ሊቨርፑል እና ቼልሲዎች ክርስቲያን ፖሊሲችን ለማዛወር የነበራቸው እድል ጨምሯል።
ይሄ የሆነው የጀርመኑ ግዙፍ ክለብ ባየር ሙኒክ አሜሪካዊውን የክንፍ መስመር ተጫዋች ላለፉት 18 ወራት ያህል ሲከታተሉት ከቆዩ በኃላ በድንገት እቅዳቸውን መቀየራቸው ነው።
ባቭሪያኖቹ በ2019 አመት ላይ እድሜያቸው የገፉ የክለቡ ተጭዋቾችን በማሰናበት በአዲስ ሊተኩ ያቀዱ ሲሆን በፑሊሲች ዝውውር ምትክ የባየር ሊቨርኩሰኑን Kai Havertz ለማዛወር ከወዲሁ ቅድመ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
________________________________________
አርሰናሎች Henrikh Mkhitaryan የእግር ጣት ጉዳት በማስተናገዱ እስከ ፌበርዋሪ ድረስ ከሜዳ እንደሚርቅ ገለፁ።
የ29 አመቱ አርሜኒያዊው ኢንተርናሽናል ጉዳቱን ያስተናገደው ቡድኑ ከቶተንሃም ጋር በCarabao Cup በቶተንሃም ሲሸነፍ ነው።
አርሰናሎች ዛሬ እንዳረጋገጡት ከሆነ ተጭዋቹ ለሳምንት ያህል ምርመራ ካደረገ በኃላ የእግር ጣት ስብራት እንደገጠመው እና ጉዳቱ ቢያንስ ለስድስት ሳምንታት ከሜዳ እንሰሚያርቀው አረጋግጠዋል።
ይሄ ማለት ተጭዋቹ የገና ሰሞን የfestive fixtures ጨዋታዎች የሚያመልጡት ከሆነ የጃንዋሪ ሙሉ ፕሮግራሞችም ያመልጡታል።
________________________________________
ማንቸስተር ዩናይትዶች ጆዜ ሞሪንዎን ባሰናበቱ አምስት ደቂቃዎች ውስጥ የፓርቹጋላዊውን አለቃ ቢሮ ቁሳቁሶች በፍጥነት እንዳፀዷቸው ተገለፀ።
ፖርቹጋላዊው ኢንተርናሽናል በሊቨርፑል የ3ለ1 ሽንፈት ከደረሰባቸው ከ48 ሰአታት በኃላ ባለፈው ማክሰኞ ከስራ እንደተሰናበቱ ይታወሳል።
የዩናይትዱ አለቃ ኢድ ውድዋርድ ቢሮአቸው ከጆዜ ሞሪንዎ ጋር የ44 ደቂቃ ውይይት ካደረጉ በኃላ ንግግራቸውን በስንብት ቋጭተዋል።
የክለቡ የፅዳት ቡድን አባላት ቢሮአቸው ገብተው እንዲያፀዱት የተነገራቸው ወዲያውኑ ነበር። ግድግዳ ላይ ተለጥፈው የነበሩ የሞሪንዎ ፎቶዎች እና በቆይታቸው ያገኙአቸው ዋንጫና ሜዳልያዎችም ታሽገው እንዲወጡ ተደርገዋል።
አንድ ምንጭ ለThe Sun ጋዜጣ እንዳለው ከሆነ : "ጆዜን ወደ ታሪክ ለመቀየር 15 ደቂቃ ብቻ ነው የፈጀው። የእርሱ የነበሩ ወረቀቶችን ሁሉ ሳይቀር በነጭ ፌስታል ውስጥ ተቋጥረው እንዲወገዱ ተደርገዋል።"