ማንቸስተር ዩናይትዶች ከቴላስ ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቶዎች ለዝውውሩ €20m ድረስ እንዲከፈላቸው ይፈልጋሉ። ሁለቱም ክለቦች በሂሳቡ ላይ ድርድር ላይ ይገኛሉ። አሌክስ ቴላስ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ማንቸስተር ዩናይትድን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል። [mufcMPB]
እንዲሁም ማንቸስተር ዩናይትዶች ለእንግሊዛዊው የቦሩሲያ ዶርትመንድ ክንፍ ጃደን ሳንቾ ዝውውር የመጨረሻ ያሉትን የ90 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ እሚያቀርቡት በዚህ ሳምንት ነው። [Liam Bradford84]
አርሰናሎች ለሁሴም አዋር ያቀረቡት የ €36m ሂሳብ ውድቅ ከተደረገባቸው በኃላ አዲስ በድጋሚ ያቀረቡት የ€38m, ሂሳብም በሊዮኖች ወዲያው ውድቅ ተደርጓል። ሊዮኖች ተጭዋቹን ለመልቀቅ እስከ €50m ድረስ እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል። [mohamedbouhafsi]
ሆኖም ሁለቱ ክለቦች በተጭዋቹ ዝውውር ዙሪያ አሁንም ድርድር ላይ ናቸው። ሁሴም አዋር አርሰናልን መቀላቀል ይፈልጋል። [DiMarzio]
አሁን መድፈኞቹ የመጨረሻ ያሉትን የ€40m + €10m በጉርሻ መልክ አዲስ ሂሳብ ለፈረንሳዩ ክለብ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል። [jamesbeng)
ማንቸስተር ዩናይትዶች ከፈረንሳዊው የቻልሲ አማካይ ንጎሎ ካንቴ ወኪሎች ጋር በዝውውሩ ዙሪያ ንግግር አድርገዋል። ሆኖም ዝውውሩ እንዲሳካ ንጎሎ ካንቴ በቼልሲ ቤት ይከፈለው የነበረውን ሳንታዊ የ£300,000 ደሞዝ ከቀነሰ ብቻ ነው። (Mirror)
ፒኤስዤዎች የ28 አመቱን ጣሊያናዊ አማካይ ጀርጊንዎ በአመት ውሰት ውል ከቼልሲ ስለሚያስፈርሙበት ሁኔታ ንግግር ላይ ናቸው።
(Telefoot, via Mail)
ላዚዎዎች ለስፔናዊው የ32 አመት አማካይ ዩሃን ማታ እና ለ24 አመቱ ብራዚላዊ አማካይ እንድርያስ ፔሬራ የዝውውር ለእንግሊዙ ክለብ ጥያቄ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል። (Sun)
ቶተንሃሞች የቤኔፊካውን ሲውዘርላንዳዊ አጥቂ ሃሪስ ሴፍሮቢችን በውሰት ውል ለማስፈረም ጥያቄ አቅርበዋል። (Football Insider)
ሲቲዎች አንዴ የቤኔፊካውን የ23 አመት ተከላካይ ሩበን ዲያዝን ዝውውር ካጠናቀቁ በኃላ የ19 አመቱ ስፔናዊ ተከላካይ ሉዊስ ጋርሺያ ወደ የሚፈልገው ባርሴሎና እንዲዛወር ፍቃዳቸውን የሚሰጡት ይሆናል። (Sport - in Spanish)
ሌዝስተር ሲቲዎች የቶሪኖውን ብራዚላዊ የ23 አመት መሃል ተከላካይ ግሊሰን ብሬመርን ለማዛወር ጥያቄ ያቀርባሉ። ተጭዋቹ የኤቨርተን የዝውውር ኢላማም ነው። (Football Insider)
ባርሴሎናዎች የኢንተር ሚላኑን የ23 አመት አርጀንቲናዊ አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ ለማስፈረም ሲያደርጉት የነበረውን ጥረት አቋርጠዋል።
(Calciomercato - in Italian)
ማንቸስተር ሲቲዎች በግራ ተመላላሽ ወይም በግራ ክንፍ ቦታ መጫወት የሚችለውን የ23 አመቱን ዩክሬናዊ ተከላካይ አሌክሳንደር ዚቼንኮን ባርሴሎናዎች እንዲያስፈርሙት አቅርበውላቸዋል።
(Mundo Deportivo - in Spanish)
ባርሴሎናዎች የ 19 አመቱን ሆላንዳዊ የአያክስ ቀኝ ተመላላሽ ተከላካይ ሰርጂኖ ደስትን ለማስፈረም ተቃርበዋል። ተጭዋቹ ዛሬ የህክምና ምርመራውን በስፔን እንደሚያደርግ ይጠበቃል። (Mundo Deportivo - in Spanish)
ሆኖም ባየር ሙኒኮች በቅድስት ዝውውር ላይ በአያክስ እንደተከዱ ያምናሉ። ለዝውውሩ ከተጭዋቹ ጋር ከስምንት በፊት ከስምምነት ቢደርሱም ከሆላንዱ ክለብ ጋር ግን በሌሎች ጉዳዮች ላይ መስማማት አቅቷቸው ቆይቷል።
(Sport - in Spanish)