ ውድቅ በማድረግ 46 ሚ. ፓውንድ እንደሚፈልግ አስታወቀ፡፡ አርሰናል በድጋሜ

ለተጫዋቹ 36.5 ሚ. ፓውንድ እና 9 ሚ. ፓውንድ በተጨማሪ የሚከፈል ሂሳብ ለማቅረብ ተዘጋጅቷል፡፡( Football London)



ቸልሲ ለዌስትሃሙ አማካይ ዴክላን ራይስ ከ40 ሚ. ፓውንድ ከፍ ያለ የዝውውር ሂሳብ ለማቅረብ ተዘጋጅቷል፡፡ ዌስትሃም ገንዘብ ስለሚፈልግ ተጫዋቹን ሊሸጠው ይችላል፡፡  (Sun)



ዌስትሃሞች የቸልሲውን ተከላካይ አንተኒዮ ሩዲገር በውሰት ማስፈረም ይፈልጋሉ፡፡  (Sun)



ባርሴሎና ለ17 አመቱ አጥቂ አንሱ ፋቲ የቀረበውን የ125 ሚ ዩሮ የዝውውር ሂሳብ እና ብቃቱ እየታየ የሚጨመረ 25 ሚ. ዩሮ ተጨማሪ ገንዘብ ቀርቦለት ውድቅ ማድረጉ ተዘገበ፡፡ ይሁንና የክለቡ ስም አልተገለፀም፡፡ በርካታ ጋዜጦችም

ማንችስተር ዩናይትድ አጥቂውን በጣም ሲፈልገው እንደነበር አስነብበዋል፡፡ (Marca)



ቶሪኖ የአርሰናሉን አማካይ ሉካስ ቶሬራ እንደማይፈልግ አስታወቀ፡፡ ቶሪኖ ተጫዋቹን በውሰት ነው የሚፈልገው አርሰናል ግን በቋሚነት መሸጥ ነው እቅዱ፡፡ አትሌቲኮ ማድሪድ የተጫዋቹ ፈላጊ ሲሆን እሱም በውሰት ነው

ለመውሰድ ያቀደው፡፡  (Football London)



የቸልሲው አማካይ ንጎሎ ካንቴ ለዝውውር ራሱን አዘጋጅቷል፡፡ ካንቴ በቸልሲ ጨዋታዎች ላይ በቋሚነት እየተሰለፈ ቢሆንም የዌስትሃሙ ዴክላን ራይስ መምጣት ቦታውን ሊያሳጣው ይችላል፡፡ በቀጣይ አመት ለሚደረገው የአውሮፓ አህጉር ውድድር ለመመረጥ በቂ የመሰለፍ ጊዜ ስለሚያስፈልግ ወደ ሌላ ክለብ ለመሄድ ተዘጋጅቷል፡፡  (express)



ኢንተር ሚላን የቸልሲውን አማካይ ንጎሎ ካንቴ ለማስፈረም፣ ስሎቫኪያዊውን ተከላካይ ሚላን ስክሪኒር፣ እንዲሁም ክሮዒሺያዊውን አማካይ ማርሴሎ ብሮዞቪች ለቸልስ ለመስጠት ተዘጋጅቷል፡፡(90 min)



የሊቨርፑሉ ወጣት አጥቂ ርያን ብሪውስተር ከክሪስታል ፓላስ ጋር ንግግር ሊጀምር ነው፡፡ ሼፈልድ ዩናይትድ እና አስቶንቪላም ተጫዋቹን ይፈልጉታል፡፡ (Mail)



ዩድኒዜ ከሊድስ ዩናይትድ ለአማካዩ ርድሪጎ ዴ ፓውል የሚቀርበው ሂሳብ 40 ሚ. ፓውንድ መሆን እንዳልበት አስታውቋል፡፡ ሊድሶች 25 ሚ. ፓውንድ ነበር ያቀረቡት፡፡ (90 min)



ማንችስተር ሲቲ የእንግሊዛዊውን የ20 አመት አማካይ ፊል ፎደን ኮንትራት ለማራዘም ተዘጋጅቷል፡፡ ሳምንታዊ ደሞዙንም ከ30 ሺ ፓውንድ ወደ 150 ፓውንድ ሊያሳድግለት ነው፡፡  (90 min)



ሊቨርፑል፣ ሊድስ እና ብራይተን ለ16 አመቱ የማዘርዌል ተከላካይ ያቀረቡት የዝውውር ሂሳብ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ሶስቱ ክለቦች አሁን ለተጫዋቹ የሚያቀርቡት ጥቅማ ጥቅም ነው የሚጠበቀው፡፡ ሊቨርፑል ከተከላካዩ ወኪል

ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ ይዟል፡፡ (Football Insider)



በ17 አመቱ ለፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ተሰልፎ የተጫወተው እና በሪያል ማድሪድ የሚፈለገው የሬኔው አማካይ ኤድዋርዶ ካማቪንጋ በሬኔ እስከ 2021 ለመቆየት ፍላጎት አለው፡፡  (Marca)



ሪያል ማድሪድ ሰርቢያዊውን አጥቂ ሉካ ዮቪች በውሰት መልቀቅ ይፈልጋል፡፡የቀድሞ ክለቡ ኢንትራክት ፍራንክፈርት ግን ተጫዋቹን መውሰድ አይፈልግም፡፡  (AS)



ሀርታ በርሊን በቦሩሺያ ዶርትንድ የተለቀቀውን ማርዮ ጎትዜ ማስፈረም ይፈልጋል፡፡ (Bild)



የአያክሱ ተከላካይ ሰርጂኖ ዴስት ወደ ባርሴሎና ለመዘዋወር ተቃርቧል፡፡ የ19 አመቱ የቀኝ ተመላላሽ ሰኞ ባርሴሎና እንደሚደርስ እና ክለቡም ከ21 ሚ. ፓውንድ በላይ እንደሚክፈል ይጠበቃል፡፡ (De Telegraaf)



ማንችስተር ዩናይትድ የፖርቶውን ተከላካይ አሌክስ ቴሌስ እንደሚያስፈረመው ተስፋ አድርጓል፡፡ ነገር ግን ሁኔታዎች ቀስ ብለው እየሄዱ ይገኛሉ፡፡ (Fabrizio)



የዋትፎርዱ አማካይ ኢቴን ካፖ ወደ ቫሌንሺያ ለማምራት ተዘጋጅቷል፡፡  (Mirror)



ቅዳሜ የተደረጉ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ውጤት 


FT| ብራይተን 2-3 ማንችስተር ዩናይትድ

FT| ክሪስታል ፓላስ 1-2 ኤቨርተን

FT| ዌስትብሮሚች 3-3 ቸልሲ

FT| በርንሌ 0-1 ሳውዝሀምፕተን


እሁድ| ሼፊልድ ዩናይትድ 8:00 ሊድስ ዩናይትድ 

እሁድ| ቶተንሀም ሆስፐር 10:00 ኒውካስል ዩናይትድ 

እሁድ| ማንችስተር ሲቲ 12:30 ሌስተር ሲቲ

እሁድ| ዌስትሀም 3:00 ወልቭስ


ሰኞ| ፉልሀም 1:45 አስቶንቪላ

ሰኞ| ሊቨርፑል 4:00 አርሰናል



የስፔን ላሊጋ ጨዋታዎች ውጤት..


FT | ዲፖርቲቮ አላቬስ 0-0 ጌታፌ

FT | ቫሌንሺያ 1-1 ሁሴክ

FT | ኢልቼ 0-3 ሬያል ሶሲዳድ

FT | ሬያል ሴቲስ 2-3 ሬያል ማድሪድ


እሁድ| ኦሳሶና 7:00 ሌቫንቴ

እሁድ| ኢባር 9:00 አትሌቲኮ ቢልባኦ

እሁድ| አትሌቲኮ ማድሪድ 11:00 ግራናዳ

እሁድ| ካዲዝ 1:30 ሴቪያ

እሁድ| ሬያል ቫላዶሊድ 1:30 ሴልታ ቪጎ

እሁድ| ባርሴሎና 4:00 ቪያርያል



የፈረንሳይ ሊግ 1 ጨዋታ ውጤቶች..


FT| ሴንቲቴን 0-3 ሬምስ

FT| ማርሴ 1-1 ሜትዝ


እሁድ| ቦርዶ 8:00 ኒስ

እሁድ| አንገር 10:00 ብሬስት

እሁድ| ዲዦ 10:00 ሞንፔሌ

እሁድ| ሞናኮ 10:00 ስትራስቡርግ

እሁድ| ኒምስ 10:00 ሌንስ

እሁድ| ሎረንት 12:00 ሊዮን

እሁድ| ሬምስ 4:00 ፒኤስጂ



የጀርመን ቡንደስ ሊጋ ጨዋታዎች ውጤቶች..


አርብ| ኸርታ በርሊን 3 : 30 ኢንትራንክ ፍራንክፈርት


FT| ቦርሲያሞቸግላድባክ 1-1 ኡኔን በርሊን

FT| ባየርሊቨርኩሰን 1-1 አርቢላይፕዚክ 

FT| ሜንዝ 1-4 ስቱት ጋርት

FT| ኦግስበርግ 2-0 ቦርሲያዶርትመንድ 

FT| አርሜንቤስፊልድ 1-0 ኮሎኝ

FT| ሻልካ 1-3 ወርደር ብሬመን


እሁድ| ሆፈንሄም 10:30 ባየርሙኒክ

እሁድ| ፍራይቡርግ 1:00 ወልፍስበርግ


የጣልያን ሴሪያ ጨዋታዎች ውጤት..


FT| ቶሪኖ 2-4 አትላንታ

FT| ካግላሪ 0-2 ላዚዮ 

FT| ሳምፒዶሪያ 2-3 ቤኔቬንቶ

FT| ኢንተር ሚላን 4-3 ፊዮረንቲና


እሁድ| ስፔዝያ 7:30 ሳሱሎ

እሁድ| ናፖሊ 10:00 ጄኖዋ

እሁድ| ሄላስ ቬሮና 10:00 ኡዱኑዜ

እሁድ| ክሮቶኔ 1:00 ኤስሚላን

እሁድ| ሮማ 3:45 ዩቬንቱስ


ሰኞ| ቦሎኛ 3:45 ፓርማ

Featured Post/ቀጣይ ልጥፍ

የዝውውር ዜናዎች

  ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር...